Ministry of Transport and Logistics - Ethiopia

Ministry of Transport and Logistics - Ethiopia

Share

Ministry of Transport and Logistics የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

19/06/2026

የቢሾፍቱ አቡሴራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ኢትዮጵያን ወደ አቪዬሽን ማዕከልነት የማሸጋገር ሚና…

• አቡሴራ ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከባሕር ጠለል በላይ በ1 ሺህ 910 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ከአዲስ አበባ ቦሌ (2 ሺህ 334 ሜትር) በተሻለ ለአውሮፕላኖች መነሳትና ማረፍ እጅግ ምቹ የአየር ሁኔታን ይሰጣል።

• የአቡሴራ ከፍታ ከአዲስ አበባ ቦሌ ያነሰ በመሆኑ፣ የዓለም አቀፍ በረራ አውሮፕላኖች ሙሉ ነዳጅና ጭነት ይዘው ረጅም ርቀት በቀጥታ እንዲበሩ ሰፊ የአቪዬሽን ምቹነትን ይሰጣል። የአውሮፕላኖች የመጫን አቅምን ጨመረ ማለት ነው።

• ምቹ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ እና የአቪዬሽን ብቃት ደግሞ ሌላኛው ሚናው ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም ካርታ ላይ ያላት ስልታዊ አቀማመጥ (በአውሮፓ፣ በእስያ እና በአፍሪካ መገናኛ መስመር ላይ መገኘቷ) አቡሴራን ለዓለም አቀፍ በረራዎች አጭርና ተመራጭ የመሸጋገሪያ መስመር ያደርገዋል።

• አየውሮፕላን ማረፊያው አራት ዘመናዊ ማኮብኮቢያዎች እና በአንድ ጊዜ እስከ 270 አውሮፕላኖችን ማቆም የሚችል ስፍራም ይኖረዋል። አሁን ካለው የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅም በ4 ነጥብ 4 እጥፍ ይበልጣል።

• የሚገነባው ግዙፍና ዘመናዊ የካርጎ ተርሚናል የዓለም የንግድ ዕቃዎች እና የህክምና አቅርቦቶች ከአምራች ሀገራት ተነስተው ወደ ተጠቃሚዎች የሚሰራጩበት ዋነኛ የአየር ሎጂስቲክስ ማዕከል እንዲሆን ያደርገዋል።

• እንደ አበባ፣ ፍራፍሬ እና ስጋ ያሉ የኢትዮጵያና የጎረቤት ሀገራት ምርቶች ሳይበላሹ በጥራትና በከፍተኛ ፍጥነት ወደ መላው ዓለም ገበያ እንዲደርሱ ያስችላል። ይህም የዓለም አቀፍ የአየር ጭነት ማዕከልነታችንን ያረጋግጥልናል ማለት ነው፡፡

• ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኢንደስትሪ ውስጥ እንደ ዱባይ (DXB) እና ሲንጋፖር (Changi) ያሉ ታላላቅ የዓለም መገናኛ ማዕከላት ተርታ ያሰልፋታል።

• ኢትዮጵያን የአፍሪካ ቁልፍ የአቪዬሽን መናኸሪያ በማድረግ ከአህጉራዊ የትራንዚት ማዕከልነት ወደ መላው ዓለም ስልታዊ መገናኛ ድልድይነት ያሸጋግራል፤
# ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን

Photos from Ethiopian News Agency's post 17/06/2026
Photos from Public Service Transport Service / ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት's post 17/06/2026
16/06/2026

በአዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር የሚከተሉት ጠቀሜታዎች ይኖሩታል፡፡

📌ለእያንዳንዱ የተመዘገበ ተሽከርካሪ ልዩ የሆነ የፊደል ቁጥር መለያና ስቲከር ለመስጠት፤

📌ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መነሻ በማድረግ በደረጃ በመጠንና በንድፍ ወጥነት እንዲኖረው ማድረግ ለዚህም በቬይና ስምምነት የተሠጠን ኮድ “ETH” ማካተት መቻሉ፤

