Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority

Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority

Share

This is Official Page of Addis Ababa Electric Service Administration Authority/
ይህ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር #መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ይፋዊ ገፅ ነው

Photos from Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority's post 24/05/2026

በኢትዮጵያ በልዩ የሕክምና ዘርፍ ሥልጠና ላይ ከሚገኙ እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከመጡ 4ዐዐ በላይ የሕክምና ባለሙያዎች መካከል፤ ከሩዋንዳ ከመጡ 128 የሕክምና ባለሙያዎች ጋር በጋራ ማዕድ ቆርሰናል።

‎እነዚህ ባለሙያዎች የአኅጉራችን የጤና ዘርፍ የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚጠይቀውን ከፍተኛ ዕውቀትና የላቀ ብቃት ለማሟላት ታምነው እየተጉ ያሉ ሲሆን፤ ቀጣዩን አፍሪካዊ ትውልድ በሕክምና ዘርፍ የሚኖረውን የመሪነት ሚና በማረጋገጥ ላይ የሚገኙ ተቋማት አካል ናቸው።

‎በጋራ ዕውቀትና ዓላማ፣ ይበልጥ ጤናማ የሆነች አፍሪካን አብረን መገንባታችንን እንቀጥላለን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Photos from Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority's post 24/05/2026

የሀገራችን፣ የከተማችን ኩራት እና ውበት የሆኑ ህዝባዊ መሰረት ያላቸውን ክለቦች መደገፍ ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው። - ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ

​የከተማችን አርማ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ኩራት ጠንካራ ህዝባዊ መሰረት እና ድጋፍ ካላቸው እንቁ ክለቦች መካከል እና በቅርቡ ውስጣዊ ችግር ያጋጠመው አንጋፋው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ይበልጥ ለማጠናከርና ዘመኑን የዋጀ ጠንካራ ተቋም ለመገንባት በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ በመገኝቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል።

​የነበሩ ጥንካሬዎች ይዞ የነበሩ ክፍተቶችን ሞልቶ ወደፊት ለመራመድና በትውልድ መካከል የማይበጠስ ድልድይ ለመስራት ጠንካራ ተቋም መሰረት ነው። ስለሆነም የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ከገጠሙት ፈተናዎች ሁሉ በፅናት እንዲወጣና ታሪካዊ ክብሩን ጠብቆ እንዲቀጥል የከተማችን አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ሲያደርግ ቆይቷል፤ በቀጣይም ይህ ድጋፋችን ይበልጥ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

​መሰል ድጋፎች ለቅድስጊዮርጊስ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ህዝባዊ ክለቦች የእኛን ድጋፍ በፈለጉ ጊዜ ሁሉ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። ምክንያቱም እግርኳስ በከተማችን እጅግ ተወዳጁ ስፖርት ከመሆን ባለፈ አብሮነታችንን፣ አንድነታችንን እና ወንድማማችነታችንን የምናጠናክርበት፣ የህዝብ ለህዝብ ትስስራችንን የምናሳድግበት ትልቅ መሳሪያ ነው።

​ በከተማችን እየገነባናቸው ያሉ ዘመናዊ የስፖርት መሰረተ-ልማቶች፣ የምናስተናግዳቸው ታላላቅ ውድድሮች እና የምንፈጥረው የስፖርት ባህል “የስፖርት ቱሪዝምን” (Sports Tourism) ለማሳደግ ለጀመርነው ስራ ትልቅ ስንቅ ናቸው።

ክለቦቻችን ሲጠነክሩ የከተማችን ገፅታና ቱሪዝም አብሮ ያድጋል።ስለሆነም ​ለክለባችሁ ዳግም ውጤታማነት ላሳያችሁት ህብረት እና ቁርጠኝነት ምስጋናዬ የላቀ ነው።

​ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

Photos from Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority's post 24/05/2026

አዲስ አበባን የጤና ቱሪዚም መዳረሻ ለማድረግ በመንግሥት ብቻ ሳይሆን በግሉ ሴክተርም አበረታች ስራ እየተሰራ ነው።

ዛሬ ኒዩክለስ አጠቃላይ ሆስፒታል (Nucleus General Hospital) በህክምና ባለሙያዎች አክሲዮን ማህበር ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority's post 24/05/2026

