26/05/2023
የኮልፌ ቀራኒዮ እና የፉሪ ክፍለ ከተማ አስተዳደሮች በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ላይ በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የፊርማ ስነ_ ስርአት ተካሔደ፡፡
ግንቦት 18ቀን 2015 ዓ.ም
ሁለቱ ክፍለ ከተማ አስተዳደሮች በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ማለትም በከተማ ጽዳት፤ በመሰረተ ልማት እና በመሰል ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት የሁለቱም ክ/ከተሞች ዋና ስራ አስፈጻሚዎች፣ ዋና ስራ አስኪያጆች እና የሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የፊርማ ስነ ስርአት ተካሒዷል።
አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ በበኩላቸው ክፍለ ከተሞቹ አጎራባች በመሆናቸው የጋራ አገልግሎት መስጠት ስለሚገባ ሕዝቡን የሚያስተሳስር ስራ በልማት ፤በፅዳትና በሌሎች ስራዎች ላይ እንደ አስተዳደር ከእናንተ ጋር ተቀናጅትን እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የፉሪ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ወይንሸት ግዛው በተፈራረምነው ስምምነት መሰረት ያለንን አቅም በመጠቀም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ያጋራ አላማችንን ማሳካት አለብን ለዚህም በቀጣይ ዕቅዶቻችን ውስጥ አካተን በልማትና በሌሎች ዘርፎች አብረን ተባብረን አንሰራለን ያሉ ሲሆን እናንተም ይህን ተረድታችሁ እዚህ በምጣታችሁ በክፍለ ከተማው ስም አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡
አመራርነት ሁሉንም ህዝብ በእኩልበማገልገል ያሉትን ችግር በመካፈል መፍትሄ ለመስጠት ነው ያሉት አቶ አዱኛ ማሩ የሸገር ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ ዛሬ የጀመርነውን ስራ በከተማ ደረጃ ማስፋት አለብን እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማና ክፍለ ከተማዎቿ ጋር በአንድነት ለጋራ እድገት መስራት ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ አስተዳደሮቹ በጋራ በሚሰሩባቸው ተግባራት ላይ ገለጻ በማድረግ የተወያዩ ሲሆን ከመድረኩም በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ ህብረተሰቡን አስተባብረን በማሳተፍ በአንድነት ለማደግ እንሠራለን ሲሉም ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን ሰተዋል፡፡
25/05/2023
"በጎ ፈቃደኝነት ለዘላቂ አብሮነት መሰረት ነው።"
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የ2015 ዓ/ም የበጎ ፈቃድ የእውቅናና ምስጋና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መክፈቻ ፕሮግራም በክፍለከተማው ተካሄደ።
በ2015 ዓ/ም በክፍለ ከተማው ስር ካሉ 10 ወረዳዎች የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ማስተባበርያ ፅ/ቤት 2ኛ ደረጃ በመያዝ የዋንጫና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆነ ውጤቱ ለቀጣይ ስራ መነሳሳት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።
25/05/2023
"በአብሮነት የህብረተሰቡን ጤና እንጠብቃለን"። በሚል መሪ ቃል የጤና ባለሙያዎች ውይይት እያደረጉ ነው።
ግንቦት 17/2015
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ /ቤት አዘጋጅነት የጤና ባለሙያዎች፣ የፋርማሲ ባለሙያዎች እንዲሁም የግሉ ዘርፍ የጤና ተቋማት በሀገራዊ ጉዳዮች በተጨማሪም በጤናው ዘርፍ የተገኙ ስኬቶችን የሚዳስስ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።
ተወያዩቹ በ5 ዓመት የለውጥ ጊዜያትን በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና በጤናው ዘርፍ የተመዘገቡ ለውጦችን አስመልክቶ መወያየት ጀምረዋል።
ለውይይቱ መነሻ “በአብሮነት የህብረተሰብን ጤና እንጠብቃለን” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቧል።
25/05/2023
አንዲትም የኢባዱረህማን መስጂድ ህጋዊ ይዞታ እንደማይነካ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው አረጋገጡ።