📌ቀደም ሲል የነበረው የተሽከርካሪ ምዝገባ እና ሰነዶች ህጋዊነት በማረጋገጥ ድጋሚ ለመመዝገብ፤

📌በግልጽ የሚታይ እና በተለያዩ የብርሃን ሁኔታዎች ውስጥ በግልጽነት የሚታይ እንዲሆን አንጸባራቂ ምልክቶቹን ማካተት መቻሉ፤

📌በግልጽ የሚነበብ ህብረተሰቡ የሚያነበው እና ሕግ አስከባሪዎች ብቻ የሚያነቡት በግልጽ የፊደሎች አቀማመጦች እንዲኖሩት መቻሉ፤

📌ፎርጀሪን (ማጭበርበርን) ለመከላከል እንደ ሆሎግራም፣ የውሃ ምልክት እና ማይክሮ ጽሁፍ ያሉ የደህንነት ባህሪያትን እንዲካተት መደረጉ፤

📌በቀላሉ ከሲስተሞች (ከዲጂታል) ጋር ተነባቢ እንዲሆኑ እንደ ባርኮድ፣ QR ኮድ ወይም RFID ቺፖችን ለአስተማማኝ ዲጂታል መዝገቦች እና ክትትል መጠቀም መቻሉ፤

📌ለከባድ የአየር ሁኔታን በመቋቋም የሚችሉ ዘላቂ ቁስን መጠቀም መቻሉ፤

📌ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ወጪ የሚቆጥብ መሆኑ፤

📌ተሽከርካሪው ተመዝግቦ እስኪወገድ ድረስ በአንድ ሰሌዳ እና የፊት ለፊት መስታወት (Windshield) የሚለጠፍ ስቲክር የሚኖረው ይሆናል፡፡

📌አዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ( ታርጋ) ለውጥ ተመሳሳይ ታርጋዎችን ለማስቀረት፣ ህገ ወጥ ታርጋን ለመከላከል፣ ከተሽከርካሪ ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ፣የተሽከርካሪ ስርቆትን ለማስቀረት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት በመሆኑ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ጠቀሜታ አለው።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃዎችን ለማግኘት👇👇👇

በድረ ገጽ፡

www.motl.gov.et

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/EthiopianTransport?mibextid=ZbWKwL

በቴሌግራም:
https://t.me/ministryoftransportethiopia

በዩቲዩብ

https://youtube.com/

በትዊተር

https://x.com/MoTLogestics

በቲክቶክ

https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZS-93fuvA1twuuy

Photos from Ministry of Transport and Logistics - Ethiopia's post 15/06/2026

የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሰሌዳ አመራረት፣ አሰረጫጨት እና አወጋገድ ላይ ወጥነት ያለው የአሰራር ስርዓት መፈጠር እንዳለበት ተመላከተ።

ሰኔ 8/2018 ዓ.ም (ትሎሚ):-የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለክልል የትራንስፖርት ዘርፍ እና የከተማ መስተዳድር ኃላፊዎች በዘርፉ በወጡ አዋጆች ፣ ደንቦች ፣እና መመሪያዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሰሌዳ አመራረት፣ አሰረጫጨት፣ አወጋገድ ላይ ወጥነት ያለው የአሰራር ስርዓት መተግበር ላይ ያተኮረ ውይይት ተደርጓል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር አለሙ ሰሜ አዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ( ታርጋ) ለውጥ ተመሳሳይ ታርጋዎችን ለማስቀረት፣ ህገ ወጥ ታርጋን ለመከላከል፣ ከተሽከርካሪ ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ፣የተሽከርካሪ ስርቆትን ለማስቀረት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት በመሆኑ እነዚህን ችግሮች መቅረፍ እንደሚቻል ተናግረዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ ክቡር አቶ በርኦ ሀሰን በበኩላቸው አዲሱ የተሽከርካሪ ታርጋ ለውጥ የትራንስፖርት ዘርፉን ሪፎርም ለማድረግ፣ የዘርፉን ፓሊሲ ለማሳለጥ እና ወጥ የሆነ መረጃ አያያዝ እንዲኖር በማስቻል ሀገራዊ የዘርፉ ስታንዳርድ ከፍ የማድረግ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ ከነባሩ ታርጋ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲቻል፣ ከተሽከርካሪ መረጃ አያያዝ ጋር ያሉ ችግሮችን ለመፍታት፣ የተሳለጠ እና የተናበበ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር ለማስቻል አዲሱ የተሽከርካሪ ታርጋ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ የተገኙ የዘርፉ ስራ ኃላፊዎች በሰጡት አሰተያየት አዲሱ የታርጋ ለውጥ መኖሩ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን ገልፀው ተመዝግበው ቆይተው ስርጭት የጀመሩ ተቋማት የሰሌዳ አሰጣጡ ከመዘግየቱ ውጭ በአዲሱ ታርጋ ተጠቃሚዎች መደሰታቸውን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ በማጠቃለያው ከነባሩ ታርጋ ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት ከአንዱ ክልል ወደ ሌላው ክልል በትራንስፖርት በሚደረግ እንቅስቃሴ ግለሰቦች ለጥቃት የሚጋለጡበት ሁኔታ ጭምር መኖሩን ጠቅሰው አዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ይህን ችግር የሚፈታ እና የሀገራችንን የወል ትርክት ሊያዳብር የሚያስችል ነው ብለዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃዎችን ለማግኘት👇👇👇

