አዲስ ከተማ ወረዳ 11 ብልፅግና ፓርቲ -Addis 11 Prosperity

አዲስ ከተማ ወረዳ 11 ብልፅግና ፓርቲ -Addis 11 Prosperity

Share

Building a Prosperous Ethiopia. 🇪🇹
የበለፀገች ኢትዮጵያን መገንባት!

የአዲስ ከተማ ወረዳ 11 የብልፅግና ፓርቲ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ!

Official page for Addis Ketema Woreda 11 Prosperity Party.

12/06/2026

ለዉጤት የመትጋት ለህዝብ የመታመን ጉዞ :-በአዲስ ከተማ

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በ 2018 በጀት ዓመት ባለፉት 11 ወራት ህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል::

የአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እና የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ የ 1 መሶብ ማዕከል በማስመረቅ ወደ ተግባር ያስገባ ሲሆን በሰው ተኮር ተግባር የህብረተሰቡን የቤት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የበጎነት መንደር የቤት ግንባታ አስገንብቶ ለነዋሪዎች ማስረከብ ተችሏል ከዚህም በተጨማሪ በ ነባር መጠርያ ቅጠል ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አዲስ የቤት ግንባታማስጀመር ተችሏል::

በክፍለ ከተማ የቆዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ የ 18 መብራት ሃይል መንገድ ግንባታ ማስጀመር ተችሏል:: የ አዲስ እኮ ፓርክ ተመርቆ ወደ ተግባር ማስገባት ሌላኛው ስኬት ነው ።

ከተቋም ግንባታ ሥራ አኳያ G+4 ህንፃ አስገንብቶ ሥራ ማስጀመር ችሏል::

Photos from አዲስ ከተማ ወረዳ 11 ብልፅግና ፓርቲ -Addis 11 Prosperity's post 11/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች ፤ አሸንፋለች!

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የተያዙ መንትያ ግቦችን ለማሳካት የተከናወኑ ስራዎችን የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት በመገምገም በቀጣይ ተግባራት ላይ ተግባቦት ፈጥሯል።

በግምገማ መድረኩ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ህዝባችን ባራመደው ግልፅ አቋም፣ ከሌሊት እስከ ሌሊት በፅናት ድምፁን በመስጠት ባስተላለፈው ተግባራዊ መልዕክት ኢትዮጵያ አሸናፊ መሆኗን ተገልጿል።

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ፣ ጤናማ ፣ ገለልተኛ እና ሰላማዊ እንዲሆን የብልፅግና ፓርቲ አመራርና አባላት የምርጫ ስነ ምግባርን ባከበረ መልኩ አበረታች እንቅስቃሴዎችን ማድረጋቸውን በግምገማዉ ተመላክቷል።

የሚዲያ ተቋማት ሀሳቦችን በሚዛናዊነትና በፍትሀዊነት በማስተናገድ ፣ የፀጥታ አካላት ገለልተኛ ሚናቸውን በመወጣት፣ ሲቪል ማህበራት ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የድርሻቸውን በማበርከት ጉልህ ሚናቸውን መወጣታቸው ዴሞክራሲያዊነት ስርዓት ግንባታ ቁልፍ ሚና መጫወታቸዉ በመድረኩ ተገምግሟል።

ከነበሩ ጥንካሬዎች በመማር ፣ ጉድለቶችን በማረም ፣ ሁሉንም አቅሞች በማስተባበር የህዝባችንን ጥያቄዎች በመመለስ፣ በአገልጋይነት መንፈስ እርካታውን በማሳደግ ህዝባችንን ለመካስ ብርቱ ርብርብ መደረግ እንደሚገባ የግምገማ መድረኩን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰዉ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ ዶክተር ጀማሉ ጀምበር ገልፀዋል ።

የአዲስ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ የተከበሩ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ በተደረገው አበረታች ርብርብ ዓለም አቀፍ እውቅና ጭምር የተቸረው ስኬት መመዝገቡን አውስተዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ደመላሽ ጎሳ ባቀረቡት የውይይት መነሻ ሰነድ ብልፅግና ፓርቲ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መንትያ ግቦችን አስቀምጦ ፣ የምርጫ ቦርድን ህጎች ፣ አዋጅና መመሪያዎች ተከትሎ ፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በትብብር እና በፉክክር በመስራት ከቅድመ ምርጫው ጀምሮ ለምርጫው ሰላማዊነትና ዴሞክራሲያዊነት የድርሻውን መወጣቱን አብራርተዋል።

#አዲስ11

Photos from Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ's post 10/06/2026
Photos from አዲስ ከተማ ወረዳ 11 ብልፅግና ፓርቲ -Addis 11 Prosperity's post 09/06/2026

!

