አለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ሀይሎች ጓድ

አለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ሀይሎች ጓድ

Share

"..የኢትዮጵያ ጀግኖች ስማቸው ስነሳ
ከሩቅ ያስፈራሉ እንደ ዱር አንበሳ.." However, either we are ready to turn left or right, it is our turns.

ሰላም አስከባሪ ሀይሎች፦ ሰላም ፈላጊዎች እና ሰላም የሚገባቸው ዜጎች ፣ የሰላም ተጠያቂዎች እና ሀላፊዎች ፣ በብጥብጥ ሳይሆን በብቃት የምአምኑ ብቁ ተወዳዳሪዎች ናቸው።
ሰላምን ከሌሎች አንጠብቅም።ነገር ግን የሌሎችን ሰላም እንጠብቃለን!
ሰላማችን በሰለማዊ መንገድ እናደርግ ፣ እናስተዳድር ፣ እንምራ! Well Come to Global Peacekeeping Forces Alliance Africa Branch ; Baga gara Jaalleewwan Humnoota Kabachiisa Nagaa Idil Addunyaa Damee Afrikaa Naga'aan Dhuftan! ; እንኳን ወደ አለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ሀይሎች ጓድ አፍርካ ቅርንጫ

04/06/2026

ኮሌጁ ለሠላም ማስከበር ማዕከል ከፍተኛ መኮንኖች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ ለሰላም ማስከበር ማዕከል ከፍተኛ መኮንኖች በተንቀሳቃሽ የትምህርት መርሃ-ግብር ሲሰጥ የቆየውን የአመራር ስልጠና አጠናቋል።

በስልጠናው ተለዋዋጭ የሆነው የአለም ፖለቲካ በአፍሪካ ቀንድ ያለው ቀጠናዊ ሁኔታ ኢትዮጵያ ሃገራችን ከጎረቤት ሃገራት የምትጠብቀውና የሚጠበቅባትን መረዳት የሚችል አመራር እየተፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።

የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ሃላፊ ሜጄር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ በሚያስችል መልኩ በስትራቴጂክ ደረጃ ትምህርት በመስጠት በቴክኖሎጂና በኢኮኖሚ የበለፀገች ሀገር ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እየተሰራና ዘመናዊ ሠራዊት እየተገነባ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ኮሌጅ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ጥላሁን ደምሴ በበኩላቸው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለበርካታ ሀገራት አገልግሎት እየሠጠች መምጣቷን ገልፀው የከፈለችውን ዋጋ ምላሽ መስጠት በሚያስችል ደረጃ ተጠቃሚ እየሆነች አይደለም ብለዋል።

ለዚህም የወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ አቅም ለማጠናከር በስልጠና የታገዘ አመራር መፍጠር ያስፈልጋል ሲሉ አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ አሰፉ ግርማይ
ፎቶግራፍ ኢፍቱ ቢራቱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

04/06/2026

አሁናዊውን የጦርነት ሥልት መምራት የሚችል መኮንን መፍጠሩን የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አስታወቀ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

አንጋፋው የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ በጦር ሜዳ አስደናቂ ጀብድ የፈፀሙ የጦር አመራሮችን በማፍራት የሚታወቅ ሲሆን ሀገር በምትፈልገው ልክ ጀግና መሪ መኮንኖችን የማፍራት ሂደቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በኢትዮጵያ ወታደራዊ ታሪክ ውስጥ ከዘጠኝ አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የጦር ትምህርት ቤቱ አፍሪካ ከቅኝ ግዛት ሳትወጣ ቀድሞ ተመሥርቶ ለአፍሪካዊን የነፃነት ትግል ቁልፍ ሚና ከመጫወቱም በላይ ዛሬ ላይ በርካታ የጎረቤት ሀገራት ወታደሮቻቸውን ለማሰልጠን ተመራጭ አካዳሚ አድርገውታል፡፡