ዛሬ በኮልፌ ቀራንዩ እና የካ ክፍለ ከተሞች በበጎነት መንደር ያስገነባናቸውን አራት G-5 የሆኑ ህንፃዎች (በኮልፌ ቀራንዮ 72 ቤቶች፤ በየካ 78 ቤቶች) አጠቃላይ 150 ቤቶች ለአቅመ ደካሞች፣ ማህበራዊ ችግር ውስጥ ላሉና ለሃገር ባለውለታዎች አስተላልፈናል።

ለተጠቃሚዎቹ ያስተላለፍነው ቤት ብቻ ሳይሆን በጥራት የተገነቡ የህፃናት ማቆያ /ዴይ ኬር/፣ ህፃናት ቦርቀው የሚጫወቱባቸው መጫወቻዎች፣ ወጣቶች ተስጥኧቸው የሚያወጡባቸው የስፖርት ሜዳ እና ለነዋሪዎች በተመጣጥኝ ዋጋ የሚያቀርቡ የሸማች ሱቆች የተሟሉላቸው፣ ማህበራዊ ፍትህን የሚያነግሱ ንፁህ መኖሪያ መንደሮች ናቸው።

እነዚህን የበጎነት መንደሮች በጥራትና በፍጥነት ተገንብተው እንዲጠናቀቁ በክትትል እና ድጋፍ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ አመራሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም በገንዘባችሁ ድጋፍ ላደረጋችሁ ልበቀናዎች በነዋሪዎቹ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority's post 24/05/2026

አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ለጀመርነው ጉዞ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ነው - ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በንፋስ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በግል ባለሀብት የተገነባውን ኒውክለስ አጠቃላይ ሆስፒታልን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

በምረቃው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ የጤና ተቋሙ መመረቅ መንግስት ለጤናው ዘርፍ የሰጠውን ትኩረትና የግሉ ዘርፍ ያለውን ሚና የሚያሳይ ነው ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የጤና አገልግሎትን ለማስፋፋት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን፣ ተቋማቱ ቁጥራቸው እንዲጨምር ብቻ ሳይሆን በዘመናዊ አደረጃጀት እንዲታጠቁ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አዳዲስ ተቋማትን ከመገንባት ጎን ለጎን፣ ነባር ሆስፒታሎችን የማስፋፋት፣ደረጃቸውን የማሻሻልና አስፈላጊ በሆኑ ዘመናዊ የሕክምና ግብዓቶች የማሟላት ስራ በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

የጤና ፖሊሲው የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ የሚያበረታታ በመሆኑ፣ ቢሮው ለባለሀብቶች አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ በበኩላቸዉ ሆስፒታሉ ወደ ስራ መግባቱ ለጤናው ዘርፍ ትልቅ የምስራች ነው።

የኒውክለስ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ችግሮችን ለመቅረፍ ያለመ ግዙፍ የሕክምና ተቋም ነው።

ሆስፒታሉ ዓለም የደረሰበትን የሕክምና መሣሪያዎችና ምቹ የሕክምና ክፍሎችን በማሟላት፣ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ሙሉ ዝግጁ ሆኗል፡፡

ሆስፒታሉ ከሚሰጠው መደበኛ የሕክምና አገልግሎት በተጨማሪ ከአጎራባች ሀገራት የሚመጡ ታካሚዎችን በማስተናገድ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ተወዳዳሪነት ያሳድጋል፡፡

የሆስፒታሉ ወደ አገልግሎት መግባት የከተማዋን የሕክምና ቱሪዝም አቅም ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረውም ተጠቁሟል፡፡

Photos from Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority's post 24/05/2026

በልደታ ክ/ከተማ የተገነቡ 2 ት/ቤቶችና 3 የህፃናት ማቆያዎች ተመረቁ
በልደታ ክ/ከተማ ለትውልድ ግንባታ መሰረት የሚጥሉ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደረጉ።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እንደገለፁት ከለውጡ በፊት አብዛኞቹ ት/ቤቶች ለመማር ማስተማር ምቹ ያልሆኑ ምቹ የተማሪዎች መቀመጫ ያለነበራቸው ነበሩ ብለው ትውልድ ተኮር ሰው ተኮር የሆነው የለውጡ መንግስት ሀገር የምትገነባው በትምህርት መሆኑን እምነት ይዞ ት/ቤቶች ላይ በመስራት መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ችሏል በማለት ተናግረዋል።

