Ministry of Revenues of Ethiopia /የገቢዎች ሚኒስቴር /

Ministry of  Revenues of Ethiopia /የገቢዎች ሚኒስቴር /

Share

The Ministry of Revenues is the body responsible for collecting revenue from domestic taxes.

01/07/2026

የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1142/2018

ሰኔ 24/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር የአሰፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 19(4)እና በፌደራል ታክስ አሰተዳደር አዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

መመሪያውን ለማግኘት ቀጥሎ ያለውን ሊንክ ይጫኑ፡- https://shorturl.at/bKiT4

Photos from Ministry of  Revenues of Ethiopia /የገቢዎች ሚኒስቴር /'s post 30/06/2026

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሻሻለውን የፌደራል ታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ

ሰኔ 23/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

አዋጁን ማሻሻል ያስፈለገው የመረጃ ጥራትን ለማሳደግና በመረጃ መሰብስብ ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ ስህተቶችን ለማረም እንዲሁም ለስህተቱ መነሻ የሆኑ ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማስቻል መሆኑን የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ ገልጸዋል፡፡

ታክስ ከፋይ ተቋማት የተወሰነባቸው የታክስ ክፍያ ላይ ቅሬታ ማሰማት ከፈለጉ ቅሬታቸውን በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት ለሚቋቋመው ገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን አቅርበው መፍትሄ እንዲያገኙ ለማድረግ አዋጁን ለማሻሻል ሌላው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።

አሁን የተሸሻለው ‎አዋጁ አስር ዓመታትን አገልግሎት እየሰጠ መቆየቱን የገለፀው የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተሸሻለው አዋጁ የፌደራል ታክስ አስተዳደር ስርዓትን ይበልጥ የሚያዘምን ይሆናል ብለዋል፡፡

ምክርቤቱ በረቂቅ አዋጁ መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

መረጃው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

Photos from Ministry of  Revenues of Ethiopia /የገቢዎች ሚኒስቴር /'s post 30/06/2026

ታክስን በፍቃደኝነት አሳውቆ መክፈል የውዴታ ግዴታ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል - አቶ ብርሃኑ ሲሳይ የታክስ ጉዳዮች ትምህርት ዳይሬክተር

ሰኔ 23/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በ4ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 301 የሞጁላር ሰልጣኞች ዛሬ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል።

በመድረኩም የታክስ ጉዳዮች ትምህርት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ሲሳይ ታክስ ለሀገር ልማት የጀርባ አጥንት ነው ያሉ ሲሆን ታክስን በፍቃደኝነት አሳውቆ መክፈል ደግሞ የውዴታ ግዴታ መሆኑን መገንዘብ እንደምያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

የልማት በጀት ፍላጎትን ለሟሟላት ዋንኛ የፋይናንስ ምንጭ ታክስ በመሆኑ ዜጎች ታክስን በፍቃደኝነት እንዲከፍሉ የታክስ ሕግጋትን ማስተማር እና ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግም አስረድተዋል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ አነሰተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ኪሮስ ደበሱ በመድረኩ ባሰተላለፉት መልዕክት የሀገር ሉዓላዊነት ሊረጋገጥ የሚችለው ከለጋሽ ሀገራት የኢኮኖሚ ጥገኝነት በመላቀቅ እና በራስ አቅም ማደግ ሲቻል ብቻ ነው ያሉ ሲሆን ይህን ዓላማ ግብ ከዳር ለማድረስ የገቢዎች ሚኒስቴርም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን የታክስ ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

