Snnprs Trade And Market Development Bureau

Snnprs Trade And Market Development Bureau

Share

Hawassa,Ethiopia In-front of st. Gabriel Church
Hawassa, Ethiopia P.O.BOX 1987

Photos from Snnprs Trade And Market Development Bureau's post 16/05/2023

የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃንና የገላጭ ጽሑፍ መስፈርቶች ስለማያሟሉ ተመርተው እየቀረቡ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው አሳስቧል፡፡

ሀዋሳ፣ግንቦት 8/2015 ዓ.ም (ደ/ክ/ን/ገ/ል/ቢ) 91 የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች የኢትዮጵ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃንና የገላጭ ጽሑፍ መስፈርቶች ስለማያሟሉ በተጨማሪም በቁጥጥር ወቅት የተገኙ ግኝቶች እንደሚያሳዩት ምርቶቹ በአብዛኛው በሚባል መልኩ የመጠቀሚያ ጊዜ፣የአምራች ድርጅታቸው ስም ፣አስገዳጅ ደረጃ ምልክት፣መለያ ቁጥርም ሆነ አድራሻቸው ምርቱ ላይ ያልተገለጸና የሌላቸው ሲሆን ምርቱ ሊይዛቸው የሚገቡ ንጥረ ነገሮች በውል ለማይታወቅ በተጨማሪም ከሚመለከታቸው የጤና ተቆጣጣሪ አካላት ፍቃድ የሌላቸው በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እንዳያውላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡

ለጥንቃቄ የምርቱ ዓይነትና የተገኙትን ክፍተቶች ከዚህ ዜና ጋር አባሪ የተደረጉ ፎቶችን ህብረተሰባችን በትኩረት ተመልክቶ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ይጠይቃል፡፡
46፤ ዓይነት አይኦዳይዝድ ጨው
27፤ ዓይነት የምግብ ዘይት
10፤ ዓይነት ከረሜላ
5፤ ዓይነት አቼቶ
2፤ ዓይነት የለውዝ ቅቤ
1፤ ዓይነት የቫኔላ ፍሌቨር ምርቶችን

የምርት ዓይነቶች እና ብራንድ ስማቸው
የምግብ ጨዉ

1. ሳባ የገበታ ጨው(Saba IODIZED Salt)
2. ንጋት የገበታ ጨው(Nigat IODIZED SALT)
3. አዲስ ብርሃን የገበታ ጨው ADDIS BERHAN IODIZED SALT
4. ሙና የገበታ ጨው(MUNA TABLE SALT)
5. ቤዝ የገበታ ጨው/BASE IODIZED SALT
6. ጉስቶ የገበታ ጨው/GUSTO IODIZED SALT
7. ማክ የገበታ ጨው/MAK IODIZED SALT
8. አባይ የገበታ ጨው/ABAY TABLE SALT
9. መስቱራ ባለ አዮዲን የተፈጨ ጨው MESTURA REFINED & IODIZED SALT
10. መነስ ጨው /MENES IODIZED SALT
11. ሙሉ የገበታ ጨው /Mulu Table Salt
12. ኢርኮ አዮዳይዝድ ጨው ERKO IODIZED SALT
13. አርዲ የገበታ ጨው/ARDI IODIZED SALT
14. ዘመን የገበታጨው/ZEMEN IODIZED SALT
15. ዘመን የገበታጨው/ZEMEN IODIZED SALT
16. ጨረቃ የገበታ ጨው/IODIZED SALT
17. ፋና የገበታጨው/Fana Table Salt
18. ዳናት የገበታጨው
19. ሶም የገበታጨው/som iodized salt
20. ጉግሳ በአዮዲን የበለፀገ የገበታጨው/GUGSA Iodised Salt
21. ሸጋ ጨው/SHEGA Iodized SALT
22. ፍዳክ የገበታ ጨው/FDAK IODIZED SALT
23. ኡሚ የገበታ ጨው/UMI IODIZED SALT
24. ጊዜ አዮዳይዝድ ጨው/GIZE IODIZED SALT
25. ባማክ የገበታ ጨው/bamak Iodized Salt
26. ማዚ የገበታ ጨዉ/MAZI IODIZED SALT
27. አዲስ የገበታ ጨዉ/ADDIS Iodized Salt
28. የገበታ ጨው/Iodized salt
29. TANA TABLE SALT/ጣና የገበታ ጨው
30. ጣና የገበታ ጨው
31. ማኢዳ የገበታ ጨው/MAEEDA IODIZED SALT
32. አሚን ጨው/Amin iodized salt
33. ሆም የገበታ ጨው/HOME IODIZED SALT
34. ጂኤም የገበታ ጨው/GM IODIZED SALT
35. ገዳ አዮዳይዝድ የታጠበ የገበታ ጨው/ GEDA IODIZED SALT
36. ዛማ አዮዳይዝድ የታጠበ ባለ አዮዲን ጨው /ZAMA SALT
37. ሶሲ የአዮዲን ጨው/Sosi Iodized Salt
38. ብቁ የገበታ ጨው/Biku iodized salt
39. H.T.F TABLE SALT /ኤች.ቲ.ኤፍ
40. AFRAN Iodized Salt
41. ኤምሬት ጨው/Emirate IODIZED SALT
42. ስፔሻል የገበታ ጨው/Special Iodized Salt
43. ሊያ የገበታ ጨው/ LIYA IODIZED SALT
44. አፊ ጨው/AFI IODIZED SALT
45. ዩስራ ጨው/ YUSERA SALT
46. ቡዜ የገበታጨው/BUZE IODIZED SALT

