Arba Minch Blood and Tissue Bank Service የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት

Arba Minch Blood and Tissue Bank Service የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት

Share

❤ Give blood save life ❤

Photos from Arba Minch Blood and Tissue Bank Service የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት's post 25/05/2026

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ2017/18 ዓም ሻምፕዮን የሆነው አርሰናል ደጋፊዎች በአርባ ምንጭ ከተማ ጋሞ አደባባይ ከስጦታዎች ሁሉ የላቀ ስጦታ የሆነውን የደም ልገሳ መርሃ-ግብር በማከናወን ታሪካዊና አይረሴ ተግባር ፈጽመዋል።

‎ የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ -ህዋስ ባንክ አገልግሎት በርሃ-ግብሩ ለተሳተፉ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች እንዲሁም አስተባባሪዎች በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናዉን ያቀርባል።

‎ ግንቦት 16/2018 ዓም
‎ አርባ ምንጭ፤

Photos from Arba Minch Blood and Tissue Bank Service የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት's post 24/05/2026

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአርሴናል ደጋፊዎች የደም ልገሳ መርሃ-ግብር በአርባ ምንጭ ጋሞ አደባባይ በይፋ ተጀምሯል

Photos from Ministry of Health,Ethiopia's post 23/05/2026
Photos from Arba Minch Blood and Tissue Bank Service የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት's post 22/05/2026

የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ - ህዋስ ባንክ አገልግሎት ከብርብር የመጀመሪያ ጀረጃ ሆስፒታልና እና ከምዕራብ አባያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጋር በመተባበር ለትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና መምህራን ስለበጎ ፈቃድ ደም ልገሳ ቅስቀሳና የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠት የደም ልገሳ መርሃ - ግብር አከናወነ።

‎ በመረሃ - ግብሩ ፈቃደኛ የሆኑ በጎ ፈቃደኛ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሉ ሠራተኞች ተሳትፈዋል።

‎ የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ -ህዋስ ባንክ አገልግሎት ሆስፒታሉ እና ት/ቤቱ በመቀናጀት ላደረጉት ትብብር እንዲሁም በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ለተሳተፉ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናዉን ያቀርባል።

‎ ግንቦት 14/2018 ዓም
‎ አርባ ምንጭ፤

20/05/2026

ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሊያውቀዉና ሊገነዘብ የሚገባው ወሳኝ መረጃ!

20/05/2026

በሚተካ ደም መተኪያ የሌለውን ክቡሩን የሰው ህይወት ይታደጉ!

Photos from South Ethiopia Regional State Health Bureau's post 19/05/2026
Photos from Arba Minch Blood and Tissue Bank Service የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት's post 18/05/2026

የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ -ህዋስ ባንክ አገልግሎት ከማህበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማዕከል ጋር በመተባር ለሁለት ተከታታይ ቀናት የደም ልገሳ መርሃ ግብር አከናወነ።

‎ መርሃ -ግብሩ ከቀን 08-09/9/2018 ዓም የተከናወነ ሲሆን በሂደቱ ከተለያዩ አጥቢያ የተወጣጡ ማህበረ ምዕመናን ተሳትፈዋል።በዚህም ከመቶ አርባ አምስት (145) ዩኒት በላይ ደም ለመሰብሰብ ተችሏል።

‎ የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ -ህዋስ ባንክ አገልግሎት ቤተክርስቲያኒቱና ማህበሩ በመቀናጀት ላደረጉልን ትብብር እንዲሁም በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ለተሳተፉ ማህበረ ምዕመናን በሙሉ እጅግ በጣም ከፍ ያለ ምስጋናዉን ያቀርባል።

ግንቦት 10/2018 ዓም
አርባ ምንጭ

Photos from Arba Minch Blood and Tissue Bank Service የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት's post 17/05/2026

በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር በሲቀላ ክፍለ ከተማ "ደሜን ለወገኔ ካርዴን ለብልጽግና" በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሃ-ግብር ተካሂደ።

‎በመርሃ-ግብሩ የአርባ ምንጭ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሐብታሙን ጨምሮ የክፍለ ከተማው እና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም በርካታ ወጣቶች ተሳትፈዋል።

‎ግንቦት 0972018
አርባ ምንጭ

Photos from South Ethiopia Public Health Institute/የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት's post 16/05/2026
Want your business to be the top-listed Government Service in Arba Mintch?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Arba Minch
Arba Mintch