19/06/2026
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 989/ 2016 መሠረት ስለየእውቅና አሰጣጥ ገምጋሚ ቡድን ተግባርና ኃላፊነት
------------------------------------------------------------------------------------------------------
** የቀረቡትን የእውቅና ጥያቄ ማመልከቻ፣ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ ሪፖርት፣ የሰልጣኝ እርካታ ዳሰሳ ሪፖርት እና የግለ- ግምገማ ሰነድን ይመረምራል፤
** የእውቅና ግምገማ የጊዜ ሰሌዳን ያዘጋጃል፤ የመስክ ግምገማን ያካሄዳል፤
** የመስክ ግምገማውን ሲያጠናቀቅ ለተገምጋሚው ተቋም ስለ ግምገማው ሂደት የመውጫ ሪፖርት በጽሁፍ ይሰጣል፤
** የግምገማ ሪፖርት በማዘጋጀት ለዴስክ ኃላፊ ያቀርባል፤ እና
** ዝርዝር የገምጋሚ ቡድኑ ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የቡድን አባላት አመራረጥ በባለሥልጣኑ የአሠራር ሰርዓት ይወሰናል፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
14/06/2026
ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፈቃድ አሰጣጥ የውጭ ገምጋሚዎችን ለማፍራት የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ
===== = ===== ===== ===== ===== ===== ===== ===== =====
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ከተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያዎች ከሰኔ 06-07/2018 ዓ.ም በመልካ አዳማ ሆቴል ስልጠና ሰጠ።
ስልጠናው ለውጭ ገምጋሚ እና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ፈቃድ አሰጣጥ፣ የክትትል እና ቁጥጥር፣ የጥራት ኦዲት መመሪያዎች እና መስፈርቶች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር፤ እንዲሁም በቀጣይ ሰልጣኝ ባለሙያዎቹ ከባለሥልጣኑ ጋር በጋራ ለመስራት እንዲያስችል ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና አጠቃላይ ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መቅደስ ደረሰ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል።
የስልጣናውን አላማ ለማሳካት የፈቃድ አሰጣጥ መመሪያና መስፈርቶች (በአቶ ብርሃነመስቀል መላክ የቴ/ሙ/ስ ፈቃድ ዴስክ ኃላፊ)፣ የጥራት ኦዲት መመሪያ፣ የጥራት ኦዲት ስታንዳርድና አመልካች፣ የጥራት ኦዲት ሂደት ማኑዋል (በአቶ ኡርጂ ሙሉጌታ የኦዲት ከፍተኛ ባለሙያ)፤ የክትትል እና ቁጥጥር ግምገማ መስፈርቶችና ስታንዳርዶች (በዶ/ር ታምራት ሀይሌ-የቁጥጥርና ክትትል ባለሙያ)፤ እንዲሁም የገምጋሚዎች ሙያዊ ሥነ-ምግባር እና የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት (በአቶ ስማቸው አስሬ-የቴሙስ ፈቃድ ባለሙያ) ባጠቃላይ 4 ጽሁፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
የቀረቡትን ጽሁፎች መሰረት በማድረግ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተው በመሪ ስራ አስፈጻሚዋ ወ/ሮ መቅደስ ደረሰ እና በጽሁፍ አቅራቢዎች፤ እንዲሁም ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር በመጡ ተሳታፊ በቂ ማብራሪያዎች የተሰጡ ሲሆን ለቀጣይ ስራ በእቅድ የሚካተቱ እና ተኩረት የሚሹ በርካታ ግብዓት የሚሆኑ አስተያየቶችም ከተሳታፊዎች መገኘታቸው ተገልጿል።
ባለሥልጣኑ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች የታደለ ተቋም መሆኑን ያደነቁት የስልጠናው ተሳታፊዎች በቀጣይም ስታንዳርዶችን የማስተዋወቅ እና ሌሎች የአቅም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው ከቀጠሉ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፉ ወጥነት እና ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንደሚመጣ ስልጠናው ያሳደረባቸውን እምነት ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
በመጨረሻም “ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የተወጣጡ ሰልጣኞች በቀጣይ ባለሥልጣኑ በሚያከናውናቸው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፈቃድ አሰጣጥ ስራዎች ጋር በተያያዘ አምባሳደር ሆናችሁ የምትቀርቡት እናንተው ሰልጣኞች ናችሁ” ያሉት ወ/ሮ መቅደስ ደረሰ ለወደፊት ከባለስልጣኑ ጋር የትብብር ስራዎችን ለማከናወን ማንኛውንም ሙያዊ ጥያቄዎችን ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ሰልጣኞች ያገኙትን ግንዛቤ ወደ መጡበት ተቋማቸውም የማስረጽ ድርሻቸውን እንዲወጡ መሪ ስራ አስፈጻሚዋ መልዕክታቸውን አስተላለረፈዋል።
ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ፤አዳማ
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ::
14/06/2026
ለውጭ ገምጋሚ እና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለ ሥልጠና(2ኛ ቀን፤ ሰኔ 07/2018 ዓ.ም)
መልካ አዳማ ሆቴል (አዳማ)
[በቴ/ሙ/ስ ፈቃድ አሰጣጥ፣ የቁጥጥር እና ክትትል እንዲሁም ጥራት ኦዲት ስራ አስፈጻሚ የተዘጋጀ]
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ::
