04/02/2023
ግንዛቤ
የንግድ ድርጅትዎን ከሀሰተኛ ደረሰኝ አደጋ ለመከላከል የሚያስችሉ መሰረታዊ ቁምነገሮች
1. ክፍያ በጥሬ ገንዘብ ከመክፈል ይልቅ በባንክ በኩል መፈፀም የተቀባዮቻችን ዱካ ለመከታተል ያስችላል፣
2. ደረሰኝ ሲቀበሉ ደረሰኙ ላይ ያለውን መረጃ ሻጩ ሻጩ ከለጠፈው የንግድ ስምና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ጋር ያመሳክሩ በዚህም መረጃው የተለያየ ከሆነ ከህገወጥ ድርጅት ጋር ግብይት እየፈፀሙ ነውና ግብይቱን ያቋርፁት፣
3. ዕቃ ወይም አገልግሎት የሸጠልዎት ድርጅት አድራሻ ማወቅ አለብዎት የሻጩን አድራሻ ማወቅ ድርጅቱ ህገዋጥ ሆኖ ሲገኝ በህግ ለመጠየቅ ያግዝዎታል፣
4. ለድርጅትዎ ባለሙያዎች ስለታክስ ግዴታዎች ማስገንዘብ እና ማሳወቅ በግብይት ወቅት አስፈላጊው ጥንቃቄ ለማድረግ ያስችላል፣
5. ስራ አስኪያጆች/ያድርጅት ባለቤቶችየድርጅታቸውን የፋይናንስ እንቅስቃሴ በቅርበት መከታተል አለባቸው በድርጅቱ ባለሙያዎች ህገወጥ ድርጊት ለፈፀም ስለሚችል የድርጅትዎን የፋይናንስ እቅስቃሴ በቅርበት መከታተል አለብዎት፣
6. የድርጅትዎን አሰራር በቴክኖሎጅ የተደገፈ ማድረግ አሰራርን ማዘመን ለህገወጥ ሥራ በር ይሚከፍቱ አሰራሮችንለማስቀረት ይረዳል፣
7. በግብይት ወቅት የድለላ ጣልቃ ገብነት መቀነስ ግብይት ያለሦስተኛ ወገን ጣልቃገብነት መፈፀም ስለሻጩ ማንነት ለማወቅ ያስችላል፣
8. ሻጩ ድርጅት የተሰማራበት የንግድ ዘርፍ እርስዎ የሚገዙት እቃ/አገልግሎት ማቅረብ የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ በድርጅቶች በድርጅቶች የሚቀርቡ ደረሰኞች ተቀባይነት የሚኖራቸው የተሰማበት የንግድ ዘርፍ ዕቃው/አገልግሎቱ እንዲሸጡ የተፈቀደላቸው ሲሆን ነው ለምሳሌ ስሚንቶ ሻጭ ልብስ ሸጫለሁ ብሎ ደረሰኝ ቢቆርጥ ተቀባይነት የለውም፣
9. አጠራጣ ደረሰኝ ሲያጋጥምዎት በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ የገቢዎች ቅርንጫፍ በመሄድ ስለድርጅቱ ትክክለኛነት ያረጋግጡ ሀሰተኛ ደረሰኝ የሚያሰራጩ ህገወጦች በመኖራቸው ግብይት በሚፈጽሙበት ወቅት አጠራጣ ነገር ሲያጋጥምዎት ክፍያ ከመፈፀምዎ አስቀድመው የገቢዎች ባሙያዎችን ያማክሩ፣
04/02/2023
ማስታወቂያ
ለመርካቶ ቁ1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተጨማሪ ዕሴት እና የተርን ኦቨር ታክስ ለምታሳውቁ ግብር ከፋዮች በሙሉ
የተጨማሪ ዕሴት ታክስ እና የተርን ኦቨር ታክስ የማሳወቂያ እና የመክፈያ ጊዜ ከጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም – 30 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም በወሩ መጨረሻ አካባቢ ሊፈጠር የሚችለውን መጨናነቅ መቀነስ እንዲያስችል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቅርንጫፍ ጽ/ ቤት በአካል በመቅረብ እንድታሳውቁ እናሳስባለን፡፡
ግብርዎን በታማኝት፣ በፈቃደኝነት እና በወቅቱ ስለሚያሳውቁ እናመሰግናለን!
