Miki book store

Miki book store

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Miki book store, Library, Adama.

27/10/2023

"አትተኩሱ። ቼ ጉቬራ ነኝ። ከመሞቴ በላይ ቆሜ እጠቅማችኋለሁ። "

. . . . . ሰኔ 14፣1928(እ.ኤ.አ) በአርጀንቲና ተወለደ። ወላጆቹ ያወጡለት ስም ኸርኔስቶ ጉቬራ ነው። የወደዱት ኩባዎች ግን ስሙ መሃል ብለው ጨመሩለት። ማለት የእኛ ማለት ነው። ቼ ጉቬራ ለብዙዎች ጀግና ለሌሎች ደግሞ የክፉ ምሳሌ ነው። የብዙ ወጣቶች ጣኦት፣ የብዙ አብዮተኞች መንገድ - ቼ ጉቬራ!



ቤተሰቦቹ በሃብት የናጠጡ ባይሆንም ያላቸው የሚባሉ አይነት ናቸው። ቼ ግና በማለዳው ጭቁን ማህበረሰብ፣ ተበዝባዢ ሰርቶ አደር ወደሚለው የግራ ዘመም ርዕዮተ ዓለም አጋደለ።
በ1948(እ.ኤ.አ) ወደ ቦነስ አይረስ ዩኒቨርስቲ ገብቶ በህክምና ት/ት ዶክትሯል። ከዳር እስከ ዳር ድህነትን እስኪበቃው አይቷል። እንዲህም አለ፦
ዶክተር ቼ ጉቫራ ተብሏል። ቼ ግን ብዙም ሳይሰነብት የዱክትርና ስራውን ትቶ ፣ መርፌውንአስቀምጦ፣ ልቡ ላይ ያበበውን አብዮተኝነት አቅፎ ወደ ኩባ አቀና። ዶክተሩ አብዮተኛ ሆነ።
ካስትሮ የባስቲታን መንግስት ሲታገል፣ ቼ እኔም አለሁበት ብሎ ገባ። ዓለም ሁሉ ዜጋዬ፣ ጭቁን ሁሉ ወገኔ ብሎ ከኩባዊያኑ ጋር ተሰልፏል። ጠዋት ሲተኩስ ውሎ ከሰዓት በህክምና ሞያው በጦርነቱ ለተጎዱት ደርሷል።



በዚህም በ1956(እ.ኤ.አ) የባስቲታን መንግስት በቂጡ ቁጭ አደረጉት።
ቼ በዓለም ላይ ያሉ ጭቁኖችን ያፈነፍን ነበር። ኮንጎም ደርሷል፣ ቦሊቪያም አቅንቷል፣ ለጭቁኖች ዘብ ቁሟል። ነፍጥን አንግቦ ለነፍጠኛም ወኔ ሆኗል።
ቼ 1966(እ.ኤ.አ) ወደ ቦሊቪያ ሲያቀና በቦሊቪያ ያለው መንግስት ጨቋኝ መሆኑን ተረድቷል። ከስልጣን መውረድ አለበት፣ ሊያወርዱት የሚጥሩትም መታገዝ አለባቸው ብሎ የአብዮት ዘፈኑን ዘፈነ። በቦሊቪያም ከታጣቂዎቹ ጋር ታጠቀ። ጥያቄአችሁ ጥያቄዬ ነው አለ።
ግን በቦሊቪያ አመትም ሳይቆይ በሲ.አይ.ኤ በሚታገዙ የቦሊቪያ ወታደሮች ተያዘ። በተያዘ በቀጣዩ ቀን ተገደለ። የሰው ፍቅር ያለው፣ የጭቁኖች እምባ አባሽ ፣ ቼ በ39 ዓመቱ ምድር ከዳችው። ነፃነት ሞተ።



>
እንዲህም አለ፦

Want your business to be the top-listed Government Service in Adama?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Address


Adama