25/05/2026
በሀላባ ዞን በዌራ ወረዳ አቦክቾ ከተማ የከተማዉ መዘጋጃ ጽ/ቤትና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ምረቃ ስነስርዓት እና የፊታችን ግንቦት 24/2018 የሚካሄደው ሀገራዊ እና ክልላዊ የምርጫ ቅስቀሳ በድሮን እና በካሜራ የተቀረጸ ምስል
ይህ በዌራ ወረዳ ዙሪያ ስለሚገኙ የአቅማ ደከመን በሚሸለ ስለሚደገፉና የአሠሪዎች እንዲሁም የማህበራዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ መረጃዎች የሚቀርብበት ገጽ ነው።
25/05/2026
በሀላባ ዞን በዌራ ወረዳ አቦክቾ ከተማ የከተማዉ መዘጋጃ ጽ/ቤትና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ምረቃ ስነስርዓት እና የፊታችን ግንቦት 24/2018 የሚካሄደው ሀገራዊ እና ክልላዊ የምርጫ ቅስቀሳ በድሮን እና በካሜራ የተቀረጸ ምስል
25/05/2026
25/05/2026
25/05/2026
በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ በአጭር ግዜ ግንባታው የተጠናቀቀው የአቦክቾ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ህንፃ እና የስብሰባ አዳራሽ ከጥቂት ደቂቃዎች ቦሀላ በደማቅ ሁኔታ ይመረቃል ።
በምረቃው መርሃግብር ላይ የክልል የዞን የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ያስመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
22/05/2026
የህፃናት መብትና ደህንነት፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤት እያስመዘገቡ ነው -ክብርት ሂክማ ከይረዲን
****************
( ግንቦት 13/2018 ዓ.ም) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከSOS Children's Village ጋር በመሆን በህጻናት መብትና ጥበቃ ላይ የተዘጋጁ ሰነዶችን የማስተዋወቂያ እና ግብዓት የማሰባሰቢያ መርሀ-ግብር ተካሂዷል።
መርሀ-ግብሩ ላይ ከሁለቱ የከተማ አስተዳደር እና ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች እና አጋር ድርጅቶች ተሳትፈዋል።
የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን የህፃናት መብት፣ ደህንነት፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል።
የህፃናትን ተግባራት ለማቀላጠፍና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችንና ማንዋሎችን በማዘጋጀት እንዲሁም የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት በስራ ላይ እንዲውል መደረጉን ተናግረዋል።
የህፃናት ፖሊሲ እና የቅድመ ልጅነት ፖሊሲዎች በሀገራችን ያሉ ህፃናትን የትምህርትና የጤና ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋፅዖ እያበረከተ መሆኑን ገልፀዋል።
የማህበረሰብ ውይይት ማንዋሉን እና ሌሎች የአሰራር ማዕቀፎቹን እስከታች በማውረድ ለህፃናት መብትና ደህንነት መጠበቅ ሁሉ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የህጻናት ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የማህበረሰብ ውይይት ማንዋል ይፋ ተደርጓል። የህፃናት የተጠቃለለ ህግ ለማዘጋጀት የተደረገ የዳሰሳ ጥናት እንዲሁም የህጻናት መብትና ጥበቃ አዋጅ የመጨረሻ ረቂቅ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ማድረግ ተችሏል።
22/05/2026
በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ በተገኙበት የHCO 2019 ባጀት ዕቅድ ቀርቦ ፀደቀ
ግንቦት 14/2018 በዌራ ወረዳ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ በተገኙበት የHCO ፕሮጀክት 2019 ባጀት ዕቅድ በስትሪም ኮሚቴ እና በቴክኒክ ኮሚቴ ቀርቦ ፀድቋል።
መድረኩን የዌራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ የመሩት ስሆን በውይይቱ ላይ በፕሮጀክቱ የታቀፉ ሴክተሮች የ2019 ዕቅድ አቅርበው ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል ።
ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ በቀጣይ በዕቅዱ መነሻ በፕሮጀክቱ የሚመድበው ባጀት ለታለመለት ዓላማ በማዋል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በዘላቂነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በፕሮጀክቱ የሚመድበው ባጀት ግልፀኝነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር በመጠቀም የሚታቀደው ባጀት በአግባቡ ስራ ለይ እንዲውል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
በመጨረሻም በስትሪም ኮሚቴ እና በቴክኒክ ኮሚቴ በተነሱ ሀሳቦች ዙሪያ ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል፡፡
በመድረኩ ላይ የዌራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ እና ግብርና ጽ/ቤት ሀላፍ አቶ ጀማል ሚሀሌ፣ የዌራ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ገለቶን ጨምሮ ሌሎችም የስትሪም ኮሚቴ እና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል ።
21/05/2026