የመርካቶ ቁ1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
06/01/2023
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁ1 መ/ግ/ከ/ቅ/ጽ / ቤት አንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ ፡፡ በዓሉ የሰላም፣ የደስታ ፣የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆንልን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከወዲሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡
05/01/2023
ከሽያጭ ታክስ/ Turn over tax/ ክፍያ ነፃ ግብይቶች
• ቢያንስ ሁለት ዓመት ያገለገለ የመኖርያ ቤት ሽያጭ እና የመኖርያ ቤት ኪራይ
• የፋይናንስ አገልግሎቶች
• ለሳንቲሞችና መዳልያዎች ጥናት አገልግሎት ከሚውሉት በስተቀር የአገር ውስጥና የውጭ አገር ገንዘቦች እና የዋስትና ሰነዶች ማሰራጨት
• በሃይማኖት ድርጅቶች የሚሰጡ የእምነት ወይም ከአምልኮ ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች
• የሕክምና አገልግሎቶች እና አግባብ ባለው የመንግስት መሥርያ ቤት በሚወጣ መመርያ መሠረት ነፃ የተደረጉ አገልግሎቶች
• በትምህርት ተቁዋማት የሚሰጡ የማስተማር አገልግሎቶች እንዲሁም ለሕፃናት ጥበቃ በመዋእለ ሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶች
• ለሰብአዊ ዕርዳታ የሚውሉ ዕቃዎችና አገልግሎቶች፣ የኤሌክትሪክ፤የኬሮሲን እና የውሃ አቅርቦት፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶች
• ማንኛውም የስራ እንቅስቃሴ ለማከናወን ለሚስጥ ፈቃድ ለመንግስት የሚሰጥ ክፍያ
• ከ60% በላይ ሠራተኞቹ አካል ጉዳተኞች የሆኑበት አካል ጉዳተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ድርጅት የሚቀርባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች
• መፃሕፍት( ወደ ሀገር የሚገቡ፣ በሀገር ውስጥ የሚሸጡ እና መጻህፍትን ወቅታዊ ለማድረግ የሚወጡ እትሞች )
• የምግብ እህል (ጤፍ፤ ስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ዘንጋዳ ፣ዳጉሳ ፣ አጃ፣ እንዲሁም የነዚህ ዱቄት ከጥራጥሬ አተር ፣ባቄላ፣ምስር ፣አኩሪ አተር፣ሽንብራ ፣ግብጦ ፣ጓያ )
• የቅባት እህሎችም ሆኑ ፕሮሰስ የተደረጉ ምግቦች፣ ፉርሽካም ጭምር የታክስ መነሳት አይመለከታቸውም ፡፡
02/01/2023
ያለ ገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች
🔹 ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፤
🔹 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወይም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቦርድ አባል ወይም ፀሐፊ እንዲሁም የፌደራልና የክልል መንግሥታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡድኖች አባል ወይም ፀሐፊ በመሆን የሚከፈል አበል፤
🔹 ለሠራተኛው ጥቅም ተብሎ ከተቀጣሪው የወር ደመውዝ 15% (አሥራ አምስት በመቶ) ባልበለጠ መጠን በየወሩ በቀጣሪው የሚዋጣ የጡረታ መዋጮ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ፤