የብልፅግና ፓርቲ ጉዞ ታላላቅ ራእዮችን በመንደፍ እንዲሁም ራእዮች ወደ መሬት አውርዶ የህዝባችንን ህይወት በመቀየር ላይ የተመሰረተ ነው ። ይህንን ሀገራዊ አደራ በስኬት ለመወጣት ደግሞ ከመቼውም ጊዜ በላይ የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነትን ማጠናከር እና የመፈፀም አቅማችንን ማሳደግ ወሳኝነቱ የላቀ ነው።

የፓርቲያችንን የመፈፀም አቅም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በእያንዳንዱ መዋቅር ዘንድ የፓርቲያችንን ራእይ እና ግቦች በአግባቡ ለመፈፀም ራስን በዕውቀት፣ በክህሎትና በቴክኖሎጂ ማሳደግ እንዲሁም በተሰጠው የኃላፊነት ዘርፍ ላይ ግንባር ቀደም በመሆን ኃላፊነቱን መወጣት ሲችል ነው ።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በዛሬው እለት''በታደሰ ገጽታ አዲስን ወደ ከፍታ'' በሚል መሪ ቃል የ 2018 በጀት ዓመት የ 11 ወራት መደበኛ የውስጠ ፓርቲ ተግባር አፈፃፀም በመገምገም የቀሪ 1 ወር እቅድ ላይ የግምገማ መድረክ አካሄደ::
#አዲስ11

Photos from አዲስ ከተማ ወረዳ 11 ብልፅግና ፓርቲ -Addis 11 Prosperity's post 06/06/2026

ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

በ 7 ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሀገራችን ኢትዮጵያ እና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓታችን አሸንፈዋል! የምርጫው ውጤት ምንም ይሁን ምን፣ ሂደቱ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ሆኖ መጠናቀቁ ለሀገራችን የፖለቲካ ብስለትና የዲሞክራሲ ጉዞ ታላቅ ታሪካዊ እርምጃ ሆኖ ተመዝግቧል።

በዚህ ታሪካዊ ቀን ሕዝባችን በከፍተኛ ትዕግሥት፣ ሥልጣኔና ሰላማዊ መንገድ ድምፁን በመስጠት የሀገሩን ዕድል በራሱ በመወሰኑ ክብርና ምስጋና ይገባዋል።

የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎች ለሂደቱ መሳካት ትልቅ ቁርጠኝነት አሳይተዋል።

ዛሬ የ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የ 11 ወር መደበኛ ተግባራት አፈፃፀም እና የ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ተግባራት አፈፃፀም ገምግሟ::

ኢትዮጵያ መርጣለች!

05/06/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርሲ ዞን በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገልጸዋል - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
******************

‎በኦነግ ሸኔ ዐማጽያን በንጹሐን ዜጎች ላይ በተለይም በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ዒላማ ተደርገው የተፈጸሙ ጥቃቶችን ተከትሎ፤ የቤተሰብ እና የወዳጆቻቸውን ሕይወት ላጡ፣ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እና ቤት ንብረታቸው ለወደመባቸው በአርሲ ዞን ለሚገኙ ወገኖቻችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ መንግሥት ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ይገልጻሉ ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ።

ጽ/ቤቱ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ እነዚህ ጥቃቶች የሀገራችንን ብሔራዊ ዕድገት ለማደናቀፍ ከሚሹ አካላት፣ በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ አማፂ ቡድኖች እና ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ጥላቻ ካላቸው የውጭ ኃይሎች ጋር በጥምረት የተከናወኑ ሲሆኑ፤ ዓላማቸውም በኢትዮጵያ አለመረጋጋትን እና የምርጫ መስተጓጎልን ለመፍጠር ሲደረግ የነበረው የጥፋት ውጥን ተከታይ ነው ብሏል።