የምግብ ዘይት

1. ነጃ ንጹህ የምግብ ዘይት/ NEJA Pure Edible Oil
2. ረና ንጹህ የምግብ ዘይት/ Rina Edible Pure Food Oil
3. የኛ ንጹህ የምግብ ዘይት/Yegna Pure Edible Oil
4. ኑራ ንጹህ የምግብ ዘይት /Nura Pure Edible oil
5. ሕይወት ንጹህ የምግብ ዘይት /HIWOT Edible Cooking Oil
6. ሚድ ንጹህ የምግብ ዘይት /MID Pure Edible Oil
7. ጉና ንጹህ የኑግ የምግብ ዘይት/GUNA Pure Niger Edible Oil
8. አዲስ ንጹህ የምግብ ዘይት
9. ኑር ንጹህ የምግብ ዘይት/Nur Pure Edible Oil
10. ኑራ ንጹህ የምግብ ዘይት/NuraPure Edible Oil
11. ሶፊ ንጹህ የምግብ ዘይት/Sofi Pure Edible Oil
12. ደሴት ንጹህ የምግብ ዘይት/Deset Pure Food Oil
13. HADI COOKING OIL
14. Arif cooking oil
15. ሰነዓ ንፁህ የምግብ ዘይት /Senea pure food oil
16. ቃል ንፁህ የምግብ ዘይት/Kale Pure Food Oil
17. ናዲ የተጣራ ንጹህ የምግብ ዘይት/ Nadi pure food oil
18. ሰላም ንፁህ የምግብ ዘይት/Selam pure food oil
19. ኑኑ ንፁህ የምግብ ዘይት /Nunu pure food oil
20. MIFTAH pure food oil
21. ቤላ የተጣራ የኑግ ዘይት/BELLA Pure Niger Oil
22. ጣዝማ ንፁህ የምግብ ዘይት
23. ሚና ንፁህ የምግብ ዘይት
24. ብሌን ንፁህ የምግብ ዘይት/Blen Pure Edible Oil
25. ደስታ የተጣራ የኑግ ዘይት
26. ሐዲ የተጣራ የምግብ ዘይት
27. ሳራ የኑግ የምግብ ዘይት/Sara Niger Oil

የከረሚላ ምርቶች

1. ማሂ ከረሚላ/Mahi candy
2. ኢላላ ጣፋጭ ከረሚላ/Elaala sweet candy
3. ፋፊ ሎሊፖፐ/Fafi lolipop
4. ኢላላ ሎሊፖፕ ቢግ ጃር/Elaala lolypop big jar
5. ኮከብ ከረሚላ/KOKEB candy
6. ከረሚላ
7. ከረሚላ
8. ኤም ቲ ሎሊፖፕ/MT Loliipop
9. ኤ.ኤ ከረሚላ/A.A candy
10. ምንም ገለጭ ፁሑፍ የሌለው ከረሜላ

የአቼቶ ምርቶች

1. ሮያል አቼቶ/Royal VINEGAR
2. ዋልታ አቼቶ
3. ሮያል አቼቶ/ROYAL Vinegar
4. ሌመን አቼቶ/LEMEN ACETO
5. ሸገር አቼቶ/SHEGER ACETO
የለዉዝ ቅቤ
1. በእምነት ኦቾሎኒ ቅቤ/BEMNET PEANUT BUTTER
2. ናይስ/Nice peanut butter

የቫኔላ ፍሌቨር

1. ምንም ገላጭ ጽሑፍ የሌለው የቫኔላ ፍሌቨር
2.
ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ነው፡፡

Photos from የሀላባ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ's post 12/05/2023
Photos from Ethiopian Ministry of Trade and Regional Integration's post 12/05/2023
Photos from Snnprs Trade And Market Development Bureau's post 12/05/2023

በዲጂታል ከፍያ አማካኝነት የተጀመረው የነዳጅ ግብይት አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ቢሮ ገለጸ