በዚህም የታክስ እና ቀረጥ ማጭበርበርን በመከላከል እንዲሁም የታክስ ፍትሃዊነትን በማስፈን ለንግድና ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን በመፍጠርና ታክስን በፍቃደኝነት የመክፈል ባህል በማዳበር ለሀገር የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሳካት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታክስ ስርዓት ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ገነት ገዳሙ እና የታክስ ትምህርት መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደት አስተባበሪ ወ/ሮ እታገኘሁ ዘለቀ ለመድረኩ ተሳታፊዎች መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁኑ ሰዓት በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ደረጃ 1,251 የሞጁላር ሰልጣኞችን በብቃት ማሰልጠን እና ማስመረቅ ተችሏል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በ4ኛ ዙር የሞጁላር ስልጠና አስጣጥ ስርዓት የተዘጋጁ 13 ሞጁሎችን ሰልጠነው በተገቢው መንገድ ላጠናቀቁ 301 ግብር ከፋዮች የስልጠና ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በተክሉ ኤልያስ
ፎቶ፡- ክፍሌ አዳፍሬ

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

Photos from Ministry of  Revenues of Ethiopia /የገቢዎች ሚኒስቴር /'s post 29/06/2026

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የተለያየ ሀገር ገንዘብ በቁጥጥር ስር ዋለ

ሰኔ 22/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በጉምሩክ ኮሚሽን በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የተለያየ ሀገር ገንዘብ በቊጥጥር ስር ውሏል ።

በቶጎውጫሌ ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ በሻንጣ ውስጥ ተቀናንሶ በተለያየ ቦታ ተደብቆ ወደ ጎረቤት ሀገር ሊያልፍ የነበረ 40,030 ዩሮ፣ 1,520 የአሜሪካን ዶላር እና 220 የቱርክ ገንዘብ በቊጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረው ገንዘብ የተያዘው በጣቢያው የጉምሩክ ባለሙያዎች እና አመራሮች እንዲሁም በፌዴራል ፖሊስ አባላት ሲሆን አንድ ተጠርጣሪም በቊጥጥር ስር በማዋል ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል እንዲተላለፍ ተደርጓል።

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ ለጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ፣ ለቶጎውጫሌ ጉምሩክ ኬላ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ለፌደራል ፖሊስ አባላት ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

#Season1_Episode_8 የኢ-ክሊራንስ ስርዓት ያመጣው ለውጥ 27/06/2026



ሰኔ 20/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

#Season1_Episode_8 የኢ-ክሊራንስ ስርዓት ያመጣው ለውጥ ሰኔ 19/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ኮንትሮባንድን በቴክኖሎጂ! 26/06/2026

ኮንትሮባንድን በቴክኖሎጂ!

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

ኮንትሮባንድን በቴክኖሎጂ! ኮንትሮባንድ ቁጥጥር በደወሌ አና ሶማሌላንድ

Photos from Ministry of  Revenues of Ethiopia /የገቢዎች ሚኒስቴር /'s post 26/06/2026

በዜጎች ዘንድ የታክስ ሞራልን ለመገንባትና የሕግ ተገዢነት ባህልን ለማሳደግ ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በዜጎች ዘንድ የታክስ ሞራልን ለመገንባትና የሕግ ተገዢነት ባህልን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀውን የ2018 በጀት ዓመት የታክስና ጉምሩክ ሕጎች ሥልጠና በከፍተኛ ትጋት የተከታተሉ የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የምዘና ፈተናውን በብቃት አጠናቀው በዛሬው ዕለት በደማቅ ሁኔታ ተመርቀዋል።

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን በጋራ ባዘጋጁት በዚህ ታላቅ ሀገራዊ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤ ባስተላለፉት መልዕክት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን በጋራ በመሆን፣ መጪው ትውልድ በታክስና ጉምሩክ ሕጎች ላይ በቂ ዕውቀትና ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግና በቀጣይም የማኅበረሰቡን የሕግ ተገዢነት ባህል ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የዛሬ ተማሪዎች የነገ ሀገር ተረካቢዎች፣ መሪዎችና የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ነጋዴዎች በመሆናቸው የታክስና ጉምሩክ ሕጎችን ጠንቅቀው ማወቃቸው ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትሯ አክለውም በአሁኑ ወቅት በርካታ የዓለም ሀገራት ትኩረታቸውን ከቅጣት ወደ ማስተማር እያዞሩ መሆኑን ጠቅሰው፣ የታክስ ትምህርት መስጠት የአንድ ወቅት ዘመቻ ሳይሆን፣ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ዋናውና መሠረታዊ ስትራቴጂ መሆኑን አብራርተዋል። ይህ በዜጎች ላይ በትምህርት የሚገነባው የታክስ ሞራል ለሕግ ማስከበር የሚወጣውን አላስፈላጊ ወጪና እንግልት በእጅጉ እንደሚቀንስም አስገንዝበዋል።

