Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency

Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency

Share

Serving reliable cadastral services and information

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ

ራዕይ

በ2022 በከተማችን የህጋዊ ካዳስተርና አድራሻ ሥርዓት እውን ሆኖ ማየት፣

ተልዕኮ

በአዲስ አበባ ከተማ ወሰን ውስጥ የሚገኙ የመሬት ይዞታዎችን በሙሉ በማረጋገጥና በመመዝገብ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ በመታገዝ ህጋዊ ካዳስተር፣ የአድራሻና የተቀናጀ የመሬትና መሬት ነክ መረጃ ሥርዓት መገንባት፣

ዕሴቶች

 አገልጋይነት
 ታማኝነት
 ተጠያቂነት
 በዕውቀት መምራት
 ግልጽነትና አሳታፊነት
 የለውጥ ባለቤት መሆን
 የቡድን ሥራ ለስኬታማነት

25/06/2026

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ በሰጡት ማብራሪያ፣ የኢትዮጵያ የመሠረተ-ልማት ጉዞ ለዘመናት ከዘለቀው ሀገራዊ ትልም ተነሥቶ አሁን ላይ በትጉህና ግልጽ መርሆዎች እንዲሁም በተዋቀረ አፈጻጸም ወደሚመራ የለውጥ ዘመን ተሸጋግሯል፤ ለዚህ ስኬት ደግሞ የለውጡ መንግሥት ሀገራዊ ተስፋን ከተቋማዊ አቅም ጋር ወደሚያጣጥም፣ ይበልጥ አመቺ፣ ቅደም ተከተላዊ እና የፋይናንስ ሥነ-ሥርዓትን ወደ ተከተለ አካሄድ ቁርጠኛ ሽግግር ያደረገ ሲሆን ይህም መሠረተ ልማትን ወደ ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ እሴት እና ለትውልድ ተሻጋሪ ሀብት እንዲቀየር እያደረገው ይገኛል።

‎ የንጹሕ ኢነርጂ፣ የዲጂታል ማስፋፊያ፣ የትራንስፖርት፣ የኮንስትራክሽን እና የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ሀገሪቱ የምታደርገውን የለውጥና የብልጽግና ጉዞ እየመሩት ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ዕድገቷ ራሱን ችሎ የሚቀጥልና ለውጥ የሚያመጣበት ደረጃ ላይ ለመድረስ በትጋት እየገነባች ትገኛለች!

25/06/2026

በማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ኢንጂነር ሐና ብርሃኑ፣ በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ከነበረበት ደካማ አፈጻጸም ተነስቶ አሁን ላይ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች አንዱ መሆን የቻለበትን የማዕድን ትራንስፎርሜሽን ጉዞ አቅርበዋል።
‎ በቁርጠኛ ማሻሻያዎች፣ በገበያ መልሶ ማዋቀር እና እሴትን መጨመር በሚያስችሉ ኢንቨስትመንቶች በመታገዝ ዘርፉ ከፍተኛ የወጪ ንግድ ገቢን እያስገኘ፣ የገቢ ምርቶችን ጥገኝነት እየቀነሰ እና ለኢንዱስትሪ ልማት አዳዲስ ዕድሎችን እየፈጠረ እንደሚገኝ ኢንጂነር ሐና አመላክተዋል።

‎በወርቅ፣ በወሳኝ ማዕድናት፣ በነዳጅ እና በማዳበሪያ ምርት ላይ እየተስፋፋ በመጣው የኢንቨስትመንት ለውጦች፣ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት አቅም ወደ ተጨባጭ ብሔራዊ ዕድገት እየቀየረችው ትገኛለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ እነዚህ ስኬቶችም በሀገር በቀል ቅኝት የሪፎርም ማሻሻያ፣ በገዘፈ ርዕይ እና አፈጻጸም ድምር ውጤት እንደሚያስገኙ ህያው ማረጋገጫዎች ናቸው።

25/06/2026
Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication's post 25/06/2026
Photos from Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency's post 24/06/2026

በዛሬው ዕለት የባለጉዳይ ቀንን በማስመልከት የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ከፍተኛ አመራሮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ጥላሁንን ጨምሮ የሚመለከታቸው የዘርፍ ዳይሬክተሮች በተገኙበት ባለጉዳዮች ጉዳያቸውን በማቅረብ እየተስተናገዱ ይገኛሉ።