ሀዋሳ፣ግንቦት 4/2015 ዓ.ም (ደ/ክ/ን/ገ/ል/ቢ) የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘነበ ዛራ እንደሀገር የነዳጅ ግብይቱ ዲጂታል መሆን እንዳለበትና ትግበራው ከግንቦት1 ጀምሮ በሀገራችን በሚገኙ በሁሉም ክልሎች እንደሚጀመር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ወደ ስራ መገባቱን ገልፀው በቅድሚያ መንግስት ለሁሉም የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት መዋቅሮች፣ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት፣ ከቴሌና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ነው ወደ ስራ የተገባው ብለዋል፡፡

በደቡብ ክልል ደረጃ ከዞንና ልዩ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ሴክተር ኃላፊዎች ከሚያዚያ 25 ጀምሮ የተጀመረውን የሙከራ ትግበራን ሚያዚያ 29 ላይ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመለየት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ግንቦት 1 በክልል ደረጃ በወላይታ ከተማ በይፋ እንዲጀመር አድርገናል ብለዋል፡፡

አቶ ዘነበ ከዚህ በፊት የነበረውን የእጅ በእጅ ሸያጭ በሚፈጽሙበት ወቅት የሽያጭ ባለሙያዎች ገንዘቡን ይዘው ሲንቀሳቀሱ ለሌሎች አደጋና ለሀሰተኛ የብር ኖት መጭበርበር ችግር እንደሚጋለጡ ተናግረው አሁን ግን ግብይቱ ድጂታል መሆኑ የነዳጅ ማደያ ባለቤቶችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል፡፡

በከንባታ ዞን ዱራሜ ከተማ፣ በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማና በሃላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ግብይቱ በዲጂታል መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል፡፡

የሀላባ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አብድልኣዚዝ ከይረዲን ከዚህ ቀደም የቀደም የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ቢሮ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከሚያዚያ 25 ጀምሮ የሙከራ ትግበራ ማድረጋቸውን ጠቁመው በግንቦት 1 ቀን ብቻ በአንድ ማደያ ከ40 አስከ 50 ሽህ ብር ግብይት ተፈጽሟል ብለዋል፡፡

የሆሳዕና ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍሰሐ ታደሰ በሆሳዕና ከተማ በሚገኙ ሰድስት ማደያዎች ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ግብይቱን በዲጂታል ብቻ እንዲሆን አድርገናል ብለዋል፡፡

የደቡብ ክልል የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የኮሙዩንኬሽንና የሚዲያ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኑሪ ከድር በበኩላቸው ከግንቦት 1 ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ግብይት በዲጅታል መጀመሩን አውስተው እንደባለድርሻ አካል ከንግድና ገበያ ልማት ሴክተር ጋር በመቀናጀት ያለው የነዳጅ ግብይት በዲጅታል መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል፡፡

አቶ ኑሪ ቢሯቸው በክልሉ የሚገኙ የትራንስፖርት ባለሀብቶች የነዳጅ ግብይትን በዲጅታል ሥርዓት ብቻ እንዲጠቀሙ የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እየሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

አቶ ጌታሁን ሽጉጤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባቴና ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ መንግስት ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት ከግንቦት 1 ቀን ጀምሮ ከሆሳና ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ጋር በመቀናጀትና በመናበብ ግብይቱን በሲ.ቢ.ኢ ብር፣በፍዩል አፕ እና በነዳጅ አፕ መተግበሪያ በመጠቀም አገልግሎቱን እየሰጠን እንገኛለን ብለዋል፡፡

አቶ እሸቱ ከደላ የሆሳዕና የቴሌ ሽያጭ ባለሙያ በበኩላቸው የነዳጅ ግብይቱ ምቹና ቀልጣፋ እንዲሆን በማደያዎች በመገኘት የቴሌ ብር በመጠቀም አገልግሎቱን እየሠጠን እንገኛለን ብለዋል፡፡

የከባድ ተሸከርካሪ ሾፌር የሆኑት አቶ የሱፍ መሀመድ ከዚህ ቀደም የጥሬ ገንዘብ ይዘው ሲንቀሳቀሱ ለተለያዩ ችግሮች እንደሚጋለጡ አብራርተው አሁን ግን በአዲስ መልክ የተጀመረው የዲጂታል ነዳጅ ግብይት ሥርዓት ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል፡፡

የሀላባ ግሪን ማደያ ሥራ ስኪያጅ አቶ አንዋር ሰርጋፋ በአሁኑ ሰዓት መንግስት በስቀመጠው የዲጂታል ነዳጅ ግብይት ሥርዓት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በመስራታችን ለእኛም ሆነ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ዘርፈ-ብዙ ችግሮችን ፈቶልናል ብለዋል፡፡

Want your business to be the top-listed Government Service in Awassa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Paisa , Opposite Of Street Gabriel Church
Awassa
1987

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00