ከለውጡ ቀደም ብሎ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለመማር ሁሉም ህፃናት እድል የማያገኙበት ገንዘብ ያላቸው ብቻ የሚማሩበት ነበረ ያሉት ኢንጅነር ወንድሙ መንግስት ይህንን አስተሳሰብ በመቀየር ሁሉም ህፃናት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የሚያገኙበትን ዕድል ፈጥሯል ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጲያን በፅኑ መሰረት ላይ ለማስቀመጥ የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናት ላይ መስራት ያስፈልጋል ብለው በዚህም የለውጡ መንግስት ለትምህርት ዘርፉ ትኩረት በመስጠት ከዩኒቨርስቲ የሚስተካከሉ ት/ቤቶችን ከመገንባት ባለፈ የተማሪዎች የምገባ ስርዓት በመዘርጋትና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የወላጆችን ሸክም እያቃለለ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ባደረጉት ንግግር የለውጡ መንግስት ሀገር የምትሰራው ትውልድ ሲሰራ ነው የሚል መርህን አንግቦ በትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት አድርጓል ብለው በዚህም ባለፍት የለውጥ ዓመታት ደረጃቸውን የጠበቁ ለመማር ማስተማሩ ምቹ የሆኑ ት/ቤቶችን በመገንባትና በግብዓት የማሟላት ተግባር በማከናወን ትውልድ ግንባታ ላይ በትኩረት ሰርቷል ሲሉ ገልፀዋል።

ከለውጡ ወዲህ ደረጃቸውን የጠበቁ ምቹ፣ ሳቢና ማራኪ ት/ቤቶችን ከመገንባት ባለፈ ህፃናት ስለሚለብሱትና ስለሚበሉት እንዳይጨነቁ በግብዓትና በወላጅ ገቢ ማነስ ከትምህርታቸው ወደ ኃላ እንዳይቀሩ ለማድረግ በትኩረት መሰራቱን የገለፁት የትምህርት ቢሮ ኃላፊው በዚህም የወላጆችን ሸክም ያቃለለ የምገባ ስርዓትና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ በስነ-ምግባር የታነፀ እና ውጤታማ የሆነ ትውልድ የመገንባት ሂደቱን አጠናክሮ ቀጥሏል በማለት ገልፀዋል።

የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደገለፁት የበጀት ዓመቱን ስንጀምር ከነዋሪዎቻችን ጋር ምክክር አድርገን ማህበረሰቡ ያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ነቅሰን በመያዝ ወደ ዕቅድ ቀይረን በተቀየረ 24/7 የስራ ባህል እቅዳችንን በመተግበር 70 ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለረጅም ዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ የማህበረሰቡ ችግሮች ምላሽ እንዲያገኙ አስችለናል ብለዋል።

አስተዳደሩ ትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት በማድረግ ትውልድን በስነ-ምግባር የሚያንፁ ፣ በአካልና በስነ-ልቦና የዳበረ እንዲሆን የሚስችሉ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በዚህም ት/ቤቶችን፣ የህፃናት ማቆያዎችን፣ የህፃናት መዋያዎችንና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተን በመገንባት ለአገልግሎት ክፍት እያደረግን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ የኑሮ ውድነትን የሚያቃልሉ ፣ትውልድን የሚቀርፁ፣ ለማህበረሰቡ ማህበራዊ እፎይታን የሚሰጡ ፕሮጀክቶችን ገንብተን በማስመረቅ ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ይህንን ስራ ስናከናውን ከጎናችን የነበራቹህ ባለሀብቶች እና ነዋሪዎች ምስጋና ይገባቹሃል ብለዋል።

Photos from Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority's post 24/05/2026

አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት እናደርጋታለን ብለን ስንነሳ በአካልና በአዕምሮ የዳበረ ትውልድ መገንባትን ቅድሚያ በመስጠት ነው።

በቦሌ ክፍለ ከተማ 5 ስፖርት ማዘውተሪያዎችን፣ 95 የህጻናት መጫዎቻዎችን፣ 6 የህጻናት ማቆያዎችን (day cars )፣ ካፍቴሪያዎችን፣ አንፊ ትያትሮችን እንዲሁም በርካታ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶችን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።

