30/01/2022
በአፉር ክልል የስፖርት ለሁሉም የንቅናቄ መርሃግብር ማስጀመሪያ መድረክ በአይሳኢታና በአዋሽ-7 ኪሎ ከተሞች ተካሄደ፡፡
**************************************************
“ስፖርት ለሁሉም!!! ሁሉም ለስፖርት” ሚል መሪ ቃል ከጥ 22/2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 30/2014 ዓ.ም ድረስ የሚቀይ የአፋር ክልል የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የስፖርት ለሁሉም የንቅናቄ መርሃግብር ማስጀመሪያ መድረክ በአይሳኢታ እና በአዋሽ-7 ከተሞች የተካሄደ ሲሆን በአይሳኢታ ከተማ የወረዳና የከተማ መስተዳድር አመራሮችና ነዋሪዎች እንዲሁም ታዋቂ አርቲስቶች የተሳተፉ የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የ3 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የእግር ጉዞ የተካሄደ ሲሆን በአጠቃላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው 210 ተማሪዎች፣ 125 የመንግስት ሰራተኞች እና 245 የከተማው ማህበረሰብ ተሳትፈውበታ፡፡
በተመሳሳይ በአዋሽ-7 ኪሎ ከተማ በተካሄደው የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ 109 ተማሪዎች፣ 77 የመንግስት ሰራተኞች እና 99 የከተማው ማህበረሰብ የተሳተፉ ሲሆን በተጨማሪ በንቅናቄ መርሃ ግብሩ በጦርነቱ ለተጎዱ የደም ልገሳ ስነስርዓት ተካሂዷል፡፡
በቀጣይም እስከ ግንቦት 30/2014 ዓ. ም ድረስ በክልሉ በሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ መሰተዳድሮች በተከታታይ በሚዘጋጁ የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የስፖርት ለሁሉም የንቅናቄ መርሃግብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአፋር ክልል የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አመራሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች እያበረታቱና እየደገፉ ይገኛሉ፡፡
09/01/2022
⚽የጨዋታ ቀን
የ33ኛ አፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ዛሬ በሁለት ጨዋታ ይጀምራል
ምድብ አንድ
ካሜሮን🆚ቡርክናፋሶ
ምሽት 1:00
🏟ኦሌምቤ ስታድየም [ካሜሮን]
ኢትዮጵያ🆚ኬፕቬጂ
ምሽት 4:00
🏟ኦሌምቤ ስታድየም [ካሜሮን]
22/12/2021
በአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ተደረገ
***********************
በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክሉ 25 ተጫዋቾችን ዝርዝር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ አህጉራዊ ውድድር መመለሱ ይታወቃል።
ዋልያዎቹ በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ አንድ ከአስተናጋጇ ካሜሩን፣ ኬፕ ቨርዴ እና ቡርኪና ፋሶ ጋር መደልደላቸው ይታወሳል።
በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የተመረጡት ተጫዋቾች ዝርዝር፦
ግብ ጠባቂዎች፤
ፋሲል ገ/ሚካኤል
ተ/ማርያም ሻንቆ
ጀማል ጣሰው
ተከላካዮች፤
አስቻለው ታመነ
ያሬድ ባየ
ምኞት ደበበ
መናፍ አዎል
አስራት ቱንጆ
ሱሊማን ሃሚድ
ረመዳን የሱፍ
ደስታ ዮሃንስ
አማካዮች፤
አማኑኤል ዮሃንስ
ጋቶች ፖኖም
ፍፁም አለሙ
ፍሬው ሰሎሞን
በዛብህ መለዩ
መሱድ ሙሃመድ
ሽመልስ በቀለ
አጥቂዎች፤
ሽመክት ጉግሳ
ሙጅብ ቃሲም
መስፍን ታፈሰ
ዳዋ ሁቴሳ
አቡበከር ናስር
ጌታነህ ከበደ
አማኑኤል ገ/ሚካኤል ሆነው ተመርጠዋል።
08/10/2021
ዋሊያዎቹ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ደቡብ አፍሪካን ነገ ይገጥማሉ
------------------------------------------------------------
በኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ከዚምባብዌ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሶስተኛ የምድብ ጨዋታውን ነገ ቅዳሜ በባህር ዳር ስቴዲየም ከባፋና ባፋናዎች ጋር ያደርጋል።
በምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታው ወደ ጋና ያቀኑት ዋሊያዎቹ በጨዋታው አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት መሸነፋቸው የሚታወስ ነው። ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ኳስ ይዞ ለመጫወትና የበላይነት ለመውሰድ ቢሞክርም በጨዋታው ግን ግብ ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል።
ጨዋታው በተጀመረ 35ኛው ደቂቃ ላይ የጋናው ሚባራክ ዋክሶ ከርቀት የሞከራት ኳስ ወደ ግብነት ተቀይራ ጨዋታው በጋና አንድ ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል።
በመቀጠል በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በባህር ዳር ስቴዲየም ዚምባቡዌን የገጠመ ሲሆን ጨዋታውን አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ከባድ የተባለው ምድብ ውስጥ የተደለደሉት ዋሊያዎቹ ለድል ያበቃቻቸውን ግብ ማስቆጠር የቻሉት በጨዋታው መጠናቀቂያ ሰዓት ላይ የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ተከላካዩ አስቻለው ታመነ ወደ ግብነት በመቀየሩ ነው።
ሙሉውን ለማንበብ፦https://bbc.in/3lnLser
17/08/2021
በካሜሩን አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ አንድ መካተቱን (መደልደሉን) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከደቂቃዎች በፊት ገለፀ። ከወዲሁ ለብሔራዊ ብድናችን መልካም እድል እንመኛለን። በመድቡ ውስጥም:-
1. ካሜሩን
2. ቡርኪናፋሶ
3. ኢትዮጵያ
4. ኬፕ ቨርድ
07/08/2021
ለተሰንበት ግደይ !
