26/01/2026
የመጽሐፍ ምርቃት
📚 ከ11 ዓመታት በፊት ዓለምን ያስደነገጠው የሊቢያው ግድያ... እሱ እንዴት ተረፈ?
"ጓደኞቹ በISIS ሲያዙ እሱ እንዴት ቀረ? በእድል? በምክንያት? ወይስ በአጋጣሚ?"
| ከአዲስ አበባ እስከ መተማ፣ ከሱዳን እስከ ሊቢያ በረሃ... የሞት እና የሽሽት ጉዞ!
"ሃያ ሦስት" የተሰኘው የዳንኤል አብርሃ አዲስ መጽሐፍ፤ በወቅቱ የነበረውን የሊቢያን ሰቆቃ፣ የደላላዎቹን ሴራ እና የመጋዘኖቹን ጉስቁልና ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ
📖 ሰቆቃ እና ተአምር:
ጓደኞቹ ለሞት ሲነዱ፤ እሱ እንዴት ሊተርፍ ቻለ?
📖 የባሕር ላይ ውጣ ውረድ:
ሊቢያን አልፎ በጀልባ ለማቋረጥ ሲሞክር ምን ገጠመው?
📖 የአውሮፓ እውነት:
የከፈለው መስዋዕትነት የሚመጥን ካሳ በአውሮፓ አገኘ? ወይስ ሌላ ተጋድሎ?
ይህ መጽሐፍ ስለ እጣ-ፈንታ፣ ስለ ስኬት፣ ስለ ጽናት እና ተስፋ መቁረጥ አዲስ እይታን የሚሰጥ ነው።
የገጽ ብዛት - 262
ይዘት - የገዞ ማስታወሻ
26 ምዕራፎች አሉት
ደራሲ - ዳንኤል አብርሃ
አርታኢ እና አሰናኝ - ቢኒያም አቡራ
የፊታችን አርብ ሁላችንም ተገኝተን እንመርቀው!
📅 ቀን: አርብ ጥር 22 ቀን 2018ዓ.ም
📍 ቦታ: ዋልያ መጻሕፍት (4 ኪሎ፣ ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ፣ ኢክላስ ሕንጻ፣ 4ኛ ፎቅ)
የማይረሳ ታሪክ፣ የማይቀር ምርቃት!
21/01/2026
የሥራ ማስታወቂያ
ድርጅታችን መስከረም ጌታቸው መልቲሚዲያ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መደቦች አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡
1- የሥራ መደቡመጠሪያ ፡- የቢዝነስ ዲቨሎፕመንት እና ማርኬቲንግ ባለሙያ (Business development and marketing officer)
- የትምህርት ደረጃ Business development፣ Business management እና Marketing የተመረቀ የተመረቀች
- የሥራ ልምድ 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ
- ተፈላጊ ችሎታ ፕሮፖዛል የመጻፍ፣ የጨረታ ሥራዎች ክትትል እና የማስፈጸም አቅም ያለው/ያላት (በተለይም መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች NGOs ጋር የመሥራት ልምድ ያለው/ያላት ቢሆኑ ይመረጣል
- ደመዎዝ በኮሚሽን ስምምነት
- ቅጥር በኮንትራት
- ብዛት 2
2- የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡- ቪዲዮ ኤዲቲንግና ቀረጻ ባለሙያ
- የትምህርት ደረጃ በቀረጻ እና ኤዲቲንግ ደረጃ 4
- የሥራ ልምድ 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ
- ተፈላጊ ችሎታ የፈጠራ አቅም እና ትእግስት ያለው ያላት አንዲሁም ቪዲዮ ኤዲቲንግና ቀረጻ ሁለቱንም በጥራት መሥራት የሚችል/የምትችል
- ደመዎዝ በስምምነት
- ብዛት 1
ለመመዝገብ
በኢሜይል አድራሻችን [email protected] ይጠቀሙ
በስልክ ቁጥር 096202 5502
095621 0000 በመደወል መረጃ ማግኘትና መመዝገብ ይችላሉ
©Meskerem Getachew
21/01/2026
[ኅብረ ብዕር ቅጽ 3 በካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር ገጽ 119]
እየተደሰታችሁ፣ እየተዝናናችሁ የምታነብቧቸው ድንቅ ትውፊታዊ መጻሕፍት ናቸው ኅብረ ብዕር 1 2 3 ተከታታይ መጻሕፍት።
መልካም ንባብ
19/01/2026
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!
14/01/2026
እንደተለመደው---
---
ጥር 9/ 2018 ዓ.ም (ቅዳሜ ከ8:00 ጀምሮ)
ሁላችሁም በነጻ ተጋብዛችኋል!