በተለይ ካፒቴን አበራ ለሚ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የገነቡልን በ4,900 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ስታዲየም የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ፣ የመሮጫ ትራክ፣ ጥላ ያለው የተመልካች መቀመጫ፣ ለወጣቶች የስራ እድል የሚውሉ ሱቆች፣ መታጠቢያና መጸዳጃ ቤቶች፣ ጂምናዚየም እና የእቃ ማከማቻ መጋዘንን ያካተተ ነው።

የለሚ ኮሚኒቲ ስታዲየምን ገንብተው ያስረከቡንን ካፒቴን አበራ ለሚን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እያመሰገንኩ የአካባቢው ነዋሪዎችም ስታዲየሙን በእንክብካቤ እንድትጠቀሙበት አሳስባለሁ።
የክፍለ ከተማዉ አመራሮችም ለሰራችሁት ድንቅ ስራ ምስጋና ይገባችኋል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority's post 23/05/2026

በዛሬ እለት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ3 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን እና 18 ሱቆችና 18 ሼዶችን ያካተተ የተቀናጀ የከተማ ግብርና ማዕከል አገልግሎት አስጀምረናል ።

ከተማችን ለሁሉም የምትመች የጋራ ቤታችን ናት ልማታችንም አካታች ነው። ባለፈው ስርዓት ውስጥ አርሶ አደሩ የሚገፋበት መሬቱ ብቻ ተፈልጎ የሚዘነጋበት በመሆኑ ለለውጡ መምጣት ገፊ ምክንያት ሆኗል።
አርሶ አደሩ በሁሉም የከተማ ልማት ዉስጥ አካተን አብሮ እንዲለማ እና ተጠቃሚነቱ እንረጋገጥ ከማድረግ ባሻገር ለልማት ሲነሳ ተገቢውን ካሳ ከማግኘት ባለፈ ከልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከዚህን በፊት በአቃቂ ቂሊቲ ክፍለ ከተማ 14ሺ ሄክታር የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ልህቀት ማዕከልን የገነባን ሲሆን ዛሬ በለሚ ኩራ የመረቅነውም የዚሁ አካል ነው።

እነዚህን መሰል ማዕከላት በሌላ በኩል የከተማው ነዋሪ የሚያጋጥመውን የዋጋ ንረት ለመከላከል እና በተመጣጣኝ ዋጋ የግብርና ምርቶችን ለማቅረብ የሚያስችል ነው ይህን መሰሉ አሰራር በጋራ ማደግን ተባብሮ መበልጸግን የሚያሳድግ ነው።

ይህንን ስራ በማቀድ፣ በማስተባበር ውጤታማ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority's post 23/05/2026

ትውልዱ ገብቶታል !!
የዛሬው የወጣቶች ድጋፍ እና ተነሳሽነት እጅግ አስደናቂ ነበር። እኛ ለኢትዮጵያ ብልጽግና በትጋት ስንሰራ፣ ወጣቱ ደግሞ የዚህ ስራ ፍሬ ተቋዳሽ እና የሀገሪቱን ብልጽግና የሚያጣጥም ይሆናል።
በአሁኑ ወቅት ሀገራቸውን የሚወዱ እና ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ የሚተጉ ወጣቶችን መመልከት፣ እኛም በበለጠ ትጋት እንድንሰራ ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥርልናል።
ከዛሬው በተጨማሪ ሌላው ማሳያ፣ ሰሞኑን አዶናይ ብርሃነን የመሳሰሉ ወጣቶች እንደነ ዲላን ፔጅ ያሉ ታዋቂ የአጫጭር ማህበራዊ ሚዲያ ዜና አቅራቢዎችን ወደ ሀገራችን በማምጣት የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ ለመገንባት እያከናወኑት ያለው ተግባር የሚበረታታ እና ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ፣ ወጣቶቹን “በርቱ!” ልንላቸው ይገባል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority's post 23/05/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በሞጆ ከተማ የተገነባውን የግራንዴር ሴራሚክ ማምረቻ ፋብሪካን መርቀዋል።

