13/06/2026
Addis Ababa ITDB - Innovation and Technology Development Bureau
This is the Official page of
Addis Ababa City Innovation and Technology Development Bureau!
13/06/2026
12/06/2026
12/06/2026
የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ስማርት አዲስ አበባን በመፍጠር እመርታዊ ውጤት እያስገኘ ነው
አዲስ አበባ፤ሰኔ 4/2018 (ኢዜአ)፦የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ስማርት አዲስ አበባን በመገንባት እመርታዊ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ገለጸ።
በአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አስተባባሪነት ችግር ፈቺ አሰራሮችን በነፃ በማልማት የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት እንዲጠቀሙ ያደረጉ የግል ተቋማትና ባለሙያዎች የእውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ የተደረገው የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂም በስማርት ሲቲ ትግበራ አዲስ አበባን በመገንባት እመርታዊ ውጤት እያስገኘ መሆኑ ተገልጿል።
ለዝርዝሩ 👉 https://www.ena.et/web/amh/w/amh_9015865
11/06/2026
የእውቅናና ሽልማት መርሀ-ግብር ተካሄደ
*****************************
ITDB፦ ሰኔ 4/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አስተባባሪነት የከተማ አስተዳደሩን ችግር የሚቀርፉ የተለያዩ ሲስተሞች በማልማትና የፈጠራ ስራ በመስራት ለከተማ አስተዳደሩ በነፃ በማበርከት ተቋማት እንዲጠቀሙበት የሚያደርጉ ባለሙያዎችና የግል ተቋማት የእውቅናና ሽልማት መርሀ-ግብር ተካሄደ፡፡
የመር-ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈው ተቋማቱ በፍቃደኝነት ከቢሮ ጋር በመስራታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል። አክለዉም ከተማ አስተዳደሩ እያከናወነ ያለውን በርካታ ተግባር ለመደገፍ አምስት ተቋማትና ዘጠኝ ባለሙያዎች ያለምንም ስስት የተለያዩ ሲስተም አልምተው ማበርከታቸው የሚያስመሰግን መሆኑንና የለሙት ሲሰትሞች የአሰራር ስርአትን ከማዘመን ባሻገር ለወረቀት የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ ያስቀረ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የቢሮ ስማርት ሲቲ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን ስለስማርት ሲቲ ፅንሰ-ሀሳብ እና የለሙ ሲሰትሞች ለከተማ አስተዳደሩ ስላላቸው በጎ አስተዋፅኦ ዝርዝር ማብራሪያ በመስጠት ሲስተሙን ላለሙ አካላት ዝርዝር ማብራሪያ አንዲሰጡ ጋብዘዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የመማር እና አቅም ግንባታ አስተዳደር ፣የንብረት አስተዳደር እና የንግድ ሂደት ስርአት፣ የከነማ ፋርማሲ፣ የቆጠራና ሽያጭ አስተዳደር ስርአት እና አልትራይድ አውሮፕላን በአልሚ ድርጅቶች አማካኝነት ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በመጨረሻም ይህንን በጎ ተግባር ላከናወኑ ተቋማት የእውቅናና ሽልማት የምስክር ወረቀት በመስጠት መርሀ-ግብሩ ተጠናቋል፡፡
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): [email protected]
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
11/06/2026
ውድ ኢትዮጵያውያን ለ5 ሚሊዮን ኮደሮች ምዕራፍ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ!
በሦስት ዓመታት ውስጥ ለማሳካት የታቀደውን ግብ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማሳካት ተችሏል። የ«5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች» ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ በመረጃ ትንተና፣ በአንድሮይድ ሶፍትዌር ልማት እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ ትምህርቶች 5,005,146 ሰልጣኞች ተመዝግበው ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀዋል። ይህ ስኬት የሕዝባችንን ቁርጠኝነት እና ወሰን የሌለው አቅም ማረጋገጫ ነው።
በዲጂታሉ ዓለም በልኩ ለመዘጋጀት የጀመርነው ታሪካዊ ምዕራፍ፤ የጉዟችን ማብቂያ ሳይሆን፥ ብሔራዊ ርዕያችንን ይበልጥ የምናፋጥንበት መነሻ ነው። እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም. ድረስ የሰልጣኞችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ የተሰነቀውን ግብ ለማሳካት፥ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዚህ ብሔራዊ ተልዕኮ አካል እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ለወጣት ተማሪዎቻችን፤ መጭው የክረምት ወቅት ትልቅ ዕድላችሁ ነው። ጊዜያችሁን በዋዛ ከማሳለፍ ተቆጥባችሁ፤ በመመዝገብና በመማር ወደ ትምህርት ገበታችሁ ስትመለሱ ተማሪዎች ብቻ ሳትሆኑ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላችሁ የዲጂታል መሪዎች እንድትሆኑ አሳስባለሁ። ሥልጠናዎቹ ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጡ ሲሆን፥ የምስክር ወረቀቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው ነው።
የምትገነቡት ነገ የሚጀምረው ዛሬ ነው!
ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ:
ethiocoders.et/
09/06/2026
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