ትምህርት ቤቱ ልዩ ልዩ ወታደራዊ ሣይንስና ጥበብን እያስተማረ የተቋሙ የጅርባ አጥንት ሆኖ እየቀጠለ እንደሚገኝ የሚገልፁት የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አዛዥ ብርጋዲየር ጄነራል ጌታቸው ሃብታሙ እየተለዋወጠ ካለው አሁናዊ የጦርነት ባህሪ ጋር ሊራመድ የሚችል የጦር መሪ መኮንን በማዘጋጀት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

ከሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ሀገራት ዕጩ መኮንኖችንም ጭምር አካዳሚው ተቀብሎ በማሰልጠን ላይ መሆኑን የተናገሩት ብርጋዲዬር ጄነራል ጌታቸው ሃብታሙ ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊ አደራን በመወጣት ላይ መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ለሦስት ዓመታት ያሰለጠናቸውን የ71ኛ ዙር መተማ ኮርስ ሰልጣኞችን በቅርቡ በድምቀት እንደሚያስመርቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዘጋቢ ውብሸት አንበሴ
ፎቶግራፍ ሃብታሙ አማረ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

04/06/2026

ችግር ለመፍጠር የሞከረው ፅንፈኛ ሃይል በምስራቅ ዕዝ እና በክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ተመትቷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

ሰሞኑን በደቡብ ጎንደር ፣በምዕራብ ጎጃም፣ በሰሜን ጎጃምና በአዊ ዞን ምስራቅ ዕዝ ባደረገዉ ኦፕሬሽን 204 ተላላኪ ፅንፈኞችን በመደምሰስ 161 ማቁሰሉን አሥታውቋል።

በሰሜን ጎጃም ዞን የተሰማራዉ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል አዲሱ መሀመድ ችግር ለመፍጠር አስቦ ህዝቡን ለመረበሽና ሁከት ለመፍጠር የተንቀሳቀሰው ፅንፈኛ በሠራዊቱ በማህበረሰቡ እንዲሁም በክልሉ የፀጥታ አካላት መመታቱን ተናግረዋል።

በዚህ ቀጠና ጠላትን መደምሰስና ማቁሰል የተቻለ ሲሆን ህብረተሰቡ ለሰላም ያለውን ፅኑ ፍላጎት እና የዘራፊውን ፅንፈኛ ተልዕኮ አንግበው ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ያለውን የመረረ ጥላቻ አሳይቷል ነዉ ያሉት።

በምዕራብ ጎጃምና አዊ ዞን የተገኘዉን የዕዙ ሠራዊት ድል አስመልክተዉ የተናገሩት ኮር አዛዡ ብርጋዲየር ጄኔራል መላኩ ገላነህ በተሰማሩባቸዉ ቀጠናዎች በተለይም በፍኖተ ሰላም እና በቲሊሊ ከተሞች ዙሪያና አካባቢዎች የአካባቢዉን ሰላምና ፀጥታ ለማናጋት አቅዶ የመጣዉ የጠላት ሀይል በኮሩ ክፍለ ጦሮች እና ስታፍ ክፍሉ እንዲሁም በጥምር ጦሩ መመታቱን ገልፀዋል።

በዚህ ከፍተኛ ኦፕሬሽን በጠላት ላይ የሰዉ ሀይል እና የቁሳቁስ ኪሳራ የደረሰ ሲሆን ፣ የተደመሰሰ ፣ የቆሰለ ፣ የተማረከ ፣ እጅ የሰጠ የጠላት ኃይል ከመኖሩ በተጨማሪ፣ ብሬን፣ ክላሽ ፣ የቃታ መሳሪያ እና የተለያዩ ተተኳሾች ተማርከዋል።

ከተደመሰሱት የፅንፈኛው አባላት መካከልም በእነሱ አሰያዬም ሙልጌታ የተባለ የፅንፈኛዉ ሻለቃ አዛዥ ፣ዋሴ ወርቁ ጎድ አዛዥ ፣ጤናዉ አቻም ክፍለጦር አዛዥ የተባሉ እና የቡድን መሳሪያ ተኳሾች ይገኙበታል።

