Addis Ababa City Manager's Office

Addis Ababa City Manager's Office

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ababa City Manager's Office, Government Organization, Addis Ababa.

For a Vibrant Addis Ababa: Efficient and Effective Service

This page presents information on the Addis Ababa City Manager’s Office, particularly its mandate, responsibilities, and work in the municipal service sector.

18/06/2026
Photos from Abiy Ahmed Ali's post 18/06/2026
Photos from Addis Ababa City Manager's Office's post 17/06/2026

የ90 ቀናት ልዩ የንቅናቄ መሪ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት የ90 ቀናት ልዩ የክረምት ንቅናቄ ስራዎች መሪ እቅድ ላይ ከተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ዛሬ የጋራ ውይይት አካሄደ።

በመድረኩ በቀጣይ 90 ቀናት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እና በተቋማት ቅንጅት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። በተለይም የአረንጓዴ አሻራ፣ የወንዞች ብክለትና የጎርፍ አደጋ መከላከል፣ የከተማ ጽዳትና ውበት፣ አረንጓዴ ልማት፣ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች፣ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እና ንጹህና ምቹ ከተማን መፍጠር ላይ በውይይቱ የተነሱ ቁልፍ ጉዳዮች ነበሩ።

በመድረኩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እንደገለጹት፣ የ90 ቀናት ልዩ የንቅናቄ እቅዱን ወደ ተግባር ለመቀየር በሁሉም ዘርፎች የተቀናጀ፣ ውጤት ተኮር እና ኃላፊነት ያለው አሰራር መዘርጋት ያስፈልጋል።

ኢንጅነር ወንድሙ በመሠረተ ልማት ግንባታና ጥበቃ፣ በጽዳት፣ በውበት፣ በአረንጓዴ ልማት እና በአረንጓዴ አሻራ ስራዎች ህብረተሰቡን በባለቤትነት ማሳተፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ከከተማ አስተዳደሩ የወረደውን እቅድና አቅጣጫ ከተቋማት የተግባር እቅድ ጋር በማስተሳሰር በልዩ ትኩረት መፈጸም እንዳለበትም ገልጸዋል።

በተጨማሪም የአደጋ ስጋትና የጎርፍ መከላከል ስራዎች፣ ንጹህ የመኖሪያ አካባቢ መፍጠር፣ የሞዴል ብሎክ መስፈርትን የሚያሟሉ አካባቢዎችን ማስፋፋት እና የከተማውን ነዋሪ በባለቤትነት ማሳተፍ በቅንጅት ሊተገበሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኢንጅነር ወንድሙ ሞዴል ብሎኮችን መፍጠር፣ የበጎ ፈቃደኞችን ተሳትፎ ማጎልበት፣ ጽዳትን የህብረተሰቡ ባህል ማድረግ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማጠናከር እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን በትኩረት ማከናወን እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የወንዝ ዳርቻ ጽዳትን መጠበቅ፣ ወቅታዊ የኩነት ምዝገባ ማሳደግ፣ ሀገራዊና ሀይማኖታዊ በዓላት ቅድመ ዝግጅት፣ ወንዞችን ከብክለት መጠበቅ፣ የጎርፍ ፍሳሽ መስመሮችን ማጽዳት እና የከተማዋን ጽዳት፣ ውበትና አረንጓዴ መሠረተ ልማቶች በጋራ መንከባከብ በትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።

የ90 ቀናት ልዩ የንቅናቄ እቅድ በቀሪ ጊዜያት ውጤታማ እንዲሆን የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግና በስፋት ማሳተፍ አስፈላጊ መሆኑን ኢንጅነር ወንድሙ ገልጸዋል። በተለይም ከክረምት ወቅት ጋር ተያይዞ የጎርፍ መፍሳሽ መሠረተ ልማትን የሚጎዱ ችግሮችን፣ ከደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት ጋር የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት ፈጣን ምላሽ መስጠት ላይ ተቋማት በትኩረት እንዲሰሩ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

በአረንጓዴ አሻራ፣ በመንገድ ዳር መብራት መሠረተ ልማት፣ በኮሪደር ልማት ስራዎች ጥበቃና እንክብካቤ እንዲሁም ሁሉንም ስራዎች በተገቢው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ በማጀብ ለማህበረሰቡ ተደራሽ ማድረግ ላይ በተቀናጀ መልኩ መስራት እንዳለባቸው በመድረኩ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

Photos from Addis Ababa City Manager's Office's post 17/06/2026

የኦን ላይን አገልግሎት መተግበሪያ የደረሰበት ደረጃ ተገመገመ

CRRSA: ሰኔ 10/2018ዓ.ም
አዲስ አበባ

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የኦንላይን አገልግሎት ለመስጠት እያለማ የሚገኘው መተግበሪያ (Portal) የደረሰበት ደረጃ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በተገኙበት ተገምግሟል፡፡

