15/06/2026
Yeka Wereda 4 Communication የካ ወረዳ 4 ኮሙኒኬሽን
ህዝብና መንግስትን ማገናኘት፣ተጨባጭ ፣ታማኝ ወቅታዊ ፣ ቀላጣፋና ጠቃሚ መረጃዎችን ለህዝብ ማድረስ ነው ። (በቅንነት follow )አድርጉና እናመሰግናለን 🙏
15/06/2026
15/06/2026
የአዲስ አበባን ገፅታ የቀየረውና ለኑሮ ምቹ ያደረገው አረንጓዴ አሻራ
ተፈጥሮ ንጹህ አየርን፣ ዝናብንና ለምለም መሬትን በመለገስ የሰውን ልጅ ህልው ስትደግፍ፣ ሰው ደግሞ እሷን በመንከባከብና በመጠበቅ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።
ይህንኑ የተፈጥሮ ሚዛን ለመጠበቅ በ2011 ዓ.ም የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ አገራዊ ንቅናቄ፤ በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በአካባቢያዊ ገጽታ ላይ ዘርፈ-ብዙ ፋይዳዎችን እያስገኘ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል እንደገለጸው፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት በመዲናዋ 90 ሚሊዮን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ ከተተከሉት ውስጥ 86 ነጥብ 82 በመቶ የሚሆኑት ፅድቀዋል።
ከተተከሉት መካከልም ለምግብ የሚሆኑ የፍራፍሬ ዛፎች እንዲሁም ለባህላዊና ዘመናዊ ሕክምና የሚያገለግሉ ዕፅዋት እንደሚገኙበት ዳይሬክቶሬቱ አክሎ ገልጿል።
ይህ ታላቅ ንቅናቄ የከተማዋን ሥነ-ምህዳር ከማደስ ባለፈ፣ የአካባቢ ብክለትን በመከላከልና የአየር ንብረት መዛባትን በመቋቋም ረገድ የጎላ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ከተማዋን ውብና ለኑሮ ተስማሚ ከማድረግ ባሻገር፣ ለነዋሪዎች ምቹ የሆኑ በርካታ አረንጓዴ የመዝናኛ ቦታዎችን ለመፍጠርም አስችሏል።
በተጨማሪም ለአካባቢው ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፥ ለሀገሪቱ የዲፕሎማሲ ገፅታ ግንባታም ትልቅ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ይህንኑ ስኬት በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል፣ በዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 5 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በከተማዋ ሰፊ የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ናቸው።
የዘንድሮውን ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ በአሁኑ ወቅት የችግኝ ማፍላትና ማጓጓዝ፣ የጉድጓድ ቁፋሮ፣ ሰፊ የሕዝብ ንቅናቄ መፍጠርና ለዘርፉ ባለሙያዎች ሥልጠና የመስጠት ሥራዎች በተሟላ ሁኔታ መከናወናቸውን ዳይሬክቶሬቱ አስታውቋል።
ይህ ታላቅ አገራዊ ንቅናቄ መዲናዋ ነዋሪዎቿን ባሳተፈ መልኩ አረንጓዴና ለኑሮ ተስማሚ የሆነች ከተማ ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ዘላቂ ጥረት ይበልጥ የሚያጠናክረው መሆኑ ተገልጿል።
AMN
14/06/2026
በኑሮ ማረጋጋት ሂደት ውስጥ የቅዳሜና እሁድ ገበያ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው !
ሰኔ/07/2018 የካ ወረዳ 04 ኮሙኒኬሽን
fans Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን Yeka Wereda 4 Communication የካ ወረዳ 4 ኮሙኒኬሽን
14/06/2026
13/06/2026
"ፍትሃዊ ግብይት፣የዋጋ ንረትንና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ውጤታማ የሰንበት ገበያ ምርት ዋጋ፣ አቅርቦትና ጥራት ክትትል ለማህበረሰባችን እርካታ!"
የካ ወረዳ 04፤ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም
የወረዳ 04 ንግድ ፅ/ቤት ኃላፊና ባለሙያዎች ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን በዛሬው ዕለት በሚኒሊክ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የሰንበት ገበያ ላይ የመስክ ምልከታና የክትትል ሥራ አከናውነዋል።
ይህ የጋራ የምልከታ መርሃ-ግብር በዋናነት በሰንበት ገበያው ላይ የሚቀርቡ የምርት ዓይነቶችን አቅርቦት፣ ጥራት፣ዋጋ ተደራሽነትና አጠቃላይ የገበያውን ውጤታማነት ለመገምገም ያለመ ነው።
በተደረገው ምልከታና ክትትል የግብርና ምርቶች በበቂ ሁኔታና በጥራት ለገበያ እየቀረቡ መሆኑን፣
ሸማቹ ማህበረሰብ ያለምንም እንግልት ግብይት እየፈፀመ እንደሚገኝና ምርቶችንም በተመጣጣኝና ፍትሃዊ ዋጋ እያገኘ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።
የወረዳው ንግድ ፅ/ቤት የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስናየገበያ መረጋጋትን ለመፍጠር የተጀመረውን የተቀናጀ የክትትል ናየቁጥጥር አጠናከሮ እንደሚቀጥል የወረዳው ንግድ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ኤሊያስ መንግስቱ ገልፀዋል ።
fans Yeka Wereda 4 Communication የካ ወረዳ 4 ኮሙኒኬሽን Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን Mayor Office of Addis Ababa Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 17:00 |
| Tuesday | 08:00 - 17:00 |
| Wednesday | 08:00 - 17:00 |
| Thursday | 08:00 - 17:00 |
| Friday | 08:00 - 17:00 |
| Saturday | 08:00 - 17:00 |
| Sunday | 08:00 - 17:00 |
