Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency

Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency

Share

C R R S A - Civil Registration and Residency Service Agency - የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ

Photos from Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency's post 24/06/2026

የመሰረተ ልማት የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የበጀት አመቱን የስራ አፈጻጸም የመስክ ምልከታ አደረገ

CRRSA: ሰኔ 16/2018ዓ.ም
አዲስ አበባ

የመሠረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የተከናወኑ የበጀት ዓመቱን የሥራ አፈጻጸሞች ለመገምገም የሚያስችል የመስክ ምልከታ ማድረጉ አሳወቀ፡፡

የመሰረተ ልማት የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመስክ ምልከታው ኤጀንሲው በበጀት አመቱ ያቀዳቸውን እቅዶች በስራ ላይ ማዋሉንና ለተገልጋዩ ማህበረሰብ እየሰጠ ያለውን የአገልግሎት ጥራትና እያጋጠሙ ያሉ ማነቆዎችን ምልከታ ለማድረግ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥ በዘመናዊ የዲጂታል አሰራር በማስፋፋት ረገድ የተጀመሩ ስራዎች ለተገልጋዩ ህዝብ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እያገዙ መሆኑ የጠቀሱት ቋሚ ኮሚቴው የዜጎችን መረጃ በአግባቡና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ለመያዝ የተከናወኑ ተግባራት እናየዲጂታል አሰራርን በማስፋፋት ረገድ የተጀመሩ ስራዎች ለተገልጋዩ ህዝብ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት አበረታች መሆናቸው ገልጸዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በኤጀንሲው የተመዘገቡ ጥንካሬዎችና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ጉዞ ከማስፈጸም ረገድ ተቋሙ ግንባር ቀደም መሆኑን በማድነቅ ቀልጣፋ ና ፍትሀዊ አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ የሚታዩ ክፍተቶችና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): https://www.tiktok.com/

ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/

ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

ፖስታ ሳ.ቁ (Box No)፡ 20320

Photos from Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency's post 23/06/2026

የልደትና የሞት ማሳወቂያ አገልግሎትን በዲጂታል ለማከናወን የሚያስችል የሲስተም ስልጠና በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተሰጠ

CRRSA: ሰኔ 16/2018ዓ.ም

አዲስ አበባ

የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ለሚኒሊክ ሆስፒታል ዶክተሮች እና አዋላጅ ነርሶች በሲስተም የኩነቶች ማሳወቂያ ላይ ስልጠና መስጠቱን አስታውቋል፡፡

የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ የልደትና የሞት ማሳወቂያ ወረቀት (Notification Paper) አሰጣጥን ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችል ስልጠና ለዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለዶክተሮችና ለአዋላጅ ነርሶች መስጠት ጀምሯል።

ቀደም ሲል በሆስፒታሉ ውስጥ የሚከሰቱ የልደትና የሞት ኩነቶች ምዝገባ በወረቀት (Manual) ይከናወን የነበረ ሲሆን ይህንን አሰራር ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ፈጣንና ተደራሽ ለማድረግ አሁን ላይ ኩነቱ እንደተከሰተ ወዲያውኑ በሲስተም ማሳወቅ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተዘርግቷል።

የተሰጠው ስልጠናም የህክምና ባለሙያዎቹ ይህንን አዲስ የዲጂታል አሰራር በአግባቡ ተገንዝበው ስራ ላይ እንዲያውሉ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

ዶክተሮች እና አዋላጅ ነርሶች በሙሉ ተደራሽ ለማድረግ የታቀደው ይህ ስልጠና በሆስፒታሉ ደረጃ በተከታታይ አምስት ቀናት እንደሚሰጥ ታውቋል።

