30/12/2023
የአዲሱ ወረዳው ስያሜ ፥ወረዳው የሚይዛቸው ቀበሌያት ላይ በአቶ ጢሞቲዎስ በቀለ የኮሬ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ እና የአደረጃጀት ኮሚቴ ሰብሳቢ ለምክር ቤቱ አባላት ሞሽን አቅርበዋል።
በዚህ መሠረት ጎርካ ወረዳ የወረዳ ስያሜ ሲሆን
ማዕከሉ ጂጆላ ከተማው እንዲሆን የምክር ቤቱ አባላት በሰፊው ከተወያዩ በኋላ በቀረበው ሞሽን ጥያቄና ማብራሪያ ከተሠጠ በኋላ ሞሽኑ በምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
በመጨረሻም ጉባኤው በጎርካ ወረዳ ተጠባባቅ ዋና አስተዳደር አቶ አገኘሁ በቀለና የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ሞሮማ ጨንዶ የኢትዮጵያ ናየደቡብ ኢትዮጵያ ባንድራ በመሥቀል እና የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ሥነ ሥርዓት በማድረግ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
30/12/2023
የኮሬ ዞን ነባር ወረዳ መስራች ጉባኤ በጂጆላ ከተማ የነባር ወረዳ ሽግግር ምክርቤት አባላት የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮ አፅድቀዋል።
1. የተከበሩ አቶ ወዳጁ ሀሰን የጎርካ ር ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
2. የተከበሩ አቶ ዮሐንስ ታደሰ የጎርካ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ
3. የተከበሩ አቶ ወንድሙ ውንጋ የጎርካ ወረዳ ፋይናስ ጽ/ቤት ኃላፊ
4. የተከበሩ አቶ ብሩክ አየለ የጎርካ ወረዳ ሠላምና ፀጥታ ሀላፊ
5. የተከበሩ አቶ ተፈራ አለቃ የጎርካ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ
6. ክብሪት ወ/ሮ ባህሯ ብዙነህ የጎርካ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ
7.የተከበሩ አቶ ዳግም ጃንቦ የጎርካ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ
8. የተከበሩ አቶ ፍፁም አራጋው የጎርካ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ
9. የተከበሩ አቶ ሳሙኤል ካዱ የጎርካ ወረዳ ፕላን ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ
10.የተከበሩ አቶ ከፍያሌው አዱላ የጎርካ ወረዳ ደን አከባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ
11. የተከበሩ አቶ ስላስ ሽሎ የጎርካ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ
12. የተከበሩ አቶ አሸብር ፀተዋ የጎርካ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ
13. የተከበሩ አቶ ወገኑ ወ/ማሪያም ሙሉነህ የጎርካ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊ
14. የተከበሩ አቶ አያሌው አሳምኖ የጎርካ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ
15. የተከበሩ አቶ ቻላቸው አባተ የጎርካ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ
16. የተከበሩ አቶ ወገኔ ገነነ የጎርካ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርትና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ
17.አቶ ሀብታሙ የልብሰው የጎርካ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት ሀላፊ
18. የተከበሩ አቶ አጥናፉ ሠለሞን የጎርካ ወረዳ ኢንቨስትመንት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ
19. የተከበሩ አቶ አሌና ጨርቆስ የጎርካ ወረዳ ውሃና ማዕድን ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ
20. የተከበሩ አቶ አብተት ታዬ የጎርካ ወረዳ ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት
21.የተከበሩ አቶ ኢሳያስ ገቡሬ የጎርካ ወረዳ ቴክኒክና ሙያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ
22. የተከበሩ አቶ ስንታየሁ ሙሉጌታ የጎርካወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ
ሆነው እንዲያገለግሉ የቀረበዉን ሹመት የነባር ወረዳ ሽግግር ምክርቤት አባላት በሙሉ ድምጽ መርምሮ አጽድቀዋል።
30/12/2023
ዜና #ሹሜት
በኮሬ ዞን ነባር ወረዳ ጂጆላን ማዕከል ያደረገ ነባር ወረዳ ሽግግር ምክር ቤት
1.የተከበሩ አቶ አገኘው በቀለ የነባር ወረዳ ዋና አስተዳደር ።
2. አቶ ዜና ረታ የነባር ወረዳ ምትክል አስተዳደርና ንግድ ኢንዳስትሪ ፅ/ቤት ሀላፊ።
3. አቶ ታጋይ ተፈራ የነባር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊው።
4. ወ/ሮ አስተር ግርማ የነባር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግኑኝነት ዘርፍ ሀላፊ።
5. አቶ እንዳልኩ ሚልክያስ የነባር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊው።
የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ አስተያየት ከሰጡ በኋላ
በሙሉ ድምፅ አፅድቀዋል።
በዕጩነት የቀረቡ ተሿሚዎችም በወረዳው ሽግግር ምክር ቤት የተሰጣቸውን ትልቅ የህዝብና የመንግስት ኃላፊነት በታማኝነትና በቅንነት ለመወጣት በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላቸውን ፈፅመዋል።
30/12/2023
ዜና #ሹሜት
በኮሬ ዞን ነባር ወረዳ ጂጆላን ማዕከል ያደረገ አዲሱ ወረዳ ሽግግር ምክር ቤት
የተከበሩ አቶ አገኘው በቀለ የነባር ወረዳ ዋና ተጠባባቅ አስተዳደር ሆነው እንዲመሩ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ ሾሙዋቸዋል።
30/12/2023
ዜና #ሹመት