ነገረ መጻሕፍት
ተጋባዥ እንግዳ:- መ/ር ዳንኤል ሠይፈሚካኤል (ረ/ፕሮፌሰር)
የተመረጠው መጽሐፍ
ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ (THE SIGN AND THE SEAL)
አዘጋጅና አቅራቢ:- እንዳለጌታ ከበደ
አሰናጅ:- ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ
የዝግጅት ቦታ:- FSS. አዳራሽ
በዝግጅቶቻችን ላይ በአካል በመገኘት መሳተፍ ለምትፈልጉ አድራሻችን:- ቀበና፣ የካቶሊክ ኪዳነምሕረት ትምህርት ቤት አቅራቢያ፣ ወደ ሳንፎርድ ትምህርት ቤት በሚወስደው መንገድ፣ ባማ አዲስ ሕንፃ አጠገብ፣ FSS አዳራሽ ሲሆን፣ የመገኛ ቦታው Google Map link:-
https://maps.app.goo.gl/2n1myQXCCaTteCw69?g_st=ic
ለበለጠ መረጃ:- 0976066720
0900651010
በቴሌግራም ቻናላችንም ቤተሰብ ይሁኑን:-
https://t.me/ZagolBookBank1
ከዚህ ቀደም የተደረጉ ፕሮግራሞችን ለመከታተል:-
https://youtube.com/?si=hEO0egZkKPtR1mv0
13/01/2026
ዋልያ የሃሳብ እና መጽሐፍ መድረክ
ቅዳሜ ከሰዓትዎን ስለ ቀለም አይነታ እና ትርጓሜ፣ ስለ ቀለም ፅብረቃ እና በስነ-ልቦና ላይ ስለሚያደርሱት ልውጥውጥ ስሜቶች፣ ስለ መልክ እንዲሁም ስለ ምልክቶች፣ ስለ ገፅታ ተንተርሶ ፈኪ ቀለማት ደምቀው ስለተገኙት ስለ ፈዛዞችም ኹሉ ስለሚፈጥሩት ፍልስፍና እና ትዝታ ልንወያይ ቀጠሮ ይዘናል። በዕለቱ ከጉዳዩ ጋር የትምህርት ዝግጅት እና ልምድ ያላቸውን ሙያተኞች የጋበዝን በመሆኑ ከኛ ጋር ያሳልፉ።
አቅራቢዎች፦
ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ (ቀለም ፊሎሶፊ)
ሰዓሊ ሶሎሜ ጌታቸው (ቀለም እና ትዝታ)
ቦታ፦ 4ኪሎ ኢክላስ ህንፃ ዋልያ መፃሕፍት
አዳራሽ
ቀን እና ሰዓት፦ ቅዳሜ ጥር 9 ቀን 2018 ዓም ከሰዓት 8:00 ጀምሮ
walia publisher /ዋልያ መጻሕፍት
13/01/2026
ደራስያንን የማስፈረምና ከደራስያን ጋራ የመገናኘት እድል እየተስፋፋ መጥቷል፤ አንዱ አዘጋጅ ደግሞ Jafer books ነው ይኸው የተወዳጁን ፀሐፊ Mesfin Wondwossen Abbi ሸሙኔን መጽሐፍ ቅዳሜ ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00-10:00 ለገሀር በሚገኘው አዲሱ ጃዕፈር መጻሕፍት መደብር ጎራ በሉ ተብላችኋል።
10/01/2026
መቀመጫውን በሀገረ ካናዳ ያደረገውና በታዋቂዎቹ ጋዜጠኞች፣ የጥበብ ወዳጆችና ፀሐፍያን የተቋቋመው New Perspective አዲስ ቅኝት የሬዲዮ ፕሮግራም ከዩቲብ ባሻገር ወደ ቴሌቪዥን ካደገ አንድ ዓመት መቆጠሩን አዘጋጆቹ ጋዜጠኛ ገዛኸኝ መኮንን እና ባለቤቱ ጋዜጠኛና ደራሲ ሶስና አሸናፊ ገልጸዋል።
የዩቲዩብ ገጻቸውን ሰብስክራይብ በማድረግ ደስታችንን እንግለጥ፤ ልፋታቸውን በዚህ እንክፈላቸው!
- YouTube
አዲስቅኝት | New Perspective - Ethiopian Canadian Television,Radio,Digital MagazineAddiskignit (አዲስቅኝት) / New Perspective is a dynamic Ethiopian Canadian media p...
05/01/2026
እንደሁልጊዜው በነጻ ተጋብዛችኋል!
ነገረ መጻሕፍት
በዛጎል ቡክ ባንክ አሰናጅነት
በእንዳለጌታ ከበደ አጋፋሪነት
የተመረጠው መጽሐፍ፦ የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ
አቅራቢ ኢዛና አምደወርቅ [ዶ/ር]
ቅዳሜ ጥር 2/2018 ዓ.ም
ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ
ቀበና በሚገኘው FSS አዳራሽ
04/01/2026
በተገቢው ልክ እና በበቂ ሁኔታ ባልተነበበው ተወዳጅ መጽሐፍ ላይ በወመዘክር አዳራሽ ውይይት ተደረገ!
በውይይቱ ላይ መምህር ይኩኖአምላክ መዝገቡ የመነሻ ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን መድረኩን መምህር መሠረት አበጀ አጋፍረውታል።
በMesfin Wondwossen Abbi የተዘጋጀው "ሸሙኔ" መጽሐፍ ላይ መጽሐፉን አንብበው የወደዱት ተደራስያን ሃሳብ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን በውይይቱ ላይ የተሳተፉና ሃሳባቸውን ያጋሩት በአብዛኛው በመጽሐፉ የቋንቋ ውበት የተደነቁ መሆናቸወሸንና ተደጋግሞ ሊነበብ እንደሚገባው አስታውሰዋል።
መምህር ይኩኖአምላክ በመጽሐፉ ላይ ያለኝ ትችት አለመነበቡ ነው የሚል ሃሳባቸውን ያቀረቡ ሲሆን መጽሐፉን በስፋት እንዲነበብ በተለያየ አማራጭ ሊተዋውቅ እንደሚገባም ተነስቷል።
📸 ከደራሲው የፌስቡክ ገጽ ተገኝቷል!
02/01/2026
ቅዳሜ ታኅሣሥ 25/2018 ዓ.ም
ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት [ወመዘክር]
ሸሙኔ ላይ የቀድሞ የወመዘክር ዋና ዳይሬክር የነበሩት የአአዩው መምህር ይኩኖአምላክ መዝገቡ ሃሳብ ሲያቀርቡ መምህር መሠረት አበጀ ደግሞ ያስተባብሩታል።
የምትችሉ ታደሙ!