ኤጀንሲው የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና መረጃዎችን በዲጂታል መንገድ ለማደራጀት የጀመረው ይህ በሲስተም የልደትና ሞት ማሳወቂያ ወረቀት አሰጣጥ ሂደት፣ በቀጣይም በሌሎች በተመረጡ ሆስፒታሎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃ፣ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን እንዲሁም የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ይከታተሉ
ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et
ፌስቡክ (Facebook):https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686
ቴሌግራም (Telegram):https://t.me/addisvaitalpress
ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ (TikTok):https://www.tiktok.com/
ኢንስታግራም (Instagram)https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/
ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

Photos from Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency's post 23/06/2026

ኤጀንሲው የልደት ምዝገባን ተደራሽ ለማድረግ የ90 ቀናት የንቅናቄ መድረክ አካሄደ

CRRSA: ሰኔ 16/2018ዓ.ም
አዲስ አበባ

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ‘’የልደት ምዝገባ እና ሰርቲፊኬት የእያንዳንዱ ህፃን መብት’’ ነው በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ የህፃናት ማቆያ ማዕከላት ባለቤቶች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡት እና የንቅናቄ መድረኩን የመሩት የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ የህፃናት የልደት ምዝገባ እና ሰርቲፊኬት የህፃናት መብት መሆኑን ገልፀው በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ሁሉም ህፃናት የልደት ምስክር ወረቀት እንዲኖራቸው በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የወሳኝ ኩነት ምዝገባን ውጤታማ ማድረግ እና ማሳካት የሚቻለው ሁሉም አካላት ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ነው ያሉት አቶ ጥጋቡ የንቅናቄ መድረኩ ዓላማም በመንግስት፣በግል እንዲሁም በመያድ በህፃናት ማቆያ ለሚገኙ ህፃናት መቶ ፐርሰንት በመመዝገብ የልደት ምስክር ወረቀት እንዲኖራቸው ማስቻል መሆኑን ገልፀው የልደት ምዝገባ ማከናወን ለግለሰቦች ህጋዊ ከለላ የማግኘት መብትን የሚሰጥ ሲሆን ለአስተዳደራዊ ጉዳዮች እና አስታስቲካዊ መረጃዎች ምንጭ በመሆን እንደሚያገለግልም አስረድተዋል፡፡

በተዘጋጀው የ90 ቀናት የንቅናቄ መድረክ ከ4መቶ በላይ የህፃናት ማቆያ ባለቤቶች እና ከ10 በላይ የህፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ኃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ጥሩ ግንዘቤ እንደተፈጠረላቸው ገልፀው ከኤጀንሲው ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሀሳቦች እና አስተያየቶች የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ ምላሽና ማብራሪያ የሠጡ ሲሆን በቀጣይም በትምህርት ተቋማትና በዘላቂ ማረፊያዎች የንቅናቄ መድረኩ እንደሚቀጥል ተነግሯል::

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): https://www.tiktok.com/

ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/

ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

ፖስታ ሳ.ቁ (Box No)፡ 20320

22/06/2026
Photos from Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency's post 22/06/2026

የኦንላይን አገልግሎት ለሚሰጡ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

CRRSA: ሰኔ 15/2018ዓ.ም
አዲስ አበባ

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ወደ ስራ ባስገባው የኦንላይን አገልግሎት መተግበሪያ (Online Application Portal) ዙሪያ ለባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ተቋሙ ላለፉት ዓመታት ቀጣይነት ያለው ሪፎርም በማድረግ፣ አሰራሩን በዘመናዊ መንገድ፣ በፍጥነት እና በግልጸኝነት ላይ የተመሰረተ ማድረጉን ገልጸዋል።አዲሱ የኦንላይን መተግበሪያም የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በቤታቸው ወይም ባሉበት ቦታ ሆነው በቀላሉ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸው በመሆኑ የህዝቡን ጊዜ፣ ጉልበት እና ወጪ በከፍተኛ ደረጃ የሚቆጥብ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የነዋሪዎች፣የህትመት እና የኢንፎርሜሸን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናውን የሰጡት በኤጀንሲው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ባለሙያ አቶ ዮናስ አለሙ የለማው የኦንላይን መተግበሪያ ከነዋሪዎች በኦንላይን ለተጠየቁ መረጃዎች፣በፍጥነት ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ያስረዱ ሲሆን ይህም ኤጀንሲው የያዘውን ተደራሽ እና ፈጣን አገልግሎት የመሰጠት ራዕይ እውን እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