በደቡብ ጎንደር ዞንም የዕዙ ሠራዊት በደብረ ታቦር፣ በእስቴ፣ በአንዳቤት፣ በስማዳ፣ በሳሊ፣ በንፋስ መውጫ፣ በታች ጋይንት፣ በላይ ጋይንት እና ክምር ድንጋይ ላይ ፅንፈኛዉ ያለ የሌለውን ሀይል ከተደበቀበት ጉድጓድ አሰባስቦ የህብረተሰቡን ሰላም ለማወክ ቢመጣም በሠራዊቱ በክልሉ የፀጥታ ሀይል የተቀናጀ ኦፕሬሽን ጠላት ሙትና ቁስለኛ መሆኑን የቀጠናዉ ኮር ምክትል አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ልጃለም ምትኩ አብራርተዋል።

በጠላት ላይ ማቴሪያላዊና ሰብዓዊ ኪሳራ የደረሰ ሲሆን ጠላት ተደምስሷልም ቆስሏልም ፣የተማረከ ክላሽ፣ የቃታ መሳሪያ እና ጂም 3 መሳሪያ መኖሩም ተገልጿል።

በቀጠናው ግዳጃቸውን በአመርቂ ውጤት እየፈፀሙ ያሉት ክፍለጦር አመራሮች እንደተናገሩት ሠራዊቱ ጠላቱን ጠንቅቆ የሚያውቅ እና ለሚሰጠው ግዳጅ አስፈላጊውን ሞራላዊና ወታደራዊ ዝግጅት በማድረግ በጠላት ላይ ከፍተኛ ጥቃት በመፈፀም ተስፋ እንዲቆርጥ አድርገዋል። ዘገባዉ የኮሮች የሰራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነዉ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

03/06/2026

ለሀገሩ እና ለህዝቡ ሠላም የቆመው ሠራዊት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

ወትድርና በታሪክ በደም የሚፃፍበት ራስን አሳልፎ በመስጠት ሌሎችን የማኖር ክብር ነው። ወታደር መነሻው የሃገር ፍቅር መዳረሻው ደግሞ የሀገር ክብር ነው። ወታደር ፅፎ የሚያልፈው ታሪክ በማንም የማይፈፀም የፍቅር ጥግ የሚንፀባረቅበት ታላቅ ፅናት ነው።

ወታደር ህዝባዊ ነው የምንለው በተግባር ነው እንጅ ለይስሙላ አይደለም። ደሙን አፍስሶ ሀገር ማፅናት አጥንቱን ከስክሶ ትውልድ ማኩራት ህይወቱን ገብሮ ነፍስ መዝራት ለሀገር ለህዝብ ሲል ራስን መርሳት የምቾትና የተድላ ህይወትን መዘንጋት የወታደር መለያ ባህሪው ነው።

እየሞቱ ያኖራሉ ፣እየደሙ ያፈቅራሉ፣እየተራቡ ያጉርሳሉ ያጠግባሉ፣ እየተጠሙ ያጠጣሉ፣ እየቆሰሉ ያክማሉ እየተራዙ ያለብሳሉ በአጥንታቸው ፍላፅ ሀገር ያፀናሉ በደማቸው ጠብታ ደንበር ያስከብራሉ በፈርጣማ ክንዳቸው ጠላት ይመክታሉ ድል አድራጊነታቸው ይደመስሳሉ።

በማይናወጥ የሀገር ፍቅር እንዲሁም ጀግንነታቸው ሰንደቅ-ዓላማቸውን ከፍ አድርገው በክብር ያውለበልባሉ ሀገርን ያደምቃሉ። ለእናት ሀገራቸው ለሰንደቅ-ዓላማቸው ክብር ሲሉ በማይመች አስቸጋሪ ስፍራዎች ውስጥ በሞት አፋፍ ይራመዳሉ። የፍቅራቸው ልክ ወሰን አልተገኘለትም የመውደዳቸው ልክ ደንበር አልተበጀለትም የጀግንነታቸው ከፍታ አይገመትም።

