Ethiopian Capital Market Investors Expo Successfully Concluded
*******************************************************************
The Ethiopian Capital Market Authority successfully concluded the two-day Investors Expo held from June 19–20, 2026 with strong public participation and a significant number of visitors attending to learn more about investment opportunities in the capital market.
We sincerely thank all stakeholders, exhibitors, and participants whose contributions helped make the Expo a meaningful and successful event.
ECMA remains committed to creating similar platforms that promote investor awareness, enhance understanding of the capital market, and strengthen investor protection across Ethiopia.
የካፒታል ገበያ ኢንቬስተሮች ቀን አውደ ርዕይ በስኬት ተጠናቀቀ
************************************************
የኢትዮጵያ የካፒታል ባለስልጣን ከሰኔ 12 እስከ13 2018 ዓ.ም ያካሄደውን የሁለት ቀናት የኢንቬስተሮች አውደ ርዕይ በስኬት አጠናቋል።
በአውደ ርዕዩ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጎብኚዎች የጎበኙ ሲሆን፥ ስለ ካፒታል ገበያው እድሎች እና የኢንቨስትመንት አማራጮች ሰፊ ግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰጠበት መርሃ -ግብር ሆኖ አልፏል።
ለአወደ ርዕዩ ውጤታማ መሆን እና ለስኬታማነቱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት፣ ለተሳታፊዎች እና ለጉብኝዎች በሙሉ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል ።
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የካፒታል ገበያውን ግንዛቤ የሚያስጨብጡ፣ በመላው ኢትዮጵያ የኢንቬስተሮችን ደህንነት የሚያስጠብቁ መሰል መድረኮችን በማዘጋጀት በቂ ግንዛቤ እንዲኖር የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=XbQBCdNJMFY&t=63s
Ethiopian Capital Market Authority - የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን
Official page of the Ethiopian Capital Markets Authority
15/06/2026
Meet and Greet with the Ethiopian Capital Market Authority Director General
****************************************************************
The Ethiopian capital market is evolving fast, and this is your rare opportunity to sit down face-to-face with the Director General of the Ethiopian Capital Market Authority (ECMA).
This exclusive individual session is designed for active, high impact engagement. Come ready to:
✅ Ask questions and gain insights into the emerging Ethiopian Capital Market.
✅ Present your new ideas, products, alternatives, and innovative market solutions.
✅ Share a document or do a quick presentation to showcase your strategic vision.
✅ Flag operational bottlenecks or administrative challenges affecting your business operations.
✅ Appointments are strictly limited and granted on a first-come, first-served basis. Secure your preferred executive session for June 19 or 20, 2026, by registering today:
🔗 Register Here https://lnkd.in/efM7j_J4
ልዩ የውይይት እና የምክክር መድረክ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጋር
*******************************************************
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ይገኛል፤ ይህ መድረክ በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች፣ ኢንቨስተሮች እና ተዋናዮች ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጋር በቀጥታ ለመገናኘት እና ለመወያየት የተዘጋጀ ልዩ መድረክ ነው።
ይህ የተለየ የአንድ ለአንድ የውይይት መድረክ በገበያው ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ጠቃሚ ውይይቶችን ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ለውይይት ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው እንዲቀርቡ ተጋብዘዋል፦
✅ አዲስ እየተገነባ ስላለው የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ማብራሪያዎችን እንዲጠይቁ ብሎም ጠቃሚ መረጃዎችን እንዲቀስሙ፤
✅ አዳዲስ የገበያ ሀሳቦችን፣ የፋይናንስ አማራጮችን እና የገበያ መፍትሄዎችን እንዲያቀርቡ፤
የእርስዎን ስትራቴጂካዊ ራዕይ የሚያሳዩ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ ወይም አጭር ማብራሪያ እንዲሰጡ፤
✅ በስራዎ ላይ ተጽዕኖ እያሳደሩ ያሉ የአሰራር ማነቆዎችን ወይም አስተዳደራዊ ተግዳሮቶችን እንዲያነሱ።
✅ የቀጠሮ አሰጣጥ መረጃ፦ የምክክር ጊዜዎቹ በጣም ውስን በመሆናቸው ቀጠሮ የሚሰጠው ቀድመው ለተመዘገቡ ቅድሚያ በመስጠት ይሆናል።
በመሆኑም ለሰኔ 12 ወይም 13 ቀን 2018 ዓ.ም በተመደቡት ልዩ የውይይት ክፍለ-ጊዜ ዛሬውኑ እንዲመዘገቡ ተጋብዘዋል።
🔗 ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ https://lnkd.in/efM7j_J4
15/06/2026
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሰኔ 12 እና 13 2018 ዓ.ም የሚያዘጋጀው የኢንቬስተሮች ኤክስፓ ሊካሄድ አራት ቀናት ብቻ ቀሩት !!