ኤጀንሲው የቴክኖሎጂ ልማት በማሳደግ ለከተማዋ ነዋሪዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ፈጣን ተደራሽ እና ምቹ ለማድረግ የሚያስችለውን አገልግሎት ይበልጥ በማዘመን ነዋሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በእጅ ስልካቸው ወይም በኮምፒውተር አገልግሎት መጠየቅ የሚችሉበት እና የሚስተናገዱበት የኦንላይን አገልግሎት መስጫ መተግበሪያ በማልማት ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል፡፡

«አንድ ጊዜ ይመዝገቡ፤ በሁሉም ቦታ ይገልገሉ!»
«REGISTER ONCE ፤SERVE EVERYWHERE!»

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): https://www.tiktok.com/

ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/

ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

ፖስታ ሳ.ቁ (Box No)፡ 20320

Photos from Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency's post 21/06/2026

በአዲስ አበባ የልደትና ሞት ኩነቶችን በዲጂታል ስርዓት ለመመዝገብ የሚያስችለውን የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ

CRRSA:ሰኔ 13/2018ዓ.ም
አዲስ አበባ

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በጤና ተቋማት የሚከሰቱ የልደት እና የሞት ማሳወቂያ የአገልግሎት ስርዓቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን የሚያስችለውን ሲስተም ከጤና ተቋማት የዲጂታል ስርዓት ጋር በማቀናጀት ወደ ሙሉ ትግበራ ለመግባት የሚያስችለውን የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

ኤጀንሲው የዲጂታል ምዝገባ ሥርዓቱን በፓይለት ደረጃ በአራት የተመረጡ የመንግሥት ጤና ተቋማት ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቶችን ቀደም ብሎ ማከናወኑን የሚታወስ ሲሆን በዚህም መሠረት በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የዲጂታል ምዝገባውን ለማስጀመር የሚያስችለውን የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው መክፈቻ መርሃ ግብር የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ የፕሮጀክቱን ዓላማና ተጠቃሚነት በተመለከተ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን የወሳኝ ኩነት ምዝገባን ዲጂታላይዝ ማድረግ ለአገራዊ እቅድ እና ለዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ መሰረት መሆኑን በመጥቀስ ሲስተሙ ከጤና ተቋማት ጋር መተሳሰሩ መረጃዎች በወቅቱ እና በጥራት እንዲመዘገቡ ትልቅ ሚና አለው ሲሉ ተናግረዋል።

የዜጎችን የልደትና የሞት ኩነት በትክክልና በዲጂታል መንገድ መመዝገብ ተራ የአስተዳደር ስራ ሳይሆን የሀገርን ሉዓላዊነትና ደህንነት የሚያረጋግጥ ስትራቴጂካዊ መሳሪያ ነው ያሉት አቶ ጥጋቡ ባለፉት ስርዓታት የተሟላና የተማከለ የመረጃ እጥረት በመኖሩ ምክንያት ለሀገራዊ እቅድ የልማት ተደራሽነትና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ትልቅ ማነቆ የነበረበትን ሁኔታ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የእቅድ ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ የልደትና ሞት ኩነቶችን በወቅቱ መመዝገብ ያለውን ጠቀሜታ አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለሚሰሩ ሚድዋይፎችና ዶክተሮች ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ዳይሬክተሩ የጠቀሱ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ሲስተሙ በሆስፒታሉ የዲጂታል ስርዓት ትግበራ የልደትና ሞት ምዝገባ አገልግሎት በይፋ ሥራ እንደሚጀምር ገልጸዋል።
ዲጂታል ስርአት ትግበራው በአበበች ጎበና፣ በዘውዲቱ እና በጋንዲ ሆስፒታሎች ላይ የሚተገበር በመሆኑ በቀጣይ በ90 ቀናት ውስጥ በከተማው በርካታ ልደትና ሞት በሚከሰትባቸው 50 የጤና ተቋማት ውስጥ ሥርዓቱን ለማስፋፋት እቅድ መያዙን ያስታወቀ ሲሆን በ2019 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሁሉም የጤና ተቋማት ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱ ተገልጿል።

ኤጀንሲው በአዲስ አበባ የሚከሰቱ ወሳኝ ኩነቶችን በተሟላ ሁኔታ ለመመዝገብ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ምድብ ችሎቶች እና በሸሪዓ ፍርድ ቤት የፍቺ፣ የጉዲፈቻ እና የጋብቻ ኩነቶችን በተሟላ ሁኔታ ምዝገባ እያደረገ እንደሚገኝ የሚታወስ ሲሆን በቀጣይም በቤተ እምነት የሚፈጸሙ ጋብቻዎችን በተሟላ ሁኔታ ለመመዝገብ የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል።

በቀጣይም “በአዲስ አበባ የልደት ምስክር ወረቀት የሌለው ሕፃን ሊኖር አይገባም” በሚል መርህ የ90 ቀናት የሕፃናት የልደት ምዝገባ ንቅናቄ በሕፃናት ማቆያዎችና በትምህርት ቤቶች ሊጀመር መሆኑ የገለጹት አቶ ጥጋቡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የሚከሰቱ ወሳኝ ኩነቶችን በወቅቱ በማስመዝገብ የሚገኘውን ጠቀሜታ በመገንዘብ ሕጋዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ እና የተከሰቱ ወሳኝ ኩነቶችን በወቅቱ ማስመዝገብ የሥልጡን ማኅበረሰብ መገለጫ መሆኑን አስገንዝቧል።

በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ፅንሰ ሐሳብ አስፈላጊነትና በአዲስ አበባ ያለው የምዝገባ ሁኔታ እንዲሁም በኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንስቲትዩት የለማው አዲሱ የዲጂታል ሥርዓት ሲስተም ቴክኒካል ስልጠናው ተሰጥቷል።

ስልጠናውም ከቫይታል ስትራቴጂ አጋር ድርጅት ጋር በትብብር እየተሰጠ ሲሆን ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የወሳኝ ኩነት ምዝገባን ከጤና ዘርፍ ጋር በማስተሳሰር በምዝገባ የሚገኘውን መረጃ ለእቅድ፣ ለፖሊሲ እና ለአገልግሎት ልማት ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚያስችል ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): https://www.tiktok.com/

ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/

ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

ፖስታ ሳ.ቁ (Box No)፡ 20320

19/06/2026

«REGISTER ONCE ፤SERVE EVERYWHERE!»
«አንድ ጊዜ ይመዝገቡ፤ በሁሉም ቦታ ይገልገሉ!»

ኤጀንሲዉ አዲስ የአገልግሎት አማራጭ ለተገልጋዮች አቀረበ!

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ለከተማዋ ነዋሪዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ፈጣን ተደራሽ ምቹ ለማድረግ በየጊዜው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ አማራጮችን እና አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት የእርስዎን አገልግሎት ፍላጎት በተሻለ ሁኔታ ለማሟላት፣ አዲስ የአገልግሎት አማራጭ አቅርበናል!

የደንበኞቹን እርካታ ለማሳደግ በሚያደረገው ያላሰለሰ ጥረት የኦንላይን አገልግሎት መስጠት ከሚችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ኤጀንሲው ባሉበት ሆነው በእጅ ስልክዎወይም ኮምፒዉተር በኦንላይን የነዋሪነት መታወቂያዎትን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር እንዲሁም አገልግሎት መጠየቅ የሚችሉበትን ደህረ ገፅ https://portal.aacrrsa.gov.et የአገልግሎት ጥያቄዎችን ማቅረብ እንደሚችሉ እገለፀ፤

አገልግሎት ጥያቄ ለማቅረብ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ባሉበት ሆነው ወረዳ በአካል መቅረብ ሳያስፈልግ ባሉበት ሆነዉ አገልግሎት ጠይቀዉ በፈለጉት ግዜ መጥተዉ መቀበል ይችላሉ፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት

1.የዲጂታል የነዋሪነት መታወቂያ ምዝገባ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ ለምሳሌ፤- (AA0000000001) ያለው.