ሳይሰስቱ ሀገር ህዝባቸውን ያፈቅራሉ። ሳይቀንሱ ይወዳሉ ወደር በሌለው ጀግንነት ወደፊት ይገሰግሳሉ በድል ይረማመዳሉ።

እነሱ ሀገራቸውን የሚነካባቸውን ህዝባቸውን የሚተነኩስባቸው አይወዱም ሀገር ስትነካ ያማቸዋል ህዝብ ሲደፈር ያንዘረዝራቸዋል።

ከራስ በላይ ንፋስ አልያም ከራስ በላይ ሰማይ በሚባልበት አለም ውስጥ ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ይላሉ። ከመኖር ይልቅ ማኖርን ያስቀድማሉ። ከራሳቸው መኖርን የሚመኙት ከሀገርና ከህዝብ አስከትለው እንጅ አስቀድመው አይደለም።

የሀገር ፍቅር ተሸክመው ተስፋና ምልክት የሆነችውን ሰንደቅዓላማቸው አስቀድመው ይገሰግሳሉ። ለሀገር ለወገን ሞት ለመስጠት እነሱ ሞት ወዳለበት ይተማሉ የሞትን ምሽግ ጥሰው የከበደውን ቋጥኝ ደርምሰው የጠላትን የክፋት ሴራ አፈራርሰው በኩራት ይቆማሉ።

ጀግንነት፣አትንኩኝ ባይነት፣አንድነት እና ኢትዮጵያዊነትን አዛኝነትን ፣ሩህሩህነትን ፣መልካምነትን በጥቅሉ ከራስ በፊት ሀገርና ህዝብ ማለትን በአንድ ላይ አቅፎ መያዝና በአንድ አጣምሮ መጓዝ የኢትዮጵያ ወታደር ሁሉንም የተቸረው ፀጋ መሆኑን አስመስክሯል።

የኢትዮጵያ ወታደር የሀገር መከታና የወገን አለኝታ ከዕለት ጉርሱ ቀንሶ እንኩ ብሉልኝ ከተሰጠችው የኮዳ ውሀ ጠብታ ቀንሶ እንኩ ጠጡልኝ እኔ ልሙት እናንተ በሰላም በፍቅር ኑሩልኝ የሚል ነው እናም ህዝባዊ ነው የምንለው በተግባር ነው። ክብር ለሀገር ባለውለታ ወታደሮች ።

በውበቴ አማረ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

01/06/2026

የምስራቅ ዕዝ አባላት በአስተማማኝ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኙ ገለፁ።

የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም.

በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ የሚገኘው የምስራቅ ዕዝ አንድ ክፍለጦር አባላት በአስተማማኝ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኙ የኮሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል ሬድዋን ሬባቶ ገለጹ።

ኮሎኔሉ በስፍራው ተገኝተው የሬጅመንቱን ዝግጁነት ምልከታ ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት መሪ ሁለገብ አመራርነትን ሲከተል ፣ የሚመራውን አሃድ ሲያበቃ ብሎም ጠላቱን ጠንቅቆ ሲያውቅ ድልን በእጁ ያደርጋል ብለዋል።

ኮሎኔል ሬድዋን ሬባቶ ወታደራዊ ሚስጥሩን የሚጠብቅ እንዲሁም የአመራሩን ትዕዛዝ እና የመፍትሔ ሀሳብ ሳይሸራርፍ የሚተገብር ሰራዊት ምንጊዜም አሸናፊ መሆኑን አስታውሰው በእነዚህ እና መሰል መለኪያዎች በአካባቢው የተሰማራው ሰራዊት በአስተማማኝ ቁመና ላይ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

የሬጅመንት አዛዥ ሻምበል ፍቃዱ ሀይሌ በበኩላቸው ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸው ግንኙነት መልካም መሆኑን አንስተው የሬጅመንቱ አባላት በአሁኑ ሰዓት ጥብቅ ወታደራዊ ዲስፕሊን ተላብሰው በላቀ ቁርጠኝነት ግዳጃቸውን እየተወጡ መሆናቸውንና በቀጣይ ለሚሰጣቸው ማንኛውም ግዳጅ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአሳተማማኝ ቁመና ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