የክፍለ ከተማው አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስልምና ጉዳዮች ስራ አሰፈፃሚ ኮሚቴ ጋር በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወር የነበረ በክፍለ ከተማው ወረዳ 05 የሚገኘው ኢባዱረህማን መስጂድ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ስራ አሰፈፃሚ ሰብሳቢ ኡስታዝ ሀሽም ሀምዛ
መስጂዱ እድሜ ጠገብና ታሪካዊ እንደሆነና በትላንቶናው እለት የተከናወነው ተግባር ተገቢ አለመሆኑን አስተዳደሩም መረጃውን አጥርቶ እርምጃ እንዲወስድ የጠየቁ ሲሆን ይዞታውን እንዲያስጠብቅ ጠይዋል።
አስተዳደሩ ተቀራርቦ በጉዳዮ ለይ በመወያየቱ ያመስግኑት ሰብሳቢው ከዚህ ቀደም እንደሚያደርጉት ሁሉ ተቀራርበው እደሚሰሩም አስታውቀዋል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን መረጃ አግባብነት የሌለው መሆኑን ገልፀው ክስተቱ በአስተዳዳሩ እውቅና እንደሌለውና ተቋማዊ አሰራርን ያልጠበቀ ሲሆን አስተዳዳሩ መረጃውን አጥርቶ ተጠያቂ እንደሚያደርግና አንዲትም የመስጂዱ ህጋዊ አካል እንደማይነካ አረጋግጠዋል።
አስተዳዳሩ ከመጂሊሱ ጋር በማህበራዊና የልማት ስራዎች ላይ ተቀራርቦ እየሰራ መሆንና ይህንንም እንደሚያስቀጥል አስታውቀዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም የተሳሳተ መረጃ በመያዝ ህዝበ ሙስሊሙ እንዳይረጋጋ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ማህበረሰቡም ትክክለኛ መረጃ ከአስተዳዳሩ እንዲወስዱ መልዕክት አስተላልፈዋል።
24/05/2023
በክፍለ ከተማው የቆሙ ህንፃዎች ግንባታቸው የሚያልቅበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሔደ፡፡
ኮልፌ ቀራኒዮ ኮሙኒኬሽን ግንቦት 16/2015ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተቋቋመ ቡድን የቆሙ ህንፃዎችና የባዶ መሬት ልየታ ግኝት ለአመራሩ ማወያየቱ ይታወሳላ። ይህንን ተከትሎ በዛሬው እለት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ባለቤት የተገኘላቸው የቆሙ ሆንፃዎች ባለቤቶቻቻው ጋር ውይይት አድርገዋል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የቆሙ ህንፃዎች ግንባታቸው የሚጠናቀቁበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓ መግባባት መደረሱንና የአስተዳደሩ እርዳታ በሚያስፈልግበት ጊዜ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።
በልየታውም በክፍለ ከተማው አስሩ ወረዳዎች 494 የቆሙ ህንፃዎች የተለዮ ሲሆን 393 የባለቤትነት መረጃ ያቀረቡ መሆናቸው በጥናቱ መጠቆሙ ይታወሳል።
24/05/2023
የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ስርጭቱን ለመቀነስ ህብረተሰቡ ሳይዘናጋ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል ሲል የክፍለ ከተማው ጤና ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ግንቦት 16/2015ዓ.ም
በዛሬው ዕለት የክፍለ ከተማው ጤና ጽ/ቤት ከህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ከሁሉም ወረዳ ለተውጣጡ ለብሎክ አደረጃጀት ማህበራዊ ዘርፍ አመራሮች በ ኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት መባባስ እና መከላከያ መንገዶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን አስታውቋል፡፡
በስልጠናው ላይ የተገኙት የጽ/ቤቱ ሀላፊ ወ/ሮ ሂሩት ባንጃው የስልጠናው አላማ ህብረተሰቡ የሚያደርገውን ጥንቃቄ በመዘናጋቱ የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ የሚያዙ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመራቸው የመድረኩ የተገኑ አካላት ለማህበረሰባችን ቅርብ በመሆናቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡
ሰልጣኞች በበኩላቸው ስልጠናው መሰጠቱ ጥሩ ነው በሽታው አሳሳቢ ደረጃ በመድረሱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ቀጣይነት ቢኖረው ሲሉ ገልፀው በተለያዩ አከባቢዎች ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ድርጊቶችን መንግስት ቁጥጥር ቢያደርግ እንዲሁም ኮንዶም በተገቢው መንገድ አግባብነት ባላቸው ቦታዎች ላይ ስርጭት ቢደረግ ሲሉ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