12/06/2026
የአሚን ሆስፒታል ባለቤት ዶክተር መሀመድ ሽኩር ለሀላባ ከነማ ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገቡትን 2,000,000 ብር ገቢ አደረጉ!
የሀላባ ከነማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመግባቱ የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ 2,000,000 ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።
ዶክተር መሀመድ የገቡትን ቃል ወደ ተግባራዊ አድርገዋል ከልብ እናመሰግናለን!!!
03/06/2026
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ለሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ የላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ድጋፍ አደረገ
ግንቦት፣26/20 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ራመቶ ቦካ ድጋፉ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል በተሰጠው ትኩረት መሰረት ተቋሙ አቅም በፈቀደው ሁሉ ድጋፉ የሚቀጥል መሆኑንም አመላክተዋል።
የሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ኤፍሬም ዘለቀ በበኩላቸው
ድጋፉ የሀላቢሳን ቋንቋን ለማሳደግ በሚደረገው ሂደት ውስጥ አጋዥ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
በተጨማሪም የትምህርት ጥራት መጠበቂያ ኢንሼቲቮችን በውጤታማነት ለመተግበር የታለመ ድጋፍ ስለ መሆኑም ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል።
በመጨረሻም የዲጂታል ትምህርትን ለመስፋፋት ብሎም የትምህርት መረጃን ለማዘመንና መረጃዎችን በዘመነ መልኩ ለማደራጀት ድጋፉ ወሳኝ ስለመሆኑም ነው ዶ/ር ኤፍሬም ያብራሩት።
03/06/2026
በበጀት ዓመቱ በቀሪ ግዜ የገቢ አሰባሰቡን በስኬት ለማጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ተቋማት እርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረባ
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የገቢ አሰባሰብ ስራንና የደረጃ ''ሀ'' እና ''ለ'' ግብር አከፋፈል አፈጻጸምን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የገቢዎች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብድልቃድር ኢማም ሎላሶ በመሩት በዚሁ የግምገማ መድረክ ላይ በበጀት ዓመቱ በቀሪ ጊዜያት የገቢ አሰባሰቡን በስኬት ለማጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ተቋማት ያለምንም መዘናጋት ቀን ከሌት ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በመደበኛና በማዘጋጃ ቤት ዘርፍ እስካሁን የተከናወኑ የገቢ አፈጻጸሞች የተገመገሙ ሲሆን የከተማውን የወጪ ፍላጎት በራስ አቅም ለመሸፈን እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።
የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት በቀጣይ በቀሪ ቀናት የደረጃ ''ሀ'' እና የደረጃ ''ለ'' ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ እንዲከፍሉ በማድረግ፣ የኦዲት ውዝፍ ያለባቸውን በልዩ ሁኔታ በመለየት፣ የደረሰኝ ቁጥጥር ስራን በማጠናከርና ወርሃዊ ሪፖርቶችን በትክክለኛው ጊዜና ጥራት በማደራጀት የተሸላ የገቢ አሰባሰብ ስራን ለመስራት እርብርብ ይደረጋል ብለዋል።
የከተማችን የልማት ፍላጎት እንዲሟላ ግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ግብሩን በወቅቱ በመክፈል የዜግነት ግዴታውን መወጣት እንዳለበት ጠቁመው በዚህም መሰረት የደረጃ "ሀ" ሁለተኛ ዙር (1/4) ግብር ከፋዮችና የደረጃ "ለ" ሶስተኛ ዙር (1/4) ግብር ከፋዮች እስከ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም ድረስ ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በኋላ ለሚመጡ ግብር ከፋዮች ወለድና አስተዳደራዊ ቅጣት የሚሰላ መሆኑን አውቀው ህጋዊ ግዴታቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲወጡ አሳስበዋል።ዘገበዉ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮምዩንኬሽን ነዉ
03/06/2026
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ የሌጋሞ ድልድይ ቀሪ ስራዎችን በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንድጀምር ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
*******
ግንቦት፣26/2018
በዌራ ዲጆ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት አማካኝነት በጮባሬ ሜዕኖ ቀበሌ በቀድሞ ደቡብ ክልል ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት ያልጀመረውን ድልድይ ቀሪ የጋብዮን ስራዎችን ለማጠናቀቅ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በዱራሜ ዲስተሪክት እየተሰራ ይገኛል።
በዚህም በዛሬው ዕለት የዌራ ዲጆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዲ አደም፣በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን የዱራሜ ድስትሪክት ስራ አስከያጅ ኢ/ር ሀይሌ አበራ፣የዌራ ዲጆ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ አቡቴን ጨምሮ የዱራሜ ድስትሪክትና የወረዳ ትራንስፖርት የሳይት ባለሙያዎች በተገኙበት ቀሪ ስራው ምልከታ ተደርጓል።