ሃምሳ አለቃ ገመቹ ብርሃኑ የሻምበል አዛዥ ሲሆን የተሰጠንን ግዳጅ በአግባቡ በመቀበል እና ወታደራዊ ቴክኒኮችን በተገቢው ሁኔታ በመተግበር ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ላይ ነን ሲል ገልጿል።

የመልክዓ ምድር ተጽዕኖም ሆነ የአየር ንብረት ፀባይ ሳይበግረን አልያም የጽንፈኛ የሀሰት ወሬ ሳያደናግረን ጠላትን የገባበት ገብተን አየደመሰስነው እንገኛለን በማለት የተናገረው ደግሞ አስር አለቃ አሪፌ አባስ ነው። ዘጋቢ አበበ ደባልቄ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

01/06/2026

የሞዛምቢክ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም

በሞዛምቢክ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ጁሊዮ ዶስ ሳንቶስ ጄን የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ አየር ኃይል የሁለትዮሽ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አድርጓል።

በጉብኝታቸው ወቅት፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የቴክኖሎጂ አቅም እና በዘርፉ እየተከናወኑ ባሉ የልማት ሥራዎች ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

​ጄኔራል ጁሊዮ ዶስ ሳንቶስ ጄን እና ልዑካን ቡድናቸው የአየር ኃይሉን የሥልጠና ተቋማት እና የከባድ ጥገና ማዕከልን የጎበኙ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል እያስመዘገበ ባለው ፈጣን የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የሰው ኃይል ግንባታ መደነቃቸውን ገልጸዋል።

​በሁለቱ አገራት አየር ኃይሎች መካከል ያለውን የጋራ ተጠቃሚነት እና የወታደራዊ ትብብርን ለማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይም ውይይት ተደርጓል።

ጉብኝቱ የሁለቱን አገራት የመከላከያ ኃይሎች የረዥም ጊዜ ወዳጅነት እና የትብብር አቅም ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

​ይህ ጉብኝት የኢትዮጵያ አየር ኃይል በአህጉራዊ ደረጃ እያሳየ ያለውን ዝና እና የአጋርነት ተቀባይነት የሚያሳይ ሲሆን፣ ለቀጣይ የቴክኖሎጂ እና የልምድ ልውውጥ በር የሚከፍት መሆኑ ተመላክቷል።

ዘጋቢ ዮናስ ጌታቸው
ፎቶ ግራፍ ማማሩ ጌትነት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

31/05/2026

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የቴክኖሎጂ የበላይነቱን እና የዝግጁነት አቅሙን ወደ ላቀ ምዕራፍ አሸጋግሯል።
ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም

በኢፌዴሪ አየር ኃይል የ5ኛ አየር ምድብ በግዳጅ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አባላት የእውቅና መርሃ ግብር አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ተገኝተው አየር ምድቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል ክህሎትና በግዳጅ አፈጻጸም ላስመዘገበው ድንቅ ስኬት እውቅና ሰጥተዋል።

አየር ምድቡ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ እንደ አዲስ የተቋቋመ ቢሆንም፣ በዚያ አጭር የዕድሜ ዘመኑ የፈጠረውን ተጽዕኖ በጀግንነትና በጥበብ በማለፍ
ሀገር የህልውና አደጋ በገጠማት ጊዜ ሁሉ ግንባር ቀደም ፈጥኖ ደራሽ በመሆን ጠላትን ድባቅ የመታ ወገንን ደግሞ ያኮራ ታሪክ መሥራቱን ዋና አዛዡ ገልፀዋል።

ሌተናል ጄኔራል ይልማ አያይዘውም፤ ምድቡ አሁን የደረሰበት የላቀ የዝግጁነት ደረጃ የአየር ኃይላችንን የቴክኖሎጂ የበላይነት የሚያመላክት ነው ብለዋል።