የተለያየ ኬዝ ያላቸው ባለጉዳዮች፤ ጉዳያቸው ለሚመለከተው ዘርፍ ወይም አካል በመመራት መፍትሄ እየተሰጠም ይገኛል።

ሰኔ 17/2018 ዓ.ም
(የመ/ይ/ም/መ/ኤ) AA-LHRIA
አዲስ አበባ

ለበለጠ መረጃ 👇👇👇
👉Website; https://addiscadaster.gov.et/
👉Facebook; Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information
👉TikTok; A.Acadaster2016
👉Telegram; https://t.me/lhria
👉you tube; Legal cadaster
👉Customer Call Center: 6577

Photos from Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency's post 23/06/2026

የአሰራር ጥራት ቁጥጥር እና ኦዲት ዳይሬክቶሬት የአመት ስራውን ገመገመ
----------------------------------------------
ሰኔ 16/2018 ዓ.ም
(የመ/ይ/ም/መ/ኤ) AA-LHRIA
አዲስ አበባ

የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የአሰራር ጥራት ቁጥጥር እና ኦዲት ዳይሬክቶሬት ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዘርፉ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ጋር የ2018 በጀት አመት አፈፃፀሙን ገምግሟል፡፡

በመድረኩ ማሳያ የሚሆን የክ/ከተሞች አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን አጠቃላይ የ2018 በጀት አመት የመሬት ይዞታ የአሰራር ጥራት ቁጥጥርና ኦዲት ዳይሬክቶሬት ሪፖርትን የዘርፉ ዳይሬክተር አቶ ኡርጌቻ ከፈኒ አቅርበዋል፡፡ አቶ ኡርጌቻ እንደገለጹት ዳይሬክቶሬቱ በተቀመጠ ህግ፣አሰራርና ስታንዳርድ መሰረት ቁጥጥርና ኦዲት ማድረጉን አስታውቀው በዚህ በጀት አመት በአዲስ ምዝገባ 5,138 ፋይሎችን ማጣራት ታቅዶ 5,796 ያህል ፋይሎችን ማየት መቻሉን፣ በኮንዶሞኒየምና ሪልስቴት ማረጋገጥ 16,574 ያህል ፋይሎችን ማጣራት ታቅዶ 17,534 ፋይሎች ላይ ቁጥጥር መደረጉን እንዲሁም በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ 34,000 ቁጥጥር ለማድረግ ታቅዶ 30,600 ላይ መደረጉንና በአሰራር ጥራት ኦዲት 4,524 ታቅዶ 4,501 መከናወኑን ገልጸዋል፡፡

በግምገማ መድረኩ አስተያየትና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በተለይም ወጥ የሆነ አሰራር በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶ ያለመኖር፣ ተመሳሳይ ቅፃችን ከመጠቀም አንፃር ጉድለቶች መኖራቸው፣ የእቅድና ሪፖርት ተናባቢነት ችግር፣ እቅድ ሲታቀድ የክ/ከተሞችን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ መሆኑ እንደ ችግር ተነስተዋል፡፡

አቶ ኡርጌቻ በማጠቃለያቸው እንዳነሱት የተነሱ ችግሮችን ለመፍታት የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ የተቋሙን ራዕይ ከሌሎች ዘርፎች ጋር በመሆን ለማሳካት የዘርፉ አመራሮች እና ባለሙያዎች በትጋት መስራት እንደሚጠበቅ ጠቅሰዋል፡፡

ዳይሬክቶሬቱም ባካሄደው የቁጥጥርና ኦዲት ስራ ሊፈጠሩ የሚችሉ ስህተቶችን በህግና መመሪያ መሰረት በማስተካከል ለተቋሙም ለህብረተሰቡም አገልግሎቱን እየሰጠ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ 👇👇👇
👉Website; https://addiscadaster.gov.et/
👉Facebook; Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information
👉TikTok; A.Acadaster2016
👉Telegram; https://t.me/lhria
👉you tube; Legal cadaster
👉Customer Call Center: 6577

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


604 Equatorial Guiene Avenue
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30