በዚህም ወቅት የሌጋሞ ድልድይ ቀሪ ስራዎችን በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ የተገለፀ ስሆን፣የጋብዮን ቀሪ ስራ ለማስጀመር ለሁለተኛ ዙር ጋብዮን የማስገባት ስራውም ተከናውኗል። ስል የዘገበው የወረዳው መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው።
03/06/2026
በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ የአሾካ ጤና ጣቢያ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የአልትራሳውንድ ማሽን እና የማይክሮስኮፕ ግዢ በመፈጸም ርክክብ ተደረገ
*******
ግንቦት፣26/2018 ዌራ ወረዳ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የአልትራሳውንድ ማሽን እና ማይክሮስኮፕ ግዢ በመፈጸም ለአሾካ ጤና ጣቢያ ርክክብ ተደርጓል ።
ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚረጋገጠው ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ መፍጠር ሲቻል ነው ያሉት የዌራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ከዲር የሴ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ማህበረሰቡ አገልግሎቱን በቅርበት እንዲያገኝ ቋማቱ ከ PBF ፕሮጄክት ካገኙት ገቢ ግዢ መፈጸሙን ገልጸዋል።
የማሽኖቹ መገዛት የጤና ተቋማት የአገልግሎት ጥራት አንድ እርጃ ከፍ የሚያደርግ መሆኑን እና አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ሀላባ አጠቃላይ ሆስፒታል ይሄዱ የነበሩ እናቶችን እንግልት የሚቀንስ መሆኑን በማንሳት በቀጣይም በሌሎች ጤና ጣቢያዎች የውስጥ ቁሳቁስ የማሟላቱ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የአጋር ድርጅቶች ድጋፍ የጤና ተቋማትን የተሟላ አገልግሎት ላይ እንድገኙ ከማድረግ አንጻር ወሳኝ መሆኑን አንስተው ተጠናክሮ እንድቀጥል ጥሪ አስተላልፏል።
አያይዘውም PBF ፕሮጄክት በCORDOID ETHIOPIA አጋርነት ጤና ተቋማት የዉስጥ ገቢያቸው እጅግ በጣም እንድሻሻል ከማድረጉም በላይ መሰረታዊ የአገልግሎት መስጫ የህክምና መሣርያዎችን በራሳቸው እንድያሟሉ በማድረግ የተቋማትን ደረጃ ከፍ እያደረገ ያለውን የPBF ፕሮጄክትን እና CORDOID ETHIOPIAN አመስግኗል።
የዌራ ወረዳ ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ያዲሶ ዱበላ በበኩላቸው ማሽኑን የረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ የቆየ መሆኑን ጠቅሷል ።
አቶ ያዲሶ አያይዘው ድጋፍ የተደረገውን ማሽን ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ ባለሙያዎች በአግባቡ መገልገል አለባቸው ያሉ ሲሆን የPBF ፕሮጄክት ለዚህ ሁሉ ዉጤት ድርሻው ከፍተኛ በመሆኑ የፕሮጄክቱ ዉጤታማነት ይበልጥ እንድሰፋ ሁሉም ባለድርሻ ሀላፊነቱን በአግባቡ እንድወጣ አሳስበዋል።
በመጨረሻም የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ እና የአገልግሎት ቦታዎችን ተዟዙረው ምልከታ አድርገዋል።
በርክክቡ ወቅት የዌራ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመቹ ኤዳሳ፣ የጤና ተቋማ ሀላፊዎች እና ከዞን፣ ከወረዳና ከጤና ጣቢያዎቹ የሚመለከታቸው ባለሞያዎች ተገኝተዋል።ስል የዘገበው የወረዳው መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው።
25/05/2026
በሀላባ ዞን በዌራ ወረዳ በ11.5 ሚሊየን ብር ባላይ ወጪ የተገነባውን የአቦክቾ ከተማ ማዘጋጃ ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
=====
ግንቦት 17/2018 በሀላባ ዞን በዌራ ወረዳ በ11.5 ሚሊየን ብር ባላይ ወጪ የተገነባውን የአቦክቾ ከተማ ማዘጋጃ ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
የማዘጋጃ ቤቱ ግንባታ የተሻለና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ በከተማዋ እድገት ወሳኝ መሆኑን ተገልጸዋል።
የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን፣ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወይዘሮ መናቴ ሙንድኖ፣ የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊና የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ፣ የዌራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ፣ ሌሎች የክልሉ፣ የዞን እና የዌራ ወረዳ አመራሮች ተገኝተው የአቦክቾ ከተማ ማዘጋጃ ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በይፋ አስመርቋል።
24/05/2026
በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ በአጭር ግዜ ግንባታው የተጠናቀቀው የአቦክቾ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ህንፃ እና የስብሰባ አዳራሽ በነገው ዕለት በደማቅ ሁኔታ ይመረቃል ስል ዌራ ወረዳ ፉይናንስ ጽ/ቤት ዘግቧል።
23/05/2026
በዌራ ወረዳ በአለምጤና ቀበሌ ከ8 ዓመት በፊት ተቋፍሮ አገልግሎት ሰይሰጥ የቆመዉ የንፁህ መጠጥ ዉሃ የማስፋፍያ ስራ ተጀመረ
ግንቦት 15/2018 ዓ በሀላባ ዞን በዌራ ወረዳ በአለምጤና ቀበሌ ከ8 ዓመት በፊት ተቋፍሮ አገልግሎት ሰይሰጥ የቆመዉ የንፁህ መጠጥ ዉሃ የማስፋፍያ ስራ በዛሬው ዕለት በመካና የሱስ ድርጅት ድጋፍ ስራው በይፋ ተጀምሯል ።
የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ እና የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መሀመድከማል ኑርዬ በቀበሌው ተገኝተው ምልከታ ባደረጉበት ወቅት እንደገለፁት በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው መንግሥት በዞኑ በየደረጃው የሚስተዋለውን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።