ቦታ፦ በአዲስ አበባ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ግቢ ፋላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ
መግቢያ፦ በነጻ!
መሳተፈዎን ቀደም ብለው ለማሳወቅ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መመዝገብ ይችላሉ፡፡
https://lnkd.in/eQgfRjvD
12/06/2026
ECMA and Luxembourg Delegation Discuss Collaboration
***************************************************
The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) was pleased to welcome H.E. Jeanne Crauser, Ambassador of Luxembourg to Ethiopia, Ms. Ariane Moayed, Chargé d’Affaires, and Mr. Maxime Ladriere, First Secretary, for a productive discussion on strengthening cooperation between Luxembourg and Ethiopia’s emerging capital market.
The meeting served as a follow-up to previous engagements and focused on potential areas of technical assistance and collaboration that the Embassy of Luxembourg may facilitate in support of ECMA’s market development initiatives.
Discussions explored opportunities for cooperation with the Luxembourg Stock Exchange and LHoFT (Luxembourg House of Financial Technology), a Luxembourg government-supported financial technology and innovation hub. Key areas of collaboration were identified, including knowledge sharing, capacity building, market development, and the promotion of innovation within Ethiopia’s capital market ecosystem.
The meeting concluded with a shared understanding to pursue these collaboration opportunities and further strengthen ties between the two institutions for the benefit of Ethiopia’s capital market development.
ECMA extends its appreciation to Ambassador Jeanne Crauser and Ms. Ariane Moayed for their continued engagement and support in advancing international partnerships that contribute to the growth and development of Ethiopia’s capital market.
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሉክሰምበርግ ልዑካን ቡድን አባላት ጋር ውይይት አደረገ
***************************************************************
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በኢትዮጵያ የሉክስምበርግ አምባሳደር ከሆኑት ክቡርት ዣን ክራውዘር፣ ሻርዠ ደፌር አሪያን ሞያ እንዲሁም የመጀመሪያ ጸሀፊ ከሆኑት ማክስም ላድሪየርን ጋር በሉክሰምበርግ እና በኢትዮጵያ መካከል በካፒታል ገበያ ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ውጤታማ ውይይት አድርጓል።
ውይይቱ ቀደም ሲል የነበሩ ግንኙነቶችን መሰረት አድርጎ የቀጠለ ሲሆን በኢትዮጵያ የሉክሰምበርግ ኢምባሲ የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ልማት ሥራዎች ለመደገፍ በሚችላቸው የቴክኒክ ድጋፍ እና የትብብር መስኮች ላይም ትኩረት ሰጥቷል፡፡
በውይይቱ ከሉክሰምበርግ ስቶክ ኤክስቸንጅ (Luxembourg Stock Exchange) እና በሉክሰምበርግ መንግሥት ከሚደገፈው የፋይናንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ማዕከል (Luxembourg House of Financial Technology) ጋር በትብብር መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ምክክር ተደርጓል፡፡
በዚህም የእውቀት ሽግግር፣ የአቅም ግንባታ፣ የገበያ ልማት እና በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር ውስጥ ውስጥ በጋራ የሚስሩ የትብብር መስኮችን በመለየት እነዚህን የትብብር ዕድሎች በተግባር ለማዋል እና ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ዕድገት መጠናከር አጋርነትን በማሳደግ ረገድ በኢትዮጵያ የሉክስምበርግ ኢምባሲ እያደረገ ላለው እገዛ እንዲሁም ለአምባሳደር ዣን ክራውዘር እና ለባለደረቦቿ ያለውን ምስጋና ይገልጻል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Flamingo, Minaye Building 16th Floor
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:30 - 17:30 |
| Tuesday | 08:30 - 17:30 |
| Wednesday | 08:30 - 17:30 |
| Thursday | 08:30 - 05:30 |
| Friday | 08:30 - 17:30 |