የኮሬ ዞን ካርማን ማዕከል አድርጎ የሚመሠረተው ነባር ወረዳ ሽግግር ምክር ቤት አቶ ሞሮማ ጨንዶ የነባር ወረዳ ዋና አፈ-ጉባኤ እና ወ/ሮ የምስራች ተፈራ ምክትል አፈጉባኤ አድርጎ ሾሙቸዋል።
በዕጩነት የቀረቡ ተሿሚዎችም በወረዳው ሽግግር ምክር ቤት የተሰጣቸውን ትልቅ የህዝብና የመንግስት ኃላፊነት በታማኝነትና በቅንነት ለመወጣት በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላቸውን ፈፅመዉ መደበኛ ሥራቸውን ጀምረዋል።
30/12/2023
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮሬ ዞን ጂጆላን ማዕከል አድርጎ የሚመሠረተው ነባር ወረዳ የሽግግር ምክር ቤት ምስረታ በጂጆላ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በምስረታው ላይ የኮሬ ዞኑ ዋና አስተዳደር አቶ ታረቀኝ በቀለ፥የዞኑ ሽግግር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ አካላት በቀሌ፥የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጢሞቲዎስ በቀለ፥የዞኑ አስተባባሪዎችና ካብኔ አባላት ፥የኬሌ ከተማ ኬንቲባ አቶ ትግሉ ዘብዲዎስና የከተማው አስተባባሪ ኮሚቴዎች፥የሳርማሌ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ጎሹ ጌታቸውና የወረዳዋ አስተባባሪ ኮሚቴዎች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች፥ የሀይማኖት መሪዎች፥ታዋቂ ግለሰቦችና የአከባቢው ማህበረሰብ በምስረታውን እየታደሙ ይገኛሉ።
መርሃ ግብሩ በሀገር ሽማግሌዎችና ሀይማኖት አባቶች ቡራኬ ተጀምሯል።
29/12/2023
በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪ ጥሪና ትምህርት ማስጀመርን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል በተፈጠረው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዉ ወሰነ-ትምህርት ተማሪዎቻቸውን ለመጥራትና መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸዉን ሙሉ ለሙሉ ለመጀመር አልቻሉም ነበር።
በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር ከክልሉ ኮማንድፖስት፣ የጸጥታ አደረጃጀቶችና የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ሲያካሂድ ቆይቷል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ፣ የአስሩ ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ ጸጥታ አካላት ትናንት ታህሳስ 18/2016 ዓ.ም በጉዳዩ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን አሁን በክልሉ አንጻራዊ ሰላም የተፈጠረ በመሆኑ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን መጥራትና ማስተማር እንደሚችሉ ውሳኔ ላይ ተደርሷል።
በዚህም መሰረት ከጥር 1/2016 ጀምሮ ባሉ ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን ጠርተው የመማር ማስተማር ስራቸውን ይጀምራሉ።
በመሆኑም በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የተመደባችሁ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲዎቹ የሚያደርጉትን ጥሪ እንድትከታተሉ እንገልጻለን።
28/12/2023
የአዲሱ ወረዳ ስያሜና ዋና ከተማ ስያሜ እንዲሁም በወረዳዉ የተጠቃለሉ ቀበሌያትን በተመለከ አቶ ጢሞቲዎስ በቀለ የኮሬ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ እና የአደረጃጀት ኮሚቴ ሰብሳቢ ለምክር ቤቱ አባላት ሞሽን አርበዋል።
በዚህም መሠረት የአዲሱ ወረዳ ስያሜ "ሳርማሌ ወረዳ "እንዲሆንና ማዕከሉ" ዳርባ ማናና "እንዲሆን የምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ አፅድቀዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ፕሮግራሙ ተቋጭቷ።
28/12/2023
አቶ ጎሹ ጌቻቸው የአዲሱ ወረዳ ዋና አስተዳደር መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ጎሹ ጌታቸው ለምክር ቤቱ አባላትና መላው ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል በንግግራቸውም መላው ህዝብ ለሁሉም ከጎናችን እንዲሆኑ ጠይቀዋል።
የሠላም ዕሴት ግንባታ የውስጥና የውጭ ፀጥታ ላይ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በጋራ እንዲንሠራ ሲሉ ጠይቀዋል።
በግብና ማዘመን አርሶ አደር ተጠቃሚ በሰፊው መሰራት እንዳለበት አንስተዋል።
አከባቢው ከፍተኛ ፀጋ ያለበት ስለሆነ የገቢ አሰባሰብ ላይ ልዩ ትኩረት መሠራት እንዳለበትና ለሁሉም ነገር አንድ ሆነን በህብረት ከተነሳን ለአከባቢው ልማት ማምጣት እንደሚቻልና "አንድነት ሀይል ነው" በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
28/12/2023
በኮሬ ዞን ደርባን ማዕከል ያደረገ አዲሱ ወረዳ ሽግግር ምክር ቤት የተከበሩ አቶ ጎሹ ጌታቸው የአዲሱ ወረዳ ዋና አስተዳደር አድርጎ ሾሙዋችዋል
አቶ ዜና ዘካሪያስ የአዲሱ ወረዳ ምትክል አስተዳደርና ግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ።
አቶ ኢዮኤል ጠንካራ የአዲሱ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊው።
አቶ አሊና አሻሮ የአዲሱ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ።
አቶ አዝመራው አይጎዳው የአዲሱ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ሆነዉ እንዲሰሩ የሽግግር ም/ቤቱ ሀላፊነት ሰጥቷቸዋል።
ተሿሚዎችም በወረዳው ሽግግር ምክር ቤት የተሰጣቸውን ትልቅ የህዝብና የመንግስት ኃላፊነት በታማኝነትና በቅንነት ለመወጣት በሽግግር ምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።