Aysaqiti Daqarak Qafiyat K/buxa Aysaita Woreda Health Office

Aysaqiti Daqarak Qafiyat K/buxa Aysaita Woreda Health Office

Partager

only community service

Photos from Afar Regional Health Bureau's post 22/05/2026
Photos from Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service - EPSS's post 22/05/2026
Photos from Ministry of Health,Ethiopia's post 16/05/2026
Photos from Ethiopian Health Insurance Service's post 16/05/2026
14/05/2026

ከ69 ሚሊየን በላይ ዜጎች የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል
++++++++++++++
| በመላ ሀገሪቱ ከ69 ሚሊየን በላይ ዜጎች የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ስብስባ የጤና ሚኒስቴርን የእቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እንደተናገሩት፣ የጤና መድህን ሥርዓት በርካታ ዜጎችን ያቀፈና የአገልግሎቱ ፈላጊዎች ቁጥርም ዕድገት የታየበት ነው። ለዚህም የግብዓት ዕጥረት እንዳይፈጥር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ከሚያስፈልገው የመድኃኒት አቅርቦት 70 በመቶ የሚሆነውን በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በኩል ለማሟላት እየተሠራ ሲሆን ቀሪው በመንግሥትና በግል አጋርነት የሚሸፈን ይሆናል ብለዋል።

በ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄና ለሀገር ውስጥ አምራቾች በተሰጠው ድጋፍ፣ የሀገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦት ድርሻም 46 በመቶ መድረሱ አመላክተዋል።

ጠንካራ የጤና ፋይናንስ ሥርዓት በመዘርጋትና አሠራሮችን በማዘመን ለዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝም ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባለት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ በመላው ሀገሪቱ 69 ሚሊየን ዜጎች የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በክብረአብ በላቸው

#ጤናመድህን #የተቋማትግንባታ #ሆስፒታል

Vous voulez que votre entreprise soit Service Du Gouvernement la plus cotée à Democratic Republic of the ?

Cliquez ici pour réclamer votre Listage Commercial.

Site Web

Adresse


Democratic Republic Of The