18/06/2026
በኢትዮጵያ የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለአፍሪካ አዲስ የከፍታ ምዕራፍ የሚያስጀምሩ መሆናቸውን የአፍሪካ አምባሳደሮች ገለጹ
------------
በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች አቡዳቢ የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ በተለያዩ አገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በአቡዳቢ ለሚገኙ የአፍሪካ አምባሳደሮች ሰፊ ገለጻ ሰጥቷል፡፡
ማብራሪያውን የሰጡት በአቡዳቢ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ክቡር ዶ/ር ጀማል በከር ሲሆኑ ገለጻው በዋናነት በአራቱ ቁልፍ አገራዊ አጀንዳዎች ማለትም በቅርቡ በተካሄደው 7ኛው ብሔራዊ ምርጫ፣ በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ፣ በኮፕ32 (COP32) የአየር ንብረት ጉባኤ ዝግጅት እና በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ያተኮረ ነበር፡፡
ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ጀማል በማብራሪያቸው እ.ኤ.አ. ሰኔ 1 ቀን 2026 ዓ.ም የተካሄደውና ከ50 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተሳተፉበት 7ኛው ብሔራዊ አጠቃላይ ምርጫ በአገሪቱ ታሪክ ትልቁ የምርጫ ሂደት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ምርጫውን የታዘቡት የአፍሪካ ኅብረትና የኢጋድ (IGAD) ታዛቢ ልዑካንም ሂደቱ ሰላማዊ፣ ተዓማኒና በአግባቡ የተመራ መሆኑን ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም በ12 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እየተገነባ ስላለውና በአፍሪካ አህጉር ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ ልማት ፕሮጀክት ስለሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የግንባታ ሂደት እንዲሁም ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ጉባኤ (COP32) በሊቀመንበርነት እንድታስተናግድ ስለመመረጧ ለዲፕሎማቶቹ ሰፊ መረጃ ሰጥተዋል፡፡
በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተም የህወኃት አክራሪ ቡድኖች የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በመጣስ የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር በሕገ-ወጥ መንገድ ማፍረሳቸውን አምባሳደሩ አስታውቀዋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የውጭ ተዋናዮች እጅ እንዳለበትና ሁኔታውን እያባባሱት እንደሚገኘ የጠቀሱት ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ጀማል ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተለይም የአፍሪካ አገራት ይህንን ድርጊት እንዲያወግዙና ኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓትን ለማስፈን ለምትከተለው ቁርጠኝነት ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ገለጻውን ተከትሎ ሃሳብ አስተያየታቸውን የሰጡት የአፍሪካ አምባሳደሮች ኢትዮጵያ ስኬታማና ሰላማዊ ብሔራዊ ምርጫ በማካሄዷ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በተጨማሪም አምባሳደሮቹ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ ትልቁን ዘመናዊ ኤርፖርት እየገነባች መሆኑን እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን የኮፕ32 የአየር ንብረት ጉባኤን ለማዘጋጀት መመረጧን አድንቀዋል፡፡
እነዚህ ግዙፍ ፕሮጄክቶች የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆኑ የመላው አፍሪካ ኩራትና ሀብት መሆናቸውን የገለጹት አምባሳደሮቹ፣ ለፕሮጄክቶቹ ስኬታማነትና ፍጻሜ ማግኘት ከአገሪቱ ጎን በመቆም በጋራ ለመሥራት ሙሉ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
17/06/2026
በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነበሩ ዜጎች ወደ አገራቸው የሚገቡበት የጉዞ ሰነድ ተሰጠ
--------
በዮርዳኖው ውስጥ በስራ ላይ የነበሩ እና በሥራ ሂደት ባጋጠማቸው ችግር ምክንያት ሰነድ አልባ ለነበሩ 18 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ወደ አገራቸው መግባት የሚያስችላቸውን የጉዞ ሰነድ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
ይህ የሆነው ከአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወደ ዮርዳኖስ የተጓዘው የባልደረቦች ልዑክ ከዮርዳኖስ Department of Border Control መ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በአማን ከተማ ውስጥ በሚገኘው Al Juweidah Women’s Correctional Center ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙ 57 ታሳሪዎችንም ጎብኝቷል፡፡
የልዑካን ቡድኑ ከአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ጋር በነበረው ውይይት ዜጎቻችን ለስራ ወደ ሌሎች አገራት ሲወጡ ህጋዊ መንገድን እንዲከተሉ፣ ለሚኖሩበት አገር ህግ ተገዢ በመሆን ህግና ሥርዓትን ብሎም የአገሩን ባህል አክብሮ መስራት እንደሚኖርባቸው፣ ይህንንም በእነሱ ላይ የደረሰ ችግር በሌሎች እህቶቻቸው ላይ እንዳይደርስ ለቤተሰቦቻቸው እና በውጭ አገራት ሥራ መሰማራት ለሚፈልጉ እህቶቻቸው ማሳወቅ እንዳለባቸው ምክር ተሰጥቷቸዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያችን ትኩረት በሰጠው የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አቅጣጫ መሠረት የዜጎቻችን መብት እና ጥቅም ለማስከበር የአቡዳቢ ኤምባሲ በየሦስት ወሩ ባለሙያዎች በማሰማራት ይህንን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
11/06/2026
ማስታወቂያ!
ስማችሁ ከታች የተዘረዘረው ዜጎቻችን ፓስፖርታችሁ ታድሶ የመጣ ስለሆነ በመደበኛ የስራ ሰዓት (8:30 AM-3:30 PM) የቀድሞውን ፓስፖርትና የክፍያ ደረሰኝ በመያዝ (የፓስፖርት ባለቤቱ ብቻ) በኤምባሲያችን ቀርባችሁ የታደሰውን ፓስፖርት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን።
Beeksisa!
Lammiilee keenya Maqaan keessan kan armaan gaditti ibsame/tarraa'e Paaspoortin keessan waan isinii dhufee jiruuf guyyaalee hojiin itti kennamu Wiixataa hamma Jimaataatti sa'aatii (8:30 AM (waaree Dura)-3:30 PM (Waaree Booda) tti Imbaassitti argamuun nagahee paaspoort keessan ittiin haaromfattan harkatti qabachuun paaspoorti keessan isinii dhufee jiru fudhachuu akka dandeessan kabajaaan isin beeksifna.
06/06/2026
Ethiopian Embassy Delegation Holds Discussions with Amman Chamber of Commerce
--------------------------------------
A delegation from the Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in Abu Dhabi held constructive discussions with the leadership of the Amman Chamber of Commerce.
The Ethiopian delegation engaged with Mr. Nabil Al Khatib, President of the Amman Chamber of Commerce, and senior officials. The meeting aimed at exploring practical ways to enhance trade and investment relations between Ethiopia and Jordan.
During the discussions, both sides emphasized the importance of establishing institutional links between the Amman Chamber of Commerce and its Ethiopian counterpart. They agreed to work toward organizing business delegations and proposed the creation of a Joint Businessmen Council to facilitate closer private sector engagement.
The Ethiopian side presented an overview of the country’s ongoing economic reforms, investment incentives, and vast opportunities in agriculture, agro-processing, manufacturing, and tourism. Current bilateral trade was also reviewed, noting that Ethiopia exports sesame, coffee, and chickpeas to Jordan, while importing chemicals and fertilizers.
In addition to trade and investment, both parties acknowledged the deep historical and cultural ties between Ethiopia and Jordan and expressed optimism about expanding cooperation in the tourism sector.
The meeting concluded with a mutual understanding to follow up on the proposed initiatives and translate discussions into concrete partnerships.
05/06/2026
Press Statement on Current Issues