ሀገር ለመገንባት ጥላቻን እናፍርስ፤
ሀገር ለመገንባት የበለይነትን እናፍርስ፤
ሀገር ለመገንበት የበታችነትን እነፍርስ ፤
ሀገር ለመገንባት ኢ-ፍትሃዊነትን እናፍርስ፤
እኩልነት፤ ሰባዓዊነት፤ ፍትሃዊነት፤ እናሰፈን፤
ታታርነትን፣ አብሮነትን፣ መልካምነትን እናጎልብት፤
ይህ ከላይ የተመለከተዉ ሀሳብ ሁላችን ላይመለከት ይችላል ነገር ግን አንዳንዶቻችን ይመለክተናል። ኢትዮጵያ ሀገራችን 3000 ዓመት ታርክ ያላት ሀገር ሆና ሳለች በቅርቡ የሠዉ ልጆች መኖር የጀመረባቸዉ እኔ አሜርካ ከአሁን በኃላ 200 ዓመታት ቀንና ለልት ብንሰራ እንኳ ከዛሬ መቶ አመት በፍት አሜርካዊያን የደረሱበት የተክኖሎጅ እና ረቂቅ የሆኑ ሁለንቴናዊ ለዉጥ የመንደርስ የሆነንበት ምክንያት እኛ የወደፍት ህወት ላይ ከማጠንከር በላይ የኋላ አባቶቻችን አጽም እና ተጋድሏቸዉ ብቻስናተኩር ነዉ። ምን ለማለት ነዉ እገለ የምባል ንጉስ ፣ ቀኝ አዝማች፣ፍታዉራር ወዜቴ የኔ ዘር ነዉ የኔ ጎሳ ነዉ እያለን ፤ እኛ የበላይ ነን እያለን፤ ለሎቹን እያንኳሰሰን፤ ሁሉንም ነገሮች በትዉዉቅ፣ ዝምድናና ቅርርብ አንጻር እያየን፤ ለዉጥ በምያመጡ እሳቤዎች ላይ ከማተኮር old model አሰራርን ይዘን እየተጓዘን ከአለም መጨረሻ አገራት በመጨረሻ ተሰልፈናል
👉 ፖለትከኞች ጥሩ ስትራተጂ እና ፖሊሲ በወረቀት ላይ እናስቀምጥና በተግባር ለይ አናሳይም፤
👉 ባለሀብቶች ገንዘብ የምያሰገኝ ይሁን አንጅ ብለን ከማንም ጋር በመመሰጠር ለኔ ከምል አሰተሳሰብ አልተላቀቀንም፤
👉 ምሁራን(ሁሉ አይደለም) ለዉጥ እንድመጣ አድምተን አንታገልም፤ ጥርሶቻችን አሳይተን ቢሮ ገብተን 20 እና 30 ደቅቃ ቆይተን ከቢሮ እንደወጣን በጀበና ቡና ቤት ኃላፍዎቻችን እያማን ፤ የቅናትና ተንኮል አጃንዳ ስክረፕት እያዘጋጀን ፤ የዘር የጎሳ፣ የኃይማኖት፤ የስልጣን አጃንዳዎች ላይ አሉታዊ የሆኑ ነገሮችን እያሰራጨን እንዉላለን።በተለይ ቅንዓት ከፍተኛ ሰፍራ ይዟል ተምረናል ከምንል አካለት።
እሲቲ አስቡ አንቴ በተማርክበት በሠለጥንክበት ሙያ መተቀጠርክበት ቢሮ ተግተህ ብትሰራ፤ እኔም እንደዚሁ ብሰራ ለሎችም በተማኝነት በሀቀኝነት ጊዜ የለንም መንፈስ ብንሰራ ለሀገራችን ለዉጥ አይመጣም?
ለላዉ ከምሁራን ነን ከምንል ከኛ መንደር የምመነጭ አደገኛ እንክርዳዳ ሀሳብ አንድ ነገር ኩሽ ባለ ቁጥር ወደ ጎሳ መግባት ወይ ሆን ብለን ግጭት ለማሰነሰት መስራት ።ለምሳሌ ኦነግ የኦሮሞ አርሶ አደሮች ፍላጎት የተመሠረተ ፓሪቲ ነዉ? ግን የኦሮሞ አርሶ አደሮች በብዙ ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ፤ ፋኖስ? የአማሐራ አርሶ አደሮች የፈጠሩት ቡድን ነዉን? አይደለም!! ምሁራን ነን ፤ ወጣቶች ነን ለዉጥ ኃይል ነን ብለን የዋቀረነዉ ነዉ ግን ምን ያደርጋል ሠፊዉ የአማሐራ አርሶ አደሮች ከሕወት ጀምሮ ብዙ ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ። ህወአት ብንወስድ ራሳቸዉ ብቻ ትክክል ለላዉ መለአክ ብሆንም ትክክል እንዳልሆነ ይቆጥራሉ በዚህም ሀገራችን አትዮጵያ ልጆች ወንድም ከወንድም ጋር እት ከእህት ጋር እንድቷከሱ አድርገዋል ለዝህም ደግም ደግና የዋህ የትግራይ እናቶች አባቶች ጭንቅለት ዉሥጥ አሉታዊ ነገርን በማስረጽ ድጋፍ አግኝተናል በማለት ሁሉንም ነገር አዉድመዉበናል።
ይህ ሁሉ ትንተና ዉስጥ ለምን ገባሁ? ለምንስ እንደዚህ አይነት ሀሳብ ረበሸኝ? ምክንያቱም እጅግ ወደኋላ ቀርተናል በሁሉም ነገር!! በተግባር አስተሳሰብ አንድነት መቻቻል ፈቅር ስራ ጥረት ቅንጅት አስተዳደር ሁሉም ነገራችን ኋላ ቀሪ ነዉ።
ታድያ እንደት እንዘምን? አንድነታችንን መከባበርን እንጨምር የሥራ ባህላችንን እንቀይር ።
ደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል/south Ethio peopls' region_Follow
Polatical party
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Website
Address
A. A
Addis Ababa
