23/07/2024
Those who are misbehaving against Ethiopia and its peoples' interests are red handed for the guilty acts and corruption . Shame on Senator Menendez who took the Egyptians bribe for devastating my country Ethiopia 3 years back. Really shame on him !!
30/06/2024
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የምስራቅ ኢትዮጵያ ተቋማትን የአቅም ግንባታ ስልጠና በበረሀዋ ገነት ድሬዳዋ ላይ ሰጥተናል። ሁሉ አቀፍ የአቅም ግንባታ ስራችን በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል ።
29/06/2024
ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል፣ ውጤታማ የፊስካል ሽግግርና በክልሎች መካከል የተመጣጠነ እድገትን ማረጋገጥ ለጠንካራ የፌዴራል ስርዓት ጽኑ መሠረቶች መሆናቸውን የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡
የተከበሩ አፈ ጉባኤው ይህን ያሉት «የፊስካል ፌደራሊዝም መሰረታዊ ጉዳዮች እና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ» በሚል ርዕስ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት በተዘጋጀው የሥልጠና መድረክ ላይ ሲሆን ፌዴራላዊ ሥርዓት ከሌሎች ሥርዓተ መንግሥታት በተሻለ ደረጃ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ የሕዝቦችን በእኩልነት አብሮ የመኖርና በጋራ የመበልፀግ ዓላማ ለማሳካት የሚያስችል ሥርዓት እንደሆነ አስታውሰው ለሥርዓቱ ዘላቂነት ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል፣ ውጤታማ የፊስካል ሽግግርና በክልሎች መካከል የተመጣጠነ እድገትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡
የተከበሩ አፈ ጉባኤው አያይዘውም ያልተማከለ የፋይናንስ አስተዳደር በሚከተሉ ሀገራት ተግባራዊ ከሚደረጉ የፊስካል ሽግግሮች አንዱ የጋራ ገቢ ክፍፍል እንደሆነ አስታውሰው በአንዳንድ ሀገራት የፊስካል ሽግግር የፌዴራል መንግሥትና የበታች የአስተዳደር አካላት የጋራ ተብለው ከተለዩ የገቢ ዓይነቶች ላይ የገቢ ወይም የታክስ ምጣኔን በመጋራት የገቢ ክፍፍል የሚያደርጉ ሲሆን በሌሎች ሀገራት ደግሞ የጋራ ተብለው በተለዩ ገቢዎች ላይ ታክስ የመጣል እና የመሰብሰብ ሥልጣን ለፌዴራል መንግሥት ብቻ በመስጠት የፌዴራል መንግሥቱ የሰበሰበውን ገቢ በተለያየ መርህ ላይ በመመሥረት ገቢው በፌዴራል መንግሥት እና በክልሎች መካከል እንደሚከፋፈል አስረድተዋል፡፡
የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ዕድገትን ለማረጋገጥና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚዘጋጁ ቀመሮችን፣ ምክረ ሃሳቦችን፣ የሕግ ማዕቀፎችንና የአሠራር ሥርዓቶችን ጥራት በማረጋገጥና ተግባራዊ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ምክር ቤቱ የማይተካ ሚና እንዳለው አስገንዝበው የምክር ቤቱ አባላት በእውቀትና በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ለማሳለፍ እንዲህ አይነቱ ሥልጠና ያለው ጠቀሜታ በእጅጉ የጎላ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡
የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥትና የምክር ቤቱን ሥልጣንና ተግባር ለመዘርዘር ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ መሠረት የክልሎችና የፌዴራሉ መንግሥት የጋራ ተብለው የተመደቡ ገቢዎች በሁለቱ መካከል የሚከፋፈልበትንና የፌዴራሉ መንግሥት ለክልሎች ድጎማ የሚሰጥበትን ቀመር እንደሚወስን በግልጽ ተደንግጎ አንደሚገኝ ይታወቃል።