አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዉሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት Arbaminch Zuria Woreda Water & Energy Office

አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዉሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት Arbaminch Zuria Woreda Water & Energy Office

Share

ዉሃ ሕይወት ነዉ! water is life!

26/05/2026
Photos from Ministry of Water and Energy - Ethiopia's post 04/05/2026
Photos from Arba Minch Zuria Wereda Government Communication Affairs Office's post 28/04/2026
12/03/2026

በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ማዞ ዶይሳ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት ናዳ የብዙ ወገኖቻችን ሕይወት ያለፈ ሲሆን የደረሱበት ያልታወቁ ሰዎችን የመፈለግ ሥራ በከፍተኛ ርብርብ እየተከናወነ ይገኛል ።

የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዉና እነርጂ ጽ/ቤት በዞናችን ደጋማ አካባቢዎች በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የመሬት ናዳና የጎርፍ አደጋ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው የህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል !!

Photos from አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዉሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት Arbaminch Zuria Woreda Water & Energy Office's post 04/03/2026

በአ/ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዉሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት ብልጽግና ቤተሰብ አመራሮች እና የአባላት የ2018 በጀት ዓመት ባለፉት በ6ወራት መንግስታዊና የፓርቲ ሥራዎች አፈፃፀም ሂስ ግለ ሂስ መድረክ ተካሄደ;
በመድረኩ በመ/ቤት የብልጽግና ቤተሰብ አደረጃጀት በማጠናከር በአባሉ ዘንድ የአስተሳሰብና እና የተግባር አንድነት በማጠናከር ፓርቲውን ለማሻገር በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል ።

የብልጽግና ቤተሰብ አባላት በስድስት ወራት ውስጥ የተከናወኑ የፓርቲ እና የመንግስት ተግባራት አፈጻጸም በመገምገም በቤተሰብ የሚገኙ የአባላት ምዘናም ተካሂደዋል ።

በመድረኩ የሚገኙ የሁሉም ብልጽግና የቤተሰብ አመራሮች እና አባላት ተሳትፈዋል ።

Photos from አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዉሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት Arbaminch Zuria Woreda Water & Energy Office's post 26/01/2026

በአ/ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ጫኖ ጫልባ እና ጫኖ ሚለ ቀበሌያት የተሻሻለ እፎይ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎችን በብራይት ፕሮጄክት ስርጭት እየተካሄደ ይገኛል።

Photos from አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዉሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት Arbaminch Zuria Woreda Water & Energy Office's post 18/01/2026

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!

በክርስቲያኖች ዘንድ ጥምቀት አንድም የመገለጥ፣ ሁለትም የእርቅና ዳግም የመወለድ ምልክት ነው፡፡ በቀደመው ዘመን አዳምና ሔዋን በፈጸሙት ሐጥያት የሰው ልጅ ከአምላኩ ተቀያይሞ የፍዳ ዘመናትን አሳልፏል፡፡ ዳሩ ግን ሰው በሐጥያቱ ልጅነቱን ቢነጠቅም እስከወዲያኛው ጠፍቶ አልቀረም፤ አባቱን ያስከፋ ሥህተት ቢሰራም እስከመጨረሻው ተረግሞ አልኖረም፡፡ አጥቶ የነበረውን የልጅነት ጸጋ በክርስቶስ ዳግም ተቀብሏልና፡፡ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተገኘው እሱ ራሱ ሐጥያት ኖሮበት አይደለም፤ ይልቁንም በሐጥያት እድፍ ለቆሸሸው የሰው ልጅ የእርቅ መንገድ ለመሆን እንጂ፡፡

ሥርዓተ-ጥምቀቱን ስናከብር የጥፋት መፍትሔው ይቅርታ፣ የጸብ መድሃኒቱ እርቅ እንደሆነ እያሰብን መሆን አለበት፡፡ ጸብ አይቀሬ ተፈጥሯዊ ሁነት ነው፡፡ በአባትና በልጅ፣ በፈጣሪና በፍጡር፣ በሕዝብና በሕዝብ መካከል ጸብ ይኖራል፡፡ ነገር ግን ይቅርታና እርቅም አይቀሬ የተፈጥሮ ሁነቶች ናቸው፡፡ ጸብ በአንድ አጋጣሚ የሚከሰት ድንገቴ ክስተት እንደሆነ ሁሉ፥ እርቅ ደግሞ ልዩ ልዩ ሁነቶችን ያቀፈ ጊዜ ወሳጅ ሂደት ነው፡፡ በፈጣሪና በሰው ልጅ መካከል የተፈጠረው የጸብ ግድግዳ መፍረስ የጀመረው በቃል ነው፡፡ አምላክ “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” ብሎ ሲናገር የእርቅ ሂደቱም ያኔ ጀምሯል፡፡ የተቋጨው ግን ክርስቶስ በቤተልሄም ተወልዶ፣ በዮርዳኖስ ተጠምቆ፣ መስቀሉን ተሸክሞ ከተሰቀለ በኋላ ነው፡፡