በሰው ኃይል፣ በውጊያ መሠረተ ልማት እና በሁሉም የዝግጁነት ዘርፎች የተመዘገበው ስኬት ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ነው ያሉት ዋና አዛዡ በቀጣይም ምድቡን በሁሉም መስክ የማዘመን ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የ5ኛ አየር ምድብ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አብዮት ድርቢ በበኩላቸው፤ ምድቡ እጅግ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አቅሞችን ታጥቆ በቆራጥነት ግዳጁን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም የሚሰጠንን ማንኛውም ግዳጅ በጀግንነት በታማኝነትና በከፍተኛ ወታደራዊ ዲሲፕሊን እንወጣለን ብለዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ፣ በግዳጅ አፈጻጸማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የምድቡ አባላት እውቅና ተሰጥቷል። በተጨማሪ ለምድቡ የግዳጅ አፈጻጸም ስኬታማነት ልዩ ድጋፍ ላደረጉ አካላት የምስጋናና የእውቅና ሰርተ-ፊኬት ተበርክቷል።

ዘጋቢ ይታያል ምህረት
ፎቶ ግራፍ ጥሩዬ ጥላሁን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

30/05/2026

የመከላከያ ውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ለከፍተኛ መኮንኖች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም

የመከላከያ ውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ከተለያዩ ሀገራት፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና መንግስታት ጋር የሚደረጉ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነቶችና ወታደራዊ ትብብሮችን በተቀናጀና በስርዓተ-ሥራ በመምራት የተቋሙን የውጪ ግንኙነት አቅም ማጠናከርና የመከላከያ ዲፕሎማሲን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ማሸጋገር እንደ ዋና ተልዕኮው አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡

የመከላከያ ውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ከኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከተለያዩ የመከላከያ ስታፍ ክፍሎች ለተወጣጡ ከፍተኛ መኮንኖች ለሦስት ቀናት የቆየ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በመከላከያ ውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል ምናሴ ሃይሉ ስልጠናው ያተኮረው በዓለም አቀፍ ግንኙነት፣ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እንዲሁም በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ላይ እንደሆነ ገልጸዋል።

የስልጠናው ዋና ዓላማም በተቋሙ ውስጥ በዲፕሎማሲ ዘርፍ የሚሳተፉ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ግንኙነቶች፣ በዓለም አቀፍ ሕጎችና ኮንቬንሽኖች ዙሪያ የሚያስፈልጋቸውን እውቀትና ክህሎት እንዲያጎለብቱ መሆኑን አስረድተዋል።

በስልጠናው የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በመከላከያ ውጪ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት የሁለትዮሽ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ዋቅቶላ አዲሱ፣ ስልጠናውን የሰጡት የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች እስከ አምባሳደርነት ያገለገሉና በዘርፉ ትልቅ ልምድ ያካበቱ በመሆናቸው በስልጠናው ጥሩ እውቀት ማግኘት መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ከሰላምና ደኅንነት አንፃር መከላከያ ዘመናዊ ትጥቅን ገዝቶ ወይም አምርቶ እንደሚጠቀም ሁሉ፣ ጠንካራና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ዲፕሎማሲን መጠቀምም ለሀገራዊ ጥቅምና ደኅንነት ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይም በዘርፉ ያሉ አቅሞችን ለማጠናከር ተመሳሳይ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች ይሰጣል ብለዋል፡፡