መንግሥት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር ፍትሐዊ እና አሳታፊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀ ልዩ ትኩረት እና ዝግጅት በማድረግ በቁርጠኝነት ሲሠራ መቆየቱን መግለጫው አስታውሷል።

በሌላ በኩል የጥፋት ኃይሎች ከባዕዳን ጋር ‘ፅምዶ' የሚል ቁርኝት በመፍጠር ዕኩይ ዓላማቸውን ለማሳካት ሰፊ የጥፋት ዝግጅት ሲያድርጉ ቆይተዋል፣ ሀገራዊ ምርጫው እንዳይከናወን ሰፊ ርብርብ አድርገዋል።

በተጨባጭም በቅድመ ምርጫ እና በምርጫ ወቅት የዜጎችን የመምረጥ መብት እና ነጻነት ለመጋፋትና ለማደናቀፍ አለን የሚሉትን የጥፋት እጅ ዘርግተዋል።

‎እነዚህ የጠላት ኃይሎች በመደጋገፍና በመናበብ ዐመፅና ሁከት ለማነሳሳት፣ ከተሞችን በሽብር ጥቃት ለማወክ፣ በመንገዶች የደፈጣ ጥቃት በመፈጸም እንቅስቃሴ ለመገደብ እና በተወሰኑ አካባቢዎች ዒላማ አድርገው ነጥለው ለማጥቃት ተንቀሳቅሰዋል።

እንደ ማሳያ የጦር መሣሪያ፣ ተተኳሾችን እና ሌሎች ሎጀስቲክሶችን በድጋፍ በማቅረብ በደቡባዊ ትግራይ በሚገኙ አዋሳኝ የአማራ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ላይ ትንኮሳ ፈጽመዋል፤ በአማራ ክልል ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን እና ወልድያ ከተሞችን ጨምሮ በክልሉ ዋና ዋና ከተሞች እና ሲቪሎች ላይ ዒላማ በማድረግ የሽብር ዝግጅት አድርገዋል፤ በአዲስ አበባ ከተማ ባደራጇቸው የኅቡዕ ሴሎች አማካኝነት በተመረጡ አከባቢዎች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ተንቀሳቅሰዋል፤ ቢሆንም ይህ የጥፋት ሴራ እና ድርጊት እንዲከሽፍ ማድረግ ተችሏል።

‎በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል የሸኔ ሽብር ቡድን ከጽንፈኛው ፋኖ ታጣቂ ቡድን ጋር በመናበብ በአንዳንድ አካባቢዎች መንገዶችን በመዝጋት እንቅስቃሴ ለማስቆምና ለማስተጓጎል የተንቀሳቀሰ ቢሆንም በጸጥታ ኃይሉ በተወሰደበት የተጠናከረ እርምጃ ፍላጎቱን ማሳካት አልቻለም።

ቡድኑ በፀጥታ ኃይሉ የተወሰደበትን ርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ እና ፍላጎቱን ማሳካት ባለመቻሉ ስስ ዒላማዎች ላይ ያተኮረ ርምጃ በመውሰድ የሃይማኖት እና የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ በማለም በአርሲ ዞን አሰኮ እና አካባቢው ጥቃት በመፈጸም ሁሉን ዓይነት የጥፋት ርብርብ ያደረገ ቢሆንም፤ ሁኔታውን በመቆጣጠር የፀጥታ ኃይላችን በእነዚህ ኃይሎች ላይ የተቀናጀ ርምጃ እየወሰደ ይገኛል።

መንግሥት መሰል ሥጋቶችን በንቃት በመከታተል ላይ ሲሆን፣ በምርጫው ወቅትም በብዙ የሀገራችን አካባቢዎች የተቀነባበሩ ተመሳሳይ ዕቅዶችን በስኬት ማክሸፍ ችሏል።

በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን፤ ፍርሃትና ክፍፍልን ከሚያጎሉ የሚዲያ ዘመቻዎች ጋር በማስተሣሠር የተቀነባበረው ይህ እኩይ ተግባር፤ በመንግሥት የደኅንነት መዋቅርና ኦፕሬሽኖች አማካኝነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲስተጓጎል ተደርጓል።

ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ ክፍፍልን ለመዝራት የኃይል ጥቃትን እና ውድመትን እንደ መሣሪያ የሚጠቀሙ አካላት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ በግልጽ ሊወገዙ ይገባል።

መሰል ተግባራት በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የወደፊት ዕድል እንደሌላቸው ለማሳየት የተቀናጀ ብሔራዊ ምላሽ በመስጠት ወሳኝ ርምጃችን ይቀጥላል።

‎በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ አካላት፣ ድርጊታቸውን ምክንያታዊ ለማስመሰል ምንም ዓይነት የፖለቲካ ንግግር ቢጠቀሙ፤ ወሳኝ ዓላማን እያሳኩ ሳይሆን ወንጀል እየፈጸሙ ነው።

የፖለቲካ ቅሬታዎች በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት፣ በብሔራዊ ምክክር ሂደት እና በዴሞክራሲያዊ ተቋማት አማካኝነት መፍትሔ ሊያገኙ የሚችሉ እና ሊያገኙ የሚገባቸው ናቸው ብሏል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በመግለጫው።

01/06/2026

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-

• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

Uummanni Itoophiyaa dinqisiisaafi ajaa'ibsiisaadha! Uumaa malee uummata keenya guutummaan beekuufi gamaaggamuu kan danda'u eenyu? Aadaa gabbataa, uummata biyya jaallatuufi fedhiisaa waloo eeguu danda'u ta'uusaa filannoo baranaatiin irradeebiidhaan addunyaatti agarsiiseera. Guyyaa seena-qabeessa har'aatiin:
- Qorriifi dukkanni halkani kan isaani hin sodaachifne,
- Aduun saafaafi bokkaan tasaa kan isaan jilbeenfachiifne,
- Cidhi, gaddi, da'umsiifi taateewwan hawaasummaa kanbiroon kan isaan dhorkine,
- Hiriironni dhedheeroon kan isaan hin nuffisiifne,
- Qaama miidhamtummaan sagalee kennuuf kan isaan hin daangessine,
- Dhukkubniifi dullumni abdii biyyaa arguuf kan isaan hin dhowwine,
- Daa'imasaanii kichuu bor biyya dhaalu baatanii filuun kan isaan hin dadhabsiifne
- Hundumaa caalaa lammiilee iyyiifi sodaachiifni diinaa isaan hin dhaabsifne,
Ciminni bu'aa bayii hedduu keessatti agarsiiftan gatii diimokraasiifi jiraachuu biyyatiif kanfalame waan ta'eef galata guddaatu malaafi.

Uummata kana tajaajiluun carroomuu waan ta'eef filatamtoonni warra isin kabajan kabajjanii uummata sirna diimookraasiif gatii baase kana qulqullummadhaan tajaajiluuf isin haa gahu.

The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.

On this historic day:

* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;

The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.

It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.

Photos from አዲስ ከተማ ወረዳ 11 ብልፅግና ፓርቲ -Addis 11 Prosperity's post 01/06/2026

ድምፃችንን ሳንሰጥ ወደ ቤት አንገባም
:-የአዲስ ከተማ ነዋሪዎች
#አዲስ11

01/06/2026

በድጋሚ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት ላይ እንደነበር ይታወቃል። ቦርዱ በሥምሪት ላይ ያለው የክትትል ቡድኑ ያቀረበለትን ሪፖርት ተመልክቶ የሚከተለውን ወሥኗል።

በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49(4) መሠረት ቦርዱ የምርጫው ነፃና ፍትሐዊነት ይበልጥ ያሰፍናል ብሎ ካመነ የድምፅ መስጫ ሰዓቱን ሊያራዝም እንደሚችል በግልጽ ይደነግጋል። በመሆኑም የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ ዕኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን ቦርዱ ያሳውቃል።

ማሳሰቢያ: የተመዘገቡ መራጮች መርጠው የተጠናቀቁባቸው ጣቢያዎች ላይ አስፈጻሚዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደቱን እንዲያከናውኑ ቦርዱ ያስታውሳል።
#አዲስ11

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Address


Philipos Road
Addis Ababa