አቶ መሀመድከማል አያይዘው ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ኑሮ ለማሻሻል፣ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለማስፋት እና ፍትሃዊ ልማት ለማረጋገጥ በተግባር እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማትን በመንከባከብና ሲበላሹ በማስጠገን ዘላቂ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ህብረተሰቡ በባለቤትነት ማስተዳደር ይጠበቅበታል ሲሉም እ አክለዋል ።
የዌራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ በበኩላቸው በወረዳው የመጀመሪያና አሳሳቢ የሆነው የንፁህ መጠጥ ውሃን አቅርቦት በማስፋፋትና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብሏል ።
የሀላባ ዞን ውሃና ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ ሀላፊ አቶ አብዲልአዚዝ ከይረዲን በበኩላቸው በዞኑ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ ከመንግስት እና የተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶችን በማስተባበርና ችግሮቹን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ ነው ስሉ አስገንዝበዋል ።
በምልከታው ላይ የዌራ ዲጆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አብዲ አደም ፣የዌራ ወረዳ ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ጽ/ቤት ሀላፍ አቶ መ/ሻፊ አሳሞ ፣የዌራ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፍ አቶ ገመቹ ኤዳሳ ን ጨምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካለት ተገኝተዋል ስል የወረዳው መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።
22/05/2026
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ የምግብ ዋስትና ስራዎች አፈፃፀም ግምገማና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከቴክኒክ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት ተደረገ።
በዌራ ዲጆ ወረዳ የምግብ ዋስትና ስራዎች አፈፃፀም ግምገማና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከቴክኒክ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።
የውይይት መድረኩን የዌራ ዲጆ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጎበና ሰማን የመሩት ስሆን፣በውይይቱ መድረኩ የቴክኒክ ኮሚቴ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በውይይቱም የምግብ ዋስትና ስራዎች አፈፃፀምና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ተነስቶ በሰፊው ውይይት በማድረግ፣በቀጣይ በደካማ ጎን የተነሱትን በፍጥነት ለማረም እንድሁም በጠንካራ ጎን የተነሱት ለማስቀጠል መግባባት በመቻል፣ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።
#ዌራዲጆወረዳመንግስትኮሚዩኒኬሽንጽ/ቤት
22/05/2026
ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የበሸኖ ስንቢጣ ሶላር ፕሮጀክት ተመረቀ
ግንቦት 14/2018
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በሀላባ ዞን በዌራ ዲጆ ወረዳ ለንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት እንዲውል ያስገነባውን በሸኖ ስንቢጣ ሶላር ፕሮጀክት አስመረቀ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ ባስተላለፉት መልዕክት የክልሉን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርን በመፍታት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።
የንፁሁ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ወደ ሶላር ኢነርጂ መቀየሩ በዘላቂ ታዳሽ ሀይል አማራጭ የማህበረሰቡ የነዳጅ ወጪ በማስቀረት አስተማማኝ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን አቶ ዳዊት ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ አሁን ያለውን የኢነርጂ ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ ዘላቂ መፍትሄ መሆኑንም ሀላፊው አብራርተዋል።
ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባውና 360 የሶላር ፓኔሎች የተተከለበት 211 ኪሎ ዋት ሀይል የሚያመነጭ መሆኑን ጠቁመዋል።
በወረዳው የሚገኙ ሰባት ቀበሌያት ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑ በቀጣይ አራት ቀበሌያትም የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ መሆኑን ተናግረው በዚህም በአጠቃላይ 70ሺ የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።
ፕሮጀክቱ የክልሉ ውሃ፣ መስኖ ማዕድን ልማት ቢሮ ከከፌዴራል ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር ያስገነባው መሆኑ ተገልጿል።
በመርሃ ግብሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊ መሀመድ ኑሪዬ(ዶ/ር) ጨምሮ የክልል የፌዴራል እና የሀላባ ዞን ከፍተኛ አመራሮችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።