በአምላክና በሰው ልጅ መካከል የተፈጠረው ጸብ በክርስቶስ ፍጻሜውን እንዳገኘ ሁሉ፤ እንደ ሀገር ያሉብንን አለመግባባቶች በጠረጴዛ ዙሪያ ልንፈታቸው፣ የዘመናት የልዩነት እዳዎቻችን ፍጻሜ ሊያገኙ ከጫፍ ደርሰናል፡፡ የሀገራዊ ምክክር ኮምሽኑ ከተቋቋመ ወዲህ ባለፉት ሦስት ዓመታት ሰፊ ቁጥር ያላቸው ዜጎቻችን የተካፈሉበት፣ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፉ እና የልዩነት አጀንዳዎችን ያሰባሰቡ ሰፋፊ መድረኮች ተዘጋጅተዋል፡፡ ተቃርኖዎቻችን በዘላቂነት መፍትሔ የሚያገኙት በምክክራችን ፍጻሜ ነውና እንደሂደቱ ሁሉ ለፍጻሜው ርብርብ እንድናደርግ በዚሁ አጋጣሚ አደራ እላለሁ፡፡

ሥርዓተ-ጥምቀቱ የመገለጥም ምልክት ነው፡፡ ከጥምቀቱ እለት በፊት ክርስቶስ የሚታወቀው በጥቂቶች ብቻ ነበር። በልደቱ የተገለጠውን ብርሃን ለማዳፈን የሞከሩ ሄሮድስን የመሰሉ አካላትም የተሳካላቸው መስሏቸው ነበር። ከሠላሳ ዓመታት በፊት በቤተልሔም የታየው የሰው ልጅ ተስፋ መልሶ የጠፋ መስሎም ነበር። ታይቶ እንደሚጠፋ ኮከብ፤ መጥቶ እንደሚሄድ ዘመን፣ ተከሥቶ እንደሚሠወር መብረቅ የቆጠሩትም ነበሩ።

በጥምቀት ዕለት ግን እውነት ለዓለም ሁሉ ተገለጠች። ከሰማይ እና ከምድር ምስክር መጣ። እንደ ቤተልሔም በጥቂቶች ፊት ብቻ ሳይሆን፣ በዐደባባይ በብዙዎች ፊት ተገለጠ። “እርሱን ስሙት” የሚለው ቃልም ከሰማይ መጣ። ከዚህ በፊት ለእረኞች ብቻ ነበር የተነገረው። ዛሬ ግን ጆሮ ላላቸው ሁሉ ተነገረ። ያኔ በበረት ውስጥ ነበር፤ አሁን ግን በሄኖም ሸለቆ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ፣ በዓለም ፊት ሆነ።

ጊዜው ደርሶ የተገለጠ ነገር በዓላማው ፈጻሚዎች እና በዜናው ሰሚዎች መካከል የተለያየ አካሄድ አለው። የዓላማው ፈጻሚዎች ከየት፣ ለምን፣ እንዴት እንደመጣ ያውቃሉ። ወዴት፣ እንዴት እንደሚሄድ ይረዳሉ። ለምን ዓይነት ግብ እንደመጣ ይገነዘባሉ። ስለዚህም ምንም ዓይነት መሥዋዕትነት ለመክፈል ይዘጋጃሉ። አንድ ሆኖ የበራው ሻማ፣ ቀስ እያለ እልፎችን ሲያቀጣጥል ይታያቸዋል። በደመናት ውስጥ የፈነጠቀው ፀሐይ፣ ቀስ እያለ ደመናውን ሲገላልጥ ይታያቸዋል። ከአንድ እንጨት የተለኮሰው እሳት፣ ቀስ እ

Want your business to be the top-listed Government Service in Arba Minch'?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Gamo Zone
Arba Minch'
DOYESA