2. በመቀጠል “ከፋይዳ አገናኝ “ የሚለዉን በመንካት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር ይጠበቃል፤

3.የነዋሪነት መታወቂያ ሲመዘገቡ የሰጡት መረጃ የፋይዳ መታወቂያ ሲመዘገቡ ከሰጡት መረጃ ጋር ልዩነት ካለዉ ትክክለኛ የሆነዉን መርጠዉ ማስረጃዎትን ልከዉ አገልግሎት ያግኙ፤

4. በመጨረሻ መጠየቅ የሚፈልጉትን አገልግሎት መጠየቅ ይችላሉ.

ክቡራን የከተማች ነዋሪዎችና ተገልጋዮች ከላይ የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት የልደት፣የመታወቂያ እድሳት እንዲሁም ያላገባ አገልግሎት ባሉበት ሆነው በኦንላይን አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ በአክብሮት እየገለፅን
በቪዲዮ ከኤጀንሲዉ ዩቲዩብ ገፅ https://www.youtube.com/ ማግኘት ይችላሉ ፡፡

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ!!

«REGISTER ONCE ፤SERVE EVERYWHERE!»

The Agency Introduces a New Service Option for Customers!
The Civil Registration and Residency Service Agency has introduced a new service option to better meet the needs of city residents. To make services faster, more accessible, and more convenient, the agency continuously adopts modern technologies and new working methods. As part of this effort, we are pleased to offer a new service option.

In its ongoing commitment to improving customer satisfaction, the agency has now reached a stage where it can provide services online.

Dear city residents,
The agency would like to inform you that you can now link your residency ID card with your Fayda Digital ID and request services online using your mobile phone or computer from wherever you are through the following https://portal.aacrrsa.gov.et
By meeting the requirements listed below, you can request services without having to visit your local woreda (district) office in person. You may then collect the requested service at a time convenient for you.

Requirements for Accessing the Service

1. Use your Digital Residency ID registration number, for example:
(AA0000000001).

2. Next, click “Link with Fayda” to connect your residency ID with your Fayda Digital ID.
If the information you provided when registering for your residency ID differs from the information you provided when registering for your Fayda ID, select the correct information and upload supporting documents to receive the service.

3. Finally, you can select and request the service you need.
Dear residents and customers,

4. After fulfilling the above requirements, you can access the following services online from wherever you are:
Birth registration-related services
Residency ID renewal services
Single-status (unmarried) certificate services
Video Guide
You can watch instructional videos on the agency’s YouTube channel:
https://www.youtube.com/


Civil Registration and Residency Service Agency.

Photos from Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency's post 19/06/2026

ነዋሪዎች ባሉበት ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበት አዲስ የኦንላይን መተግበሪያ ይፋ ተደረገ

CRRSA: ሰኔ 12/2018ዓ.ም
አዲስ አበባ

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የቴክኖሎጂ ልማት በማሳደግ ለከተማዋ ነዋሪዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ፈጣን ተደራሽ እና ምቹ ለማድረግ የሚያስችለውን አገልግሎት ይበልጥ በማዘመን ነዋሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በእጅ ስልካቸው ወይም በኮምፒውተር አገልግሎት መጠየቅ የሚችሉበት እና የሚስተናገዱበት የኦንላይን አገልግሎት መስጫ መተግበሪያ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የኦን ላይን መተግበሪያው አገልግሎትን በጥራትና በፍጥነት እንዲሁም በግልፀኝነት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ገልፀው ሲስተሙ የእጅ ስልክ እና ኢንተርኔት ያለው ማንኛውንም አገልግሎት ፈላጊ የከተማው ነዋሪ መጠየቅ የሚያስችልበት ስርዓት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የኦን ላይን መተግበሪያው በከተማችን የሚገኙ አቅመ ደካሞች እና የአካል ጉዳተኞች እንግልት የሚያስቀር ተግባራዊ ለውጥ መሆኑን የተናገሩት ኢንጅነሩ ለግልፅነትና ለተጠያቂነት እንዲሁም ብልሹ አሰራርን በተግባር ያጠፋል ብለዋል፡፡