በኦንላይን ስለሚሰጡ አገልግሎቶች እና አሁን የደረሰበትን ደረጃ ያቀረቡት በኤጀንሲው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙዘሚል ሀሰን መተግበሪያው አሁን ላይ የልደት ካርድ፣የመታወቂያ አገልግሎት እና ያላገባ ማረጋገጫ የከተማዋ ነዋሪዎች በኦንላይን በመጠየቅ አገልግሎት ማግኘት እሚችሉበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አዲስ የለማው ሲስተም የገፅ ለገፅ ግንኙነትን በማስቀረት የከተማችን ነዋሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት መጠየቅ እና ማግኘት የሚችሉበት ትልቅ የአገልግሎት ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑን ገልፀው በእያንዳንዱ ነዋሪ ቤት በመድረስ አገልግሎትን በቀላሉ ተደራሽ ስለሚያደርግ ለከተማው ነዋሪ የምስራች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ በበኩላቸው ሲስተሙ ብቁ እና ውጤታማ መሆኑን ለማረጋገጥ በርካታ ሙከራዎች ሲደረጉ እንደነበር ገልፀው የለማው የኦንላይን መተግበሪያ አገልግሎት አሰጣጥን ብቻ ሳይሆን ደንበኞች በአካል መገኘት ሳይጠበቅባቸው አገልግሎትን በማግኘት የደንበኞችን ድካምና ምልልስ በማስወገድ እንዲሁም ጊዜን ከመቆጠብ ባሻገር ብልሹ አሰራርንና ሌብነትን በማስወገድ ከተማንም ሆነ ሀገርን እንደሚቀይር ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የከተማ አስተዳደሩ የስራ አስኪያጅ አመራሮች፣የኤጀንሲው አመራሮች እና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል::

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication's post 17/06/2026
Photos from Addis Ababa City Manager's Office's post 16/06/2026

በአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የአፍሪካ የህፃናት ቀን ተከብሮ ዋለ።

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የአፍሪካ የህፃናት ቀንን አስመልክቶ ሁሉም የፅ/ቤቱ ባለሙያዎች በተገኙበት በዛሬው እለት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

በዚሁ ወቅት በአፍሪካ ለ36ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ35ኛ ጊዜ በመከበር ላይ ያለውን የአፍሪካ የህፃናት ቀን አስመልክቶ "ደህንነቱና ንፅህናዉ የተጠበቀ አካባቢ ለሁሉም ህፃናት!" በሚል መሪ ቃል ታሪካዊ ታሪካዊ አመጣጡን፣የሚከበርበት አላማ፣ ጽንሰ ሃሳቦች፣የህፃናት የእይታ ማዕከል፣የህፃናት ድምፅና የአካባቢ ንፅህና፣የአካባቢ ደህንነትና የንፅህና ጥበቃ፣ማህበራዊ መገለሎችን ከማስቀረት፣የህፃናት ደህንነትና የግል ጥበቃ አንፃር በእነዚህና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮችን የሚገልፅ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

በመድረኩ ላይ በቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅና የጥናትና ልማት ትግበራ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታድሰ እንደገለፁት የአፍሪካ የህፃናት ቀንን ለተቋሙ ባለሙያዎች በዚህ ልክ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች መካሄዱ ግንዛቤን በማስፋትና የበለጠ አቅም ለመፍጠር የሚያስችል ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።

የአፍሪካ የህፃናት ቀን ሲከበር ደህንነቱና ንፅህናዉ የተጠበቀ አካባቢ ለሁሉም ህፃናት ሲባል ደህንነት በብዙ መንገድ ሊገለፅ እንደሚችል ማለትም ህፃናት አካላዊና ስነ ልቦናዊ እንክብካቤ እንዲሁም ድጋፍ ሊደረግላቸዉ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

አክለዉም በመዲናችን የህፃናትን ደህንነት ከማረጋገጥ ረገድ በከተማችን የተሰሩት ስራዎች ለዉጥ ያመጡ እና ህፃናቱን ያማከለ ስራዎች መከናወናቸዉ መቻሉ የህፃናትን ደህንነት ይበልጥ ማረጋገጥ የተቻለበትና እንደሆነም አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም የህፃናትን ደህንነትና ምቹ አካባቢን ከመፍጠርም አንፃር እንደ አገርም ብሎም እንደከተማም አበረታች ተግባራት መከናወናቸዉን ጠቁመው ከተከናወኑት ተግባራት በተጨማሪም የህፃናት የነገ ሀገር ተረካቢ እንደመሆናቸዉ የህፃናት ደህንነት በሁሉም ማህበረሰብ ሊታገዝና ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
https://linktr.ee/aacitymanager

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30