🔹 በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እና በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ከግብር ነፃ የተደረገ የጡረታ ገቢ፤
🔹 የኢትዮጵያ የፌደራል፣ የክልል ወይም የአካባቢ መንግሥታት ወይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛ ሥራዎቻቸው ጋር በተያያዘ የሚያገኙት ገቢ፤
🔹 በዓለም ዐቀፍ ስምምነት መሠረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን፤
🔹 በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በተደረገ ስምምነት መሠረት ማናቸውም ገቢ ከግብር ነፃ የሚሆነው፡- ስምምነቱ የተደረገው ለመንግሥት የገንዘብ፣ የቴክኒክ፣ ሰብአዊ ወይም አስተዳደራዊ እርዳታ ለማቅረብ የሆነ እንደሆነ እና ከግብር ነፃ ማድረግ የሚያስችለውን አንቀጽ በሚመለከት ሚኒስትሩ መስማማቱን በጽሁፍ ሲገልጽ
🔹 በማንኛውም መስክ ለላቀ የሥራ ክንውን የሚሰጥ ሽልማት፤
☑️አንድን ቴክኖሎጅ ለማሻሻል፣ አዲስ የፈጠራ ስራ በመስራት ወይም ወጪን ለመቀነስ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ስራ ላይ በማዋል የሚሰጥ ሽልማት
☑️በአለም አቀፍ ደረጃ በሚደረግ ውድድር አገርን ወክሎ ወይም በሀገር አቀፍ ደረጃ በህግ በተቋቋመ ድርጅት በሚደረግ ማንኛውም ውድድር የሚሰጥ ሽልማት
☑️በፌደራል፣ በክልል፣ በአዲስ አበባ እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር መንግስት የላቀ የስራ ክንውን ላስመዘገበ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት የሚሰጥ ሽልማት ሲሆን ሽልማቱ ከገቢ ግብር ነጻ ሊሆን የሚችለው ከፈጠራ ስራው ጋር ግንኙነት ያለው የመንግስት አካል ለፈጠራ ስራው እውቅና የተሰጠው ወይም የፈጠራ መብት ሲኖረው ነው ፡፡
🔹 በተቀባዩ ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም በሌላ ሰው ሞት ምክንያት የሚከፈል ካሳ፤
🔹 ስጦታው የመቀጠር፣የኪራይ ወይም የንግድ ሥራ ገቢ ካልሆነ በስተቀር በስጦታ ወይም በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፤
🔹 በትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርትን በነፃ ለመከታተል የሚፈፀም ክፍያ፤
🔹 ለቀለብ ወይም ለህፃናት ድጋፍ የሚሰጡ ክፍያዎች፤
🔹ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ጋር የማይገናኝ የንግድ ሥራ ገቢን ሳይጨምር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የሚያገኘው ገቢ፤
🔹ገንዘብ በሚቆጠርበት ጊዜ ለሚደርሰው ጉድለት ማካካሻ በሚሆን መጠን ብቻ ቀጣሪው ለተቀጣሪው የሚከፍለው እና ለዚሁ ዓላማ መዋሉ የተረጋገጠ የጥሬ ገንዘብ ማካካሻ ክፍያ፤
🔹 በኢትዮጵያ ፀንቶ በሚሰራበት ሕግ መሠረት በተለይ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረገ ገቢ፤
🔹 ለመኖሪያ ቤት ሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ፤
🔹በነዳጅ ሥራ ላይ የተሰማራ ሥራ ተቋራጭ ለንዑስ ሥራ ተቋራጮች የሚፈፅመው ክፍያ፡፡
🔹ለኢኮኖሚ፣ ለአስተዳደራዊ ወይም ለማህበራዊ ምክንያቶች አንድን ገቢ ከገቢ ግብር ነፃ ሊያደርግ እንደሚችል ባመለከተው መሠረት የሚከተሉት ገቢዎች ከገቢ ግብር ነፃ ናቸው፤
☑️በወጪ ንግድ ሥራ ላይ የተሠማሩ ባለሀብቶች ለእውቀት ሽግግር ከውጭ ሀገር ለሚያስመጧቸው ባለሙያዎች ከአምስት ዓመት ላልበለጠ ጊዜ የሚከፈላቸው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ፤
☑️በማንኛውም የአስራ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ለአንድ ቀጣሪ ሳያቋርጥም ሆነ በተደጋጋሚ ከሠላሳ ቀናት ላልበለጠ ጊዜ ያገለገለ ማንኛውም ባለሙያ ያልሆነ ተቀጣሪ የሚያገኘው ገቢ፤ ሆኖም በአስራ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ አንድ ሰው በተደጋጋሚ ለአንድ ቀጣሪ የሰጠው አገልግሎት ሲደመር ከአንድ ወር የሚበልጥ ከሆነ ተቀጣሪው የሚከፍለው ግብር የሚታሰበው በመጨረሻው ቅጥር ባገኘው ገቢ ላይ ብቻ ይሆናል፡፡
☑️“ባለሙያ ያልሆነ ተቀጣሪ” ማለት መደበኛ የሙያ ሥልጠና ያልወሰደ ልዩ ሙያ በሚጠይቁ ማሽኖችና መሣሪያዎች የማይጠቀም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በጠቅላላው ከ30 ቀናት ለማይበልጥ ጊዜ የተቀጠረ ግለሰብ ነው፡፡
☑️ከግብር ነጻ የተደረገው አሠሪው ሠራተኛው ሲታመም ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ በሠራተኞች የጤና መድን አቅድ መሠረት አሠሪው ለሠራተኞች ጥቅም የሚከፍለውን አረቦን ይጨምራል፡፡
☑️ለኮንስትራሽን ማሽነሪ ኦፕሬተሮች የሚከፈለው ውሎ አበል ከ25ኪ.ሜ. ባነሰ ወይም በበለጠ ርቀት ቢሆንም የተከፈለው የውሎ አበል ከግብር ነፃ ይሆናል፤
☑️የመንግስት መስሪያ ቤት ለተሿሚዎች እና ለተቀጣሪዎች ከመደበኛ የስራ ቦታቸው ውጭ ከ 25 ኪ.ሜ. በላይ ርቀው በመሄድ ለሚያከናውኑት ሥራ የሚከፈል የቀን ውሎ አበል ሙሉ በሙሉ ከግብር ነፃ ነው
14/12/2022
የህጋዊ ደረሰኝጠቀሜታ
• በደረሰኝ አያያዝና አሰጣጥ ላይ የሚደረገው ቁጥጥር በአገራችን ካለው የአመራረት፣ የክፍፍል የስርጭትና ግብይት ሁኔታ ጋር ለማጣጣም፣
• በመሠረቱ ደረሰኝ ሊሰጥ የሚገባው በአቅራቢ ቢሆንም በጊዜው በተለየ ሁኔታ ከገዢው በኩል የወጪ ሰነድን በማረጋገጥ ቁጥጥሩ ሊፈፀም እንደሚችል ለማሳወቅ፣
• የንግዱ ሕብረተሰብ በቁጥጥር ስርዓት እንዲገዛ ማድረግ፣
• ተጠያቂነትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳዮች እንዲታወቁ ለማድረግ፣
• ተግባራዊ የሚሆነውን ቁጥጥር ሥርዓት ለመምራትና ለማስፈፀም፣
• የደረሰኝን ሕትመት ስርዓት ሳያሟሉ የትም ታትመው ገበያ ላይ የሚውሉ ደረሰኞች ህትመትና አገልግሎት ለማቋረጥ፣
• በማንኛውም ግብይት የሚሰጠው ደረሰኝ ህትመትና ስርጭቱ በታወቀና ቁጥጥር በሚደረግበት ሁኔታ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ለማድረግ፣
• በባህላዊ የማምረት ተግባር የሚተዳደሩ አቅራቢዎች የሚፈጽሙት ግብይት የሚሸፍን ስርዓት ታሳቢ ለማድረግ፣
• ደረሰኝ ህጋዊ አሰራርን የሚያመለክት እጅ በእጅ ወይም በዱቤ እቃ ወይም አገልግሎት ስለመሸጡ ለማረጋገጥ የሚረዳ ሰነድ መሆኑ፣
• ግብር ከፋዮች ለሚሰጡት የሽያጭ አገልግሎቶች ለተጠቃሚው ደረሰኝ መስጠታቸው ለሚከፍሉት ግብር ትክክለኛነት በመረጃ ምንጭነት ያገለግላል፣
• በግብር ሰብሳቢው አካልና በግብር ከፋዩ ዘንድ አለመግባባቶችን ይከላከላል፣
• ግብር ከፋዩ በግብር መክፈያ ወቅት አለአግባብ ግብር እንዳይጠይቅና ከአግባቡም በታች እንዳይከፍል ለማድረግ ይጠቅማል፣
• በሀገራችን የዕቃና የአገልግሎት ግብይት በአብዛኛው በጥሬ ገንዘብ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ የታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር ሥርዓትን መዘርጋት ከፍተኛ ጥቅም አለው፡፡