የእንዳ መስቀሏ ሳተና ብቻዋን በሮጠቺበት የ10ሺህ ሴቶች ፍፃሜ ከወርቅ ህልሟ ስኬት ሳትደርስ ቀርቷለች ። ለተከታታይ ሶስት ኦሎምፒኮች ተይዞ የነበረው የኢትዮጲያ የርቀቱ የበላይነትም ወደ ሆላንድ አቅንቷል ። የሶስት ኢትዮጵያዊያን ወግ የነበረው ፍፃሜም ሪከርድ ሰባሪዋን ለነሐስ ሜዳሊያ አብቅቷል ። የቶኪዮ ኦሎምፒክ ክስተቷ የአርሲ አሰላዋ ኮኮብ ሲፋን ለሆላንድ ወርቁን ወስዳለች ። ሌላኛዋ የሸገር ኳስ ሜዳ ልጅ የሆነቺው ትውልድ ኢትዮጲያዊት ቃል ኪዳንም ለባህሬን የብር ሜዳላያ አስገኝቷለች ።
#አንድ ወርቅ ! #አንድ ብር እና #ሁለት ነሐስ ! እስካሁን ኢትዮጵያ በቶኪዮ ! ይህ ባልተባበሩ በሚጠላለፉ በሚወቃቀሱ ደጋግመው ሃላፊነታቸውን ዘንግተው በወደቁ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ እና አትሌቲክስ አመራሮች መሃል የተገኘ የጀግኖቹ አትሌቶች ውጤት ነው ።
ነገ ጠዋት 1:00 ኤልግራንዴ ታላቁ አበበ ቢቂላ የማይደገም ታሪክ በሰራቧቸው የቶኪዮ ጎዳናዎች የወንዶች ማራቶን ይካሄዳል ።
30/07/2021
ዜና ዕረፍት!
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች እና ብቸኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ 1962 ላይ ስታሳካ የማሸነፊያዋን ጎል ግብፅ ላይ ያስቆጠራት ኢታሎ ቫሳሎ የህልፈት ዜናቸው ተሰምቷል።
ኢትዮጵያ የ3ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ስታነሳ ከቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች መካከል የነበሩት እና በፍፃሜው ግብፅ ላይ ጎል ማስቆጠር የቻሉት ኢታሎ ከወንድማቸው ሉቻኖ ቫሳሎ ጋር ለረጅም ጊዜያት ለብሔራዊ ቡድን መጫወትም ችለዋል።
በአስመራ የተወለዱት ኢታሎ ከብሔራዊ ቡድን በተጨማሪ ለሀማሴን ፣ ጥጥ ማኅበር እና ኤሌክትሪክ ከ1950ዎቹ ጀምሮ በአጥቂ ስፍራ ተጫውተዋል።
በኢታሎ ቫሳሎ ህልፈት የተሰማትንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለመላ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና የስፖርት ቤተሰብ መፅናናትን እንመኛለን።
ethiopia
24/07/2021
አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3000 ሜትር መሰናክል በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክሎ እንደሚሳተፍ ታውቋል ።
**************************************************
አትሌት ለሜቻ በዚህ ውድድር ለመሳተፍ በተጠባባቂነት ተይዞ የነበረ ቢሆንም አትሌት ኃ/ማሪያም አማረ መቅረቱን ተከትሎ ነው አትሌት ለሜቻ ግርማ እንደሚሳተፍ አፍሪካን አትሌቲክስ ዩናይትድ ፌስ ቡክ ገፅ ዘግቧል ።
አትሌት ለሜቻ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ለሀገራችን ማስመዝገቡ ይታወቃል ።
አትሌቱ በቅርቡ በተካሄደ የሞናኮ ዲያሜንድ ሊግ ውድድር በፈጣን ሰዓት ማሸነፋ ይታወሳል ።
ለአትሌት ለሜቻ መልካም ዕድል እንመኛለን ።
08/06/2021
WORLD RECORD!
Letesenbet Gidey breaks Sifan Hassan's two-day-old 10,000m world record with 29:01.03.