በድረ ገጽ፡

www.motl.gov.et

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/EthiopianTransport?mibextid=ZbWKwL

በቴሌግራም:
https://t.me/ministryoftransportethiopia

በዩቲዩብ

https://youtube.com/

በትዊተር

https://x.com/MoTLogestics

በቲክቶክ

https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZS-93fuvA1twuuy

Photos from Abiy Ahmed Ali's post 15/06/2026
15/06/2026
Photos from Central Ethiopia Regional Government Transport & Road Development Bureau's post 11/06/2026
Photos from Ministry of Transport and Logistics - Ethiopia's post 11/06/2026

የህዝብ ትራንስፖርት ኤሌክትሮኒክስ ትኬት አገልግሎት አሰጣጥን በሙከራ ደረጃ ኦንላይን ለማድረግ ከልዩ ባስ አገልግሎት ሰጭ ኦፕሬተሮች ጋር ውይይት ተደረገ

ሰኔ 4/2018 ዓ.ም (ትሎሚ):- የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ ክቡር አቶ በርኦ ሀሰን የህዝብ የትራንስፖርት ትኬት አገልግሎት አሰጣጥን በሙከራ ደረጃ ኦንላይን ለማድረግ ከልዩ ባስ አገልግሎት ሰጭ ኦፕሬተር ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የህዝብ ትራንስፖርት ማኔጅመንት ሲስተም በሙከራ ደረጃ በልዩ ባስ አገልግሎት ሰጭዎች ተግባራዊ ሆኖ በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል።

የተዘጋጀው ይህ የህዝብ ትራንስፖርት ማኔጅመንት ሲስተም ተሳታፊው ባለበት ቦታ ሆኖ ትኬት መቁረጥ የሚያስችል፣ ታሪፍ የማወቅ፣ የመስመሩን መነሻ እና መድረሻ የመለየት፣ የተሽከርካሪውን መነሻ ቦታ ቀን ስዓት መለየት የሚያስችል በመሆኑ በቅርቡ በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃዎችን ለማግኘት👇👇👇

በድረ ገጽ፡

www.motl.gov.et

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/EthiopianTransport?mibextid=ZbWKwL

በቴሌግራም:
https://t.me/ministryoftransportethiopia

በዩቲዩብ

https://youtube.com/

በትዊተር

https://x.com/MoTLogestics

በቲክቶክ

https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZS-93fuvA1twuuy

11/06/2026

የአዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ስርጭትን በትዕግሥት ስለጠበቃችሁ ከልብ እናመሰግናለን!

ዛሬ የአዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ስርጭት በአዲስ አበባ በይፋ ተጀምሯል።

አገልግሎቱ ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ተደራሽ እንዲሆን የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች ተደርገዋል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Addis Ababa
1238