አዲስ የአገልግሎት ባህል የፈጠርንበት ህዝባችን የሚከበርበት መረጃው የሚጠበቅበት መንግስት በተግባር ወደ ህዝብ የሚቀርብበት ዘመኑን የዋጀ ዲጅታል አገልግሎት መፍጠር ይገባናል ብለዋል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ኤጀንሲው ላለፉት አመታት ሪፎርም እያደረገ ያለ ተቋም መሆኑን በማንሳት በዘመናዊ መንገድ በፍጥነት እና በግልጸኝነት እየሰራ የሚገኝ ተቋም መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን አዲስ የኦንላይን መተግበሪያ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በቤታቸው ሆነው በቀላሉ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል በመሆኑ ጊዜን የሚቆጥብ መሆኑን ተናግረዋል፤

ሀገር በቀል ተቋም በሆነው በኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሲስተሙ የበለጸገ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ አገልግሎቱ ለዜጎች የሚያበረክተው እድል ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የኦን ላይን መተግበሪያ ሲስተሙ ብልሹ አሰራርን፣የወረፋ መብዛትና እንግልት እንዲሁም የመረጃ ጥራት ችግርን የሚያስቀር መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ የጠቀሱ ሲሆን ከተማ መስተዳደሩ ለአገልግሎት አሰጣጥ ልህቀት ያሳየውን ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በማጠቃለያ መርሀ-ግብሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የተጀመረው ስራ ቀጣይነት ያለውና ህብረተሰቡም ሲስተሙን አውቆ በመጠቀም ትክክለኛውን አገልግሎት ማግኘት እንደሚችል አሳስበዋል ፡፡

«አንድ ጊዜ ይመዝገቡ፤ በሁሉም ቦታ ይገልገሉ!»
«REGISTER ONCE ፤SERVE EVERYWHERE!»


ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): https://www.tiktok.com/

ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/

ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

ፖስታ ሳ.ቁ (Box No)፡ 20320

18/06/2026

ፕሬስ ሪሊዝ

ነዋሪዎች ባሉበት ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበትን አዲስ የኦንላይን መተግበሪያ ይፋ ሊያደርግ ነው

CRRSA: ሰኔ 11/2018ዓ.ም
አዲስ አበባ

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የተገልጋዩን ህብረተሰብ ፍላጎት ለማርካት የጀመረውን የሪፎርም ስርዓት በማስቀጠል የተለያዩ የአሰራር ስርዓቶችን በመተግበርና የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ኤጀንሲው የቴክኖሎጂ ልማት በማሳደግ ለከተማዋ ነዋሪዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ፈጣን ተደራሽ እና ምቹ ለማድረግ የሚያስችለውን አገልግሎት ይበልጥ በማዘመን ነዋሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በእጅ ስልካቸው ወይም በኮምፒውተር አገልግሎት መጠየቅ የሚችሉበት እና የሚስተናገዱበት የኦንላይን አገልግሎት መስጫ መተግበሪያ ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑ ተነግሯል፡፡


መርሀ-ግብሩ አዲሱ ገበያ በሚገኘው የኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት በነገው እለት ሰኔ 12/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶችይገኛሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): https://www.tiktok.com/

ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/

ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

ፖስታ ሳ.ቁ (Box No)፡ 20320

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Tunisia Avenue, Gulelle Subcity Woreda 8
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 12:30