ዘጋቢ ደበላ ዲንሳ
ፎቶግራፍ ድምሩ ህሩይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

30/05/2026

መሰረተ ብስ ክስ እና ወቀሳ --- አንዳንድ ግለሰቦች "እኛ የእራሳችን ቋንቋ እና ባህል እያለን ለምን? እንዴት? በእኛ ቋንቋ አትፅፉም? በእኛ ቋንቋ አካዎንት አትከፍቱም ?" በማላት ብከሱም እንኳ ቋንቋችን በሚሉት ቋንቋ ስፃፍ፣ አካዎንት ስከፈት አይወዱም ፣ አይጋሩም በአጠቃላይ በማህበራዊ ሚዲያ የሚደረጉ ነገሮችን ለማድረግ ደስተኛ አይዴሉም። ይህ ማላት ከቅናት እና ምቀኝነት የመነጫ ክስ እንጂ እውነትም ለተባላው ቋንቋ እና ባህል እድገት መቆርቆር እንዳልሆነ ተረድታችሁ ከቋንቋ እና ባህል በፊት "እውነተኛ ኢትዮጵያዊነትን" በልባችሁ አኑሩ።

30/05/2026

ያለ አስተማማኝ አህጉራዊና ቀጠናዊ ሰላም ልማትና ዕድገትን ማረጋገጥ አይቻልም፦
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም

ያለ አስተማማኝ አህጉራዊና ቀጠናዊ ሰላም ልማትና ዕድገትን ማረጋገጥ እንደማይቻል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለፁ።

ኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ ካሁን ቀደም የተፈራረሙትን የሁለትዮሽ ወታደራዊ ትብብርን ስምምነት ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማድረስ ያለመ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በዕለቱ በሞዛምቢክ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም በጄኔራል ጁሊዮ ዶ ስሳንቶስ ጃኔ የተመራ ልዑክ በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ መምሪያ ሲደርስ በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

የአትዮጵያ እና የሞዛምቢክ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በተገኙበት የውይይት መድረክ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አውስተው በሀገራቱ መካከል ያለው ታሪካዊ ግንኙነት በ"ፓን-አፍሪካኒዝም" መርሆዎች፣ አንድነት፣እና ጽናት፣ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ተናግረዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ምዕራፍ መሸጋገር መቻሉን የገለጹት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው በወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት መጠናከር የቀጠናውን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ያለ ሠላምና ፀጥታ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትና ብልፅግናን ማሳካት እንደማይቻል የተናገሩት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሽብርተኝነትን በጋራ በመዋጋት፣ በሳይበር ደኅንነትና መሠል የትብብር መስኮች ዙሪያ በቅንጅት በመስራት አህጉራዊ እና ቀጠናዊ ሠላምን ለማረጋገጥ ፣ ሀገራቱ በጋራ ሊቆሙ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

የሞዛምቢክ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ጁሊዮ ዶ ስሳንቶስ ጃኔ በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራት በልዩ ልዩ የወታደራዊ ትብብር መስኮች ዙርያ በትብብር መስራታቸው ለአህጉራዊ እና ቀጠናዊ ሰላም መረጋገጥ የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጄኔራል ጁሊዮ ዶ ሳንቶስ ጃኔ አክለውም ከአትዮጵያ ጋር በዘርፈ ብዙ ወታራዊ የትብብር መስስኮ ዙርያ በቅንጅት መስራታችን በትምህርት እና ስልጠና ሰፊ ልምድ እና ተሞክሮ ለማግኘት ያስችልናል ብለዋል፡፡

የመከላከያ ውጪ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ የተካሄደው የሁለትዮሽ መድረክ ሀገራቱ ከአሁን ቀደም የተፈራረሙትን ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ወደ ተግባር የቀየረ እና ቀጣይ በሚሰሩ የትብብር ማዕቀፎች ዙሪያ አቅጣጫ ያስቀመጠ ውይይት እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም እና ልማት መረጋገጥ ካላት ቁርጠኝነት የተነሳ ሞዛንቢክን ጨምሮ በርካታ ሀገራት በተለያዩ ወታደራዊ ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እያሳዩ እንደሚገኙ የገለጹት ሜጄር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ መከላከያ እንደተቋም ያካሄደው የሪፎርም ስራ ውጤት በመሆኑ የተካሄደው የሁለትዮሽ መድረክ እንደ ሀገርም ሆነ እንደተቋም ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ ወንድማገኝ ታደሠ
ፎቶግራፍ ገነት አወቀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address

Addis Ababa