OBN አማርኛ

OBN አማርኛ

Share

Oromia Broadcasting Network (OBN)
Voice of the People!

OBN አማርኛ page is a part of Oromia Broadcasting Network (OBN), producing news, documentary and programs in Amharic language to reach our audiences in all over the world. Join us:
www.obnoromia.com
www.youtube.com/OBNoromiyaa
www.twitter.com/OBNoromiyaa
www.facebook.com/OBNAfaanoromo
www.facebook.com/OBNEnglish

Photos from OBN አማርኛ's post 01/06/2026

በሰርጋቸው እለት ድምጽ የሰጡ ሙሽሮች

ሙሽሮቹ በሆሳዕና ከተማ በሌሞ 01 የምርጫ ክልል በሄጦ ቀበሌ መስኪድ ሰፈር ምርጫ ጣቢያ 07 በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

ሙሽራ ሰላሙ ዳንኤል እንደገለጸው የሰርጋቸው እለትና የምርጫው ቀን በመገጣጠሙ አጋጣሚውን ተጠቅመው ድምጽ ሰጥተዋል።
በሰርጋችን እለት በርካታ ፕሮግራሞች ቢኖሩብንም ምርጫው የእኛንም ሆነ የሀገራችንን የቀጣይ እጣ ፈንታ የሚወሰንበት በመሆኑ ድምጻችን ሰጥተናል ብሏል።

እለቱ የሰርጋችን ቀን ቢሆንም ኢትዮጵያን ማስቀደም ስላለብን ድምጻችንን ሰጥተናል ያለው ሙሽራው ለኢትዮጵያም ሆነ ለእኛ ይበጃል ያልነውን መርጠናል ሲል አክሏል።
የሚሰጡት ድምጽ የእነሱንም ሆነ የሀገሪቱን የቀጣይ እጣ ፈንታ የተሻለ ከማድረግ አኳያ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት የደስታ ፕሮግራማቸውን አቋርጠው ድምፃቸውን ለመስጠት በምርጫ ጣቢያው መገኘታቸውን ተናግሯል።
ሙሽሪት ብሩክ ገብሬ በበኩሏ የሰርግ ቀናቸው ከምርጫ ቀኑ ጋር በመገጣጠሙ በምርጫው ድምፅ በመስጠት አሻራቸውን ለማኖር ወስነው እንደነበር አስታውሳለች።

የድምፅ መስጫው ቀን ከሰርጋቸው ቀን ጋር አንድ በመሆኑ የተለየ ደስታ እንደፈጠረባት ተናግራለች።
በምርጫው በመሳተፍ ይሆነኛል ለምትለው ፓርቲ ድምጿን መስጠት በመቻሏ ከራሷ አልፎ የሀገሯን እጣ ፈንታ እንድትወስን እድል የፈጠረላት በመሆኑ ድርብ ደስታን እንደፈጠረላትም ገልፃለች።

01/06/2026
Photos from OBN አማርኛ's post 01/06/2026

ምርጫው በዲሞክራሲያዊ መንገድ እየተመረጠ ነው-ተፎካካሪ ፓርቲዎች

ኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ ግንቦት 24 /2018

የምርጫውን ሂደት ከማለዳ ጀምሮ እየተከታተሉ እንደሆነ የተናገሩት በሞያሌ ምርጫ ክልል እየተወዳደሩ ያሉት የኢዜማ እና የኦነግ ፓርቲ ተወካዮች፣ ምርጫው ሞክራሲያዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሃገርን ለማስተዳደር የህዝብ ድምጽ ወሳኝ ስለሆነ ህዝብ የሰጣቸውን ድምጽ በጸገባ መንገድ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
በቦሩ ኮንሶ

Photos from OBN አማርኛ's post 01/06/2026

Handri 7L Faac'o Haniye Shin Teshts Faac'wotsiye Shengk,Faac'i Am amonuwe aaydek' Dimokrasiyawiy B'woto Asosi Kiti K'oshk'osh Jiiri Kayotsnat Benishangul Gumuz Guuron Nokoreyruw Partiyots Shaaniyrno.

Asosi Kiti K'oshk'osh Jiiri Kayotsnat Nokoreyruw Partiyotsuwe Booettsok'on Unotse Faac'i Asfes'amoyots Gelelteny wotonat Jeeno B'beyo Faac'i Am amo Shengk B'wotituwok'o B'woshono keewrno.

Guuron Terwerets K'ar Imonuwe Andish Bbodfetso Ik Kic'alo Amoka Bfa'o.

Muluk'en Zalk'i Asosi Kitona

Photos from OBN አማርኛ's post 01/06/2026

''የዘንድሮው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች የተለየና ሂደቱም ዲሞክራሲያዊ ነው'' -የአሶሳ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች

ኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ ግንቦት 24/2018

የአሶሳ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች እንዳሉት የምርጫ አስፈጻሚዎች ገለልተኝነት እና የጸጥታው ሁኔታ ሰላማዊ መሆን ለሂደቱ ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።

በጥዋቱ የተጀመረው የድምፅ መሰጠት ሂደትም እንደቀጠለ ነወ።
ሙሉቀን ዘለቀ ከአሶሳ

01/06/2026

ምርጫ የስልጣኔ መገለጫ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ካርዱን በአግባቡ ሊጠቀም ይገባል - የአብን የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ከድር ይመር

ኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ ግንቦት 24 /2018

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ከድር ይመር ምርጫ የስልጣኔ መገለጫ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ካርዱን በአግባቡ አንዲጠቀም ጥሪ አቅረቡ።

በደሴ ከተማ በተወከሉበት የምርጫ ክልል ድምጽ የሰጡት አቶ ከድር፤ የምርጫው ሂደት ፍፁም ሰላማዊ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ኅብረተሰቡ ይበጀናል ያለውን በካርዱ እየመረጠ እንደሆነም አብራርተዋል።

የምርጫ ሂደቱ መልካም መሆኑን ያነሱት እጩ ተወዳዳሪው ምርጫ የስልጣኔ መገለጫ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ካርዱን በአግባቡ አንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል።

01/06/2026

የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም እንግልት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው - ከነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ

ኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ ግንቦት 24 /2018

የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም እንግልት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው ሲሉ የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ተወዳዳሪ አቶ መሀመድ አሊ ገለጹ።
አቶ ሀመድ አሊ በድሬዳዋ በ06 ወረዳ ድምፅ ሰጥተዋል።
የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም እንግልት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከምርጫው ፍጻሜ በኋላም ቢሆን ለሀገር እድገት፣ ሰላምና ዘላቂ ግንባታ በጋራ እና በትብብር መስራት እንደሚገባም ተወዳዳሪው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Adama?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Bole
Adama
2919