አያይዘውም ሥልጠናው ስኬት በጎ ፈቃዳቸውን ለሰጡ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች፣ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች በሙሉ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።

የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዝዘዉ ጫኔ በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ ይህ ሀገራዊ አጋርነት ይበልጥ ተቋማዊና ዘላቂ እንዲሆን በቀጣይ ሥራው ካሪኩለም ተቀርጾለት እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት የሚሰጥበትን መንገድ ከዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ም/ኮሚሽነሩ አክለውም፣ የእለቱ ተመራቂዎች ወደ ማህበረሰቡ በሚቀላቀሉበት ወቅት በታክስ እና ጉምሩክ ጉዳዮች ላይ ያገኙትን እውቀት በመጠቀም ሌሎችን የማሳወቅ እንዲሁም የራሳቸውን ግብር በተገቢው ልክ ከመክፈል ባለፈ በታክስ ላይ የሚፈጸሙ ሕገወጥ ድርጊቶችን በመከላከል ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የሥልጠናውን ዝግጅት፣ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን እና የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያሳይ ዝርዝር ሪፖርት በጉምሩክ ኮሚሽን የደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ዳይሬክተር አቶ ሰኚ አሰፋ በቀረበበት ወቅት ይህ ሥልጠና በየዓመቱ እድገት እያሳየ እንደመጣ እና ለዚህም ተቋማቱ ለትውልድ ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየ መሆኑ ተመላክቷል።

በቀረበው ሪፖርትም ሥልጠናው መሰጠት በጀመረበት በ2016 በጀት ዓመት 4 ዩኒቨርሲቲዎች እና 200 ተማሪዎች ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ዛሬ ላይ ይህ ቁጥር ከፍተኛ እድገት አሳይቶ በ2018 በጀት ዓመት ዩኒቨርሲቲዎችን ቁጥር ወደ 16፣ የተመራቂዎችን ቁጥር ደግሞ ወደ 1,200 ማሳደግ ተችሏል።

በእለቱ በስልጠናው የላቀ አፈጻጸም በማሳየት ከ1ኛ እስከ 6ኛ ደረጃ ይዘው ላጠናቀቁ ተማሪዎች እንዲሁም ለዚህ ሀገራዊ ፕሮግራም ስኬትና ከፍተኛ አጋርነት ላሳዩት ዩኒቨርሲቲዎች ተገቢው ዕውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷል።

በተጨማሪም ባጋጠማት የአካል ጉዳት ሳትበገር ሥልጠናውን በከፍተኛ ጽናትና ስኬት በከፍተኛ ውጤት ያጠናቀቀችው እጩ ተመራቂ ተማሪ ሊዲያ አለማየሁ ልዩ ሽልማትና እውቅና ተሰጥቷል።

በመድረኩ የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክብርት ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ፣ የኢ-ዳታ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ ዳዊት ውብሸት፣ የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ አዝዘዉ ጫኔ፣ የዩኒቨርሲቲ የሥራ ኃላፊዎች፤ እንዲሁም የሁለቱም ተቋማት ዳይሬክተሮችና ሥራ አስኪያጆች ተገኝተዋል።

በበኃይሉ ሽመልስ
ፎቶ:- ክፍሌ አዳፍሬ

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

Photos from Ministry of  Revenues of Ethiopia /የገቢዎች ሚኒስቴር /'s post 25/06/2026

H.E. Minister of Revenues Received Austrian Ambassador to Ethiopia and Austrian Delegation

June,25/2026 (Ministry of Revenues)

H.E. Aynalem Nigussie, Minister of Revenues, received a delegation led by H.E. Dr. Simone Knapp, Ambassador of the Republic of Austria to Ethiopia.