14/06/2026
ለውጭ ገምጋሚ እና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለ ሥልጠና(የመጀመሪያ ቀን፤ ሰኔ 06/2018 ዓ.ም)
መልካ አዳማ ሆቴል (አዳማ)
[በቴ/ሙ/ስ ፈቃድ አሰጣጥ፣ የቁጥጥር እና ክትትል እንዲሁም ጥራት ኦዲት ስራ አስፈጻሚ የተዘጋጀ]
12/06/2026
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 989/ 2016 መሠረት ስለ እውቅና አሰጣጥ አተገባበር
-------------------------------------------------------------------------------------------------------
** ባለሥልጣኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የእውቅና አሰጣጥ ሥርዓት ወጥነት እንዲኖረው ያደርጋል።
** ባለሥልጣኑ በፌደራል መንግሥት አካላት ለሚቋቋሙ ማሰልጠኛ ተቋማት፣ በፌደራል ደረጃ በግል ለሚቋቋሙ ማሰልጠኛ ተቋማት፣ በውጪ ዜጐች ለሚቋቋሙ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲሁም በሌላ አገር ሕግ በተቋቋሙ ሥር መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለሚተዳደሩ ማሰልጠኛ ተቋማት እውቅና ይሰጣል።
** ከላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በክልል የእውቅና አሰጣጥ ስራን እንዲያከናውን ህጋዊ ውክልና የተሰጠው አካል የባለስልጣኑን የእውቅና አሰጣጥ ስርኣትና መመሪያ፣ ስታንዳርዶች እና የማስፈጸሚያ ሰነዶች መሠረት በማድረግ ፈቃድ ለተሰጣቸው ማሰልጠና ተቋማት እና ፕሮግራሞች እውቅና ይሰጣል።
** ባለሥልጣኑ በክልል ህጋዊ ውክልና የተሰጠው አካል በባለሥልጣኑ የወጡ የአሰራር ስርአትና መመሪያ፣ ስታንዳርዶች እና የማስፈጸሚያ ሰነዶች ተግባራዊ መደረጋቸውን በሱፐርቪዥን ይከታተላል።
** ባለሥልጣኑ በክልል ህጋዊ ውክልና በተሰጠው ኣካል ተገምግመው እውቅና ባገኙ ተቋማት እና ፕሮግራሞች ላይ የናሙና ግምገማን ያካሂዳል፡፡
** እውቅና ለመስጠት የሚደረግ ግምገማ ግልጽነት በተላበሰና አሳታፊ በሆነ ሥርዓት የሚከናወን መሆን ይኖርበታል።
** ባለሥልጣኑ በክልል የእውቅና አሰጣጥ ስራን እንዲያከናውን ህጋዊ ውክልና ለተሰጠው አካል እንዲሁም ውክልና በተሰጠው አካል እውቅና ላገኙ ማሰልጠኛ ተቋማት የአቅም ግንባታ ድጋፍ ሊያደርግ ይችላል፡፡
** በክልል የእውቅና አሰጣጥ ስራን እንዲያከናውን ህጋዊ ውክልና የተሰጠው አካል እውቅና የሰጣቸውን የማስልጠኛ ተቋማት እና ፕሮግራሞች ለባለሥልጣኑ ያሳውቃል፡፡
** ባለሥልጣኑም በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን ተቋማት ዝርዝር መዝግቦ ይይዛል፤ በየአመቱም ዝርዝራቸውን ያወጣል፡፡
** ባለሥልጣኑ የእውቅና አሰጣጥ ሰነዶች ላይ ለውጦችን ወይም ማሻሻያዎችን በሚያደርግበት ጊዜ በክልል የእውቅናአሰጣጥ ስራን እንዲያከናውን ህጋዊ ውክልና የተሰጠው አካል እንዲሁም የማሰልጠኛ ተቋማት እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
10/06/2026
ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ
===============
መስሪያቤታችን የኢፌዴሪ ትምህርት ስልጠና ባለስልጣን ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ባለሙያዎችን አወዳድሮ በዝውውር መቅጠር ይፈልጋል።
#ማሳሰቢያ፡-
1 . ከዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ በላይ የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃ ያላቸው አመልካቾች ማመልከት ይችላሉ፡፡
2 .የምዝገባ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ይሆናል፡፡
ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የዲግሪ የትምህርት ማስረጃ የሚያቀርቡ አመልካቾች የመውጫ ፈተና ያለፉበትን መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ከግል ተቋማት የሚቀርቡ የስራ ልምድ ማስረጃዎች የስራ ግብር የተከፈለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
4. አመልካቾች ለሚያቀርቡት የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ ህጋዊነት ኃላፊነት ይወስዳሉ።
5. ለፈተና ለሚመለመሉ አመልካቾች ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ በማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል።
6. የምዝገባ አድራሻ፡- አዲስ አበባ በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ሽሮ ሜዳ ከአሜሪካ ኢምባሲ ፊት ለፊት
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
07/06/2026
ከኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣልን ጋር በመተባበር ለፌዴራልና ለክልል ማረሚያ ቤት ለትምህርትና ስልጠና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ
==== === ================================
ዝዋይ ግንቦት 29/2018ዓ.ም. (የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን)
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ከኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣልን ጋር በመተባበር ከፌዴራልና ከክልል ማረሚያ ቤት ለተውጣቱ የትምህርትና ስልጠና ባለሙያዎች ከግንቦት 27 -29/2018ዓ.ም. ድረስ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።