‎በግራንዴር ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተገነባው ፋብሪካ፣ መሰረት ልማቱ በ300,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ፣ የዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ የሴራሚክና የፖርሲሌን ንጣፎች ማምረቻ ፋብሪካ ሲሆን፤ ከዕቅድና መሬት ዝግጅት እስከ ሙሉ ሥራ ማስጀመር የወሰደው ጊዜ ዘጠኝ ወራት ብቻ ነው።

‎​በአሁኑ ወቅት 60x60 የሴራሚክ ንጣፎችን በስፋት ማምረት የጀመረው ይህ ፋብሪካ፤ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ የምርት ዓይነቶቹን በማስፋት የ80x80፣ 60x120፣ 70x140 እና 80x160 መጠን ያላቸውን የንጣፍ ዓይነቶች እንዲሁም የአውሮፓን የጥራት ደረጃ ያሟሉ የፖርሲሌን ምርቶችን ማቅረብ እንደሚጀምር ይጠበቃል። ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ መዋዕለ-ነዋይ የወጣበት ይህ ፋብሪካ፣ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሽግግር ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ያመላከተ ክንውን ነው።

‎ለ​ፋብሪካው ምርት የሚያስፈልጉት ጥሬ ዕቃዎች 80 በመቶ የሚሆነው ከፋብሪካው በ100 ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ ይህም ሙሉ በሙሉ የተቀናጀና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር የተሳሰረ የአቅርቦት ሰንሰለት ፈጥሯል። ኢትዮጵያ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ባሳለፍናቸው ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ ከ4.85 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማዳን በቻለችበት በዚህ ወቅት፤ የግራንዴር ሴራሚክ መከፈት የውጭ ምርት ጥገኝነትን የሚቀንስ ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችላትም ጭምር ነው።

Prime Minister Abiy Ahmed together with high-level government officials, inaugurated Grandeur Ceramic Manufacturing in Mojo City. The facility is a world-class ceramic and porcelain tile manufacturing plant spanning 300,000 square meters, completed in just nine months from land preparation to full commissioning.
Already in active production of 60x60 ceramic tiles, the factory is expected to expand within the next two months to manufacture 80x80, 60x120, 70x140, and 80x160 tile formats, alongside porcelain tiles produced to European quality standards. With an investment exceeding 2 billion birr, the facility marks a major milestone in Ethiopia’s industrial transformation.
Approximately 80 percent of the factory’s raw materials are sourced locally from within a 100-kilometer radius, creating a fully integrated and community-rooted supply chain. At a time when Ethiopia has saved more than $4.85 billion in foreign exchange within just nine months through import substitution, Grandeur Ceramic not only reduces imports but also positions Ethiopia to compete in global markets.

Photos from Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority's post 23/05/2026

ዛሬ "ወጣት ይምረጥ ኢትዮጵያ ትጽና” በሚል መሪ ቃል የብልጽግና አሻራ በተቀመጠበት ገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ከመላ ከተማችን ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም አካሂደናል ።
ስለ ወጣቱ ተጠቃሚነት ችግርን እያወራን ሳይሆን 24/7 እየሰራን ለችግሩ ተግባራዊ ምላሽ ከሰጠንባቸው እና ተጠቃሚነቱን ካረጋገጥንባቸው ስፍራዎች አንዱ በሆነው በገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ70 ሺህ በላይ ከሆኑ የከተማችን ወጣቶች ጋር በስፓርታዊ እንቅስቃሴ የምርጫ ቅስቀሳ አድርገናል።
ባለፉት 5 ዓመታት የሰራናቸው የልማት አሻራዎች የኢትዮጵያን ብልፅግና አይቀሬነት ይመሰክራሉ። ከማንም በላይ ሀገር እየተገነባች ያለችው ለወጣቶቻችን በመሆኑ የብልፅግናዋ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ።
የከተማችን ወጣቶች የፓርቲያችንን ራዕይና የወደፊት አሻራ ሁለንተናዊ እድገት ሰንቃችሁ፥ ተስፋ ተጋርታችሁ ማልዳችሁ ከአራቱም አቅጣጫዎች በመትመም ድጋፋቸሁን ስለገለፃችሁልን በራሴ እና በፓርቲዬ ብልፅግና ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
መንገዳችን መደመር፤ መዳረሻችን ብልፅግና ነው!
ኢትዮዽያን ወደ ተምሳሌት አገር !
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Addis Ababa
1000