During the meeting, H.E. the Minister highlighted the longstanding friendship and cooperation between Ethiopia and Austria, noting that the relationship has continued to grow through dialogue, development cooperation, trade, investment, and institutional exchanges.

The Minister stated that Ethiopia is implementing significant economic reforms aimed at building a stronger, more competitive, and investment friendly economy. She noted that these reforms are creating new opportunities for partnership and cooperation.

H.E. Aynalem Nigussie further highlighted the Ministry of Revenue’s ongoing modernization agenda, which focuses on digital transformation, modernization of revenue administration, expansion of digital taxpayer services, strengthening tax compliance, and building a modern tax system that supports economic growth while improving services to taxpayers.

H.E. Dr. Simone Knapp reaffirmed Austria’s commitment to strengthening cooperation with Ethiopia and noted that Austria is keen to expand collaboration in digitalization, public sector modernization, and other areas of mutual interest.

The two sides exchanged views on opportunities for future cooperation, particularly in digital transformation, tax administration modernization, knowledge sharing, and institutional capacity building. Also they expressed their commitment to strengthening the longstanding partnership between Ethiopia and Austria through continued dialogue and practical cooperation.

At the occasion-the State Ministers of the Ministry of Revenues attended.

By:- Shimelis Sisay
Photo:- Kifle Adafre

25/06/2026

«ገቢ ለልማት» ጋዜጣ

ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም

ውድ የገቢ ለልማት ጋዜጣ አንባቢዎች፤ እንደተለመደው «ገቢ ለልማት» ጋዜጣ ቁጥር 196 ብዙ ጠቃሚ መልዕክቶችን ይዞ ቀርቧል፡፡ ያንብቡት ብዙ ቁም ነገር ይገበዩበታል፡፡

የተከበራችሁ የጋዜጣችን አንባቢዎች በገቢ ለልማት ቁጥር 197 ይዘን እንድንቀርብ የምትፈልጉት ርዕሰ ጉዳይ ካለ በ011-617-84 90 (2133) ማሳወቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ጋዜጣውን ይህንን ሊንክ በመጫን አውርደው ያንብቡ፡- https://t.me/MoREthiopiaOfficial/9822

Photos from Ministry of  Revenues of Ethiopia /የገቢዎች ሚኒስቴር /'s post 24/06/2026

የሞጁላር ስልጠና የታክስ ህግ ተገዥነትን በማጎልበት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለጸ

ሰኔ 17/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር መካከለኛ ቁጥር 1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፣ 4ኛው ዙር የሞጁላር ስልጠና ያጠናቀቁ 192 ግብር ከፋዮችን በዛሬው ዕለት አስመረቀ።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ታምሩ እንደተናገሩት፤ የሞጁላር ስልጠናው ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ ያለ መሆኑን ጠቅሰው፣ በዚህም እስካሁን ድረስ ከ2 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮችን ማሰልጠንና ማስመረቅ ተችሏል። ስልጠናው ግብር ከፋዮች የታክስ ህጎችን ጠንቅቀው እንዲረዱ በማድረግ፣ የታክስ ህግ ተገዢነት እንዲጎለብት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም ሥራ አስኪያጁ አስገንዝበዋል።

በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የታክስ ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ተግባሩ ታምሩ በበኩላቸው፤ የስልጠና ፍላጎቶችን መነሻ በማድረግና ምቹ የስልጠና ፎርማቶችን በመቅረጽ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በ13 ሞጁሎች ተከታታይ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረው በገቢ አሰባሰብ ረገድ አዎንታዊ ለውጦች ስለመመዝገባቸው ገልጸዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ በአገልግሎት አሰጣጥ እና ተቀራርቦ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ 13ቱንም ሞጁሎች በተገቢው መንገድ ተከታትለው ላጠናቀቁ ግብር ከፋዮች የሥልጠና ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

በተክሉ ኤልያስ
ፎቶ፦ የትናየት እንዳያፍሩ

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Megenagna, 24 Area
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30
Saturday 08:30 - 18:30