በስልጠናው የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ጀኔራል ሉባባ ጀማል እንደተናገሩት የህግ ታራሚዎችን አርሞና አንጾ አምራችና ህግ አክባሪ ዜጋ ሆነው እንዲወጡ ለትምህርትና ስልጠና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
በኮሚሽኑ የሚሰጡ ስልጠናዎች ከህግ ታራሚዎችን በተጨማሪ አባላትን ማካተት እንደለበት በተቋሙ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በግልጽ መቀመጡን የተናገሩት ም/ኮሚሽነሯ ለማረም ማነጽና ተሃድሶ ልማት ባለሙያዎች የሚሰጡ ስልጠናዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣልን የቴክኒክና ሙያ ፍቃድ አሰጣጥ ዴስክ ኃላፊ አቶ ብርሀነ መስቀል መላክ በበኩላቸው ስልጠናው ኮሚሽኑ የትምህርትና ስልጠና ፍቃድ ለማግኘት ምን ማሟላት እንደሚገባውና ምን አይነት ዶክመንት ማዘጋጀት እንዳለበት የሚያስችል መሆኑን አመላክተዋል።
የትምህርት ተቋማት የፍቃድ ጥያቄ አቀራረብ ሂደቶችን፣ ፍቃድና እድሳት እንዴት እንደሚሰጥ፣ ፍቃድ ለመጠየቅ ዝቅተኛ መስፈርቶች ምን እንደሆኑ ሰልጣኞች ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
ከስልጠና ተሳታፊዎች መካከል አቶ አበባው አበበ እና ዋ/ኢ/ር ደረጄ ብራቱ አሰራራቸውን እንዴት ማዘመን እንዳለባቸው ከእነሱ አስተምህሮ አንፃር ሰልጣኞችን በምን አግባብ ማስተማር እና መመዘን እንዳለባቸው ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡
በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የሐራ ደንበል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅን በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ መደረጉን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
05/06/2026
ለባለሥልጣኑ ሠራተኞች በሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና በጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
----------------------------------------------------------------------------------------------
ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በመጡ አሰልጣኝ ለባለሥልጣኑ ሠራተኞች በሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና በጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የስልጠናው ዓላማ በሀገራችን በየዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችና የሚወሰኑ ውሳኔዎች ስነምግባራዊ እንዲሆኑና የጥቅም ግጭትን ለመከላከልና ለማስተዳደር የሚያስችል አቅም ማጎልበት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህር ፣ አማካሪ እና የዩኒቨሲቲ የሥነምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አዲስዓለም በቀለ ስነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ትክክለኛ፣ ግልፅ፣ ፍትሃዊነትና ተገቢነት ያላቸው ሃሳቦችን መሠረት ያደረገ እና በሠራተኞች፤ በተቋማትና በማህበረሰብ ላይ የሚያስከትለውን ውጤት አስቀድሞ በማጤንና በመተንተን ውሳኔ ለመስጠት፣ ታማኝነትና ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በስልጠናው ላይ ስነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት ምንነት፤ የዘርፎች ተጋላጭነት፣ የጥቅም ግጭትን መከላከልና ማስተዳደር፣ የስነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎች፣ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን የተዳሰሱ ሲሆን የጥቅም ግጭት ሙስና እንዲስፋፋ ምቹ አጋጣሚዎችን ከሚፈጥሩ መንስኤዎች አንዱ በመሆኑ ይህንን መከላከል ተገቢ መሆኑ ተገልጿ፡፡
የቀረቡትን መነሻ ሀሳቦች መሠረት በማድረግ በተደረገው ውይይት ላይ ለተነሱ ሐሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህር ፣ አማካሪና የዩኒቨሲቲ የሥነምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር በሆኑት ዶ/ር አዲስዓለም በቀለ እና በባለሥልጣኑ የሥነ-ምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት ወ/ሮ መቅደስ ወንዱአንተ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
02/06/2026
#ባሉበት፤
--------------------------------------
በunified መሶብ አማካኝነት በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተመለከተ ዝርዝር ገለጻና እና ውይይት ለማድረግ እቅድ ተይዟል።
ስለሆነም በዚህ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚደረገው ገለጻ እና ውይይት ላይ የተቋሙ የበላይ ኃላፊ እና ሬጅስትራር ኃላፊ አርብ፣ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ሰዓት በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ በጥብቅ እያሳወቅን ስብሰባው ላይ መገኘት የማይችሉ ሀላፊዎች ተወካይ መላክ እንዳለባቸው እናሳስባለን፡፡
የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ::