03/06/2026
በበጀት ዓመቱ በቀሪ ግዜ የገቢ አሰባሰቡን በስኬት ለማጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ተቋማት እርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረባ
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የገቢ አሰባሰብ ስራንና የደረጃ ''ሀ'' እና ''ለ'' ግብር አከፋፈል አፈጻጸምን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የገቢዎች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብድልቃድር ኢማም ሎላሶ በመሩት በዚሁ የግምገማ መድረክ ላይ በበጀት ዓመቱ በቀሪ ጊዜያት የገቢ አሰባሰቡን በስኬት ለማጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ተቋማት ያለምንም መዘናጋት ቀን ከሌት ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በመደበኛና በማዘጋጃ ቤት ዘርፍ እስካሁን የተከናወኑ የገቢ አፈጻጸሞች የተገመገሙ ሲሆን የከተማውን የወጪ ፍላጎት በራስ አቅም ለመሸፈን እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።
የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት በቀጣይ በቀሪ ቀናት የደረጃ ''ሀ'' እና የደረጃ ''ለ'' ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ እንዲከፍሉ በማድረግ፣ የኦዲት ውዝፍ ያለባቸውን በልዩ ሁኔታ በመለየት፣ የደረሰኝ ቁጥጥር ስራን በማጠናከርና ወርሃዊ ሪፖርቶችን በትክክለኛው ጊዜና ጥራት በማደራጀት የተሸላ የገቢ አሰባሰብ ስራን ለመስራት እርብርብ ይደረጋል ብለዋል።
የከተማችን የልማት ፍላጎት እንዲሟላ ግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ግብሩን በወቅቱ በመክፈል የዜግነት ግዴታውን መወጣት እንዳለበት ጠቁመው በዚህም መሰረት የደረጃ "ሀ" ሁለተኛ ዙር (2/4ኛ ግብር ከፋዮችና የደረጃ "ለ" ሶስተኛ ዙር 3/4ኛ ግብር ከፋዮች እስከ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም ድረስ ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በኋላ ለሚመጡ ግብር ከፋዮች ወለድና አስተዳደራዊ ቅጣት የሚሰላ መሆኑን አውቀው ህጋዊ ግዴታቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲወጡ አሳስበዋል።
02/06/2026
#ማስታወቂያ
ለሀላባ ቁልቶ ከተማ ለሚትገኙ ለደረጃ "ለ" እና ለደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች በሙሉ
በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት የደረጃ 'ለ' እና 'ሀ' ግብር ከፋዮች አመታዊ ግብራቸው 1/4ኛ ወይም 25% ቅድመ ግብር በየሩብ ዓመቱ መክፈል እንዳለባቸው ተደንግጓል፡፡
በዚህም መሰረት ከግንቦት 01_30/2018ዓ.ም በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት,,የደረጀ 'ለ' ግብር ከፋዮች 3ተኛ ዙር እንዲሁም የደረጃ 'ሀ' ግብር ከፋዮች 2ተኛ ዙር 1/4ኛ ወይም (25%) ቅድመ ግብር የሚከፈልበት ጊዜ በመሆኑ ግብር ከፋዮቻችንም በወቅቱ የሚጠበቅባቸውን 1/4ኛ ቅድመ ግብር በመክፈል ኃላፊነታቸውን እንዲትወጡ የሀላባ ቁልቶ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ያሳስባል።
ግብርን በወቅቱ መክፈል የልማት አርበኝነት ነዉ!!
02/06/2026
የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብር የሚከፍሉበት በሚከተለው አኳኋን ይሆናል፣
ከተያዘው የግብር ዓመት በፊት ማለትም የ2017 ግብር ዘመን በነበረው የከፈሉትን ግብር 25%(ሃያ አምስት በመቶ) ከሐምሌ ወር መጨረሻ ጀምሮ በሚቆጠር በየሶስት ወሩ የሶስት ወሩ በተጠናቀቀ በ30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ አስቀድመው መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
በዚህ መሠረት፡-
👉የመጀመሪያ ዙር ክፍያ ጊዜ ከህዳር 01 እስከ 30 ይሆናል፣
👉የሁለተኛ ዙር ክፍያ ጊዜ የካቲት 01 እስከ 30 ይሆናል፣
👉የሶስተኛ ዙር ክፍያ ጊዜ ከግንቦት 01 እስከ 30 ሲሆን በየግብር ዓመቱ ሐምሌ ወር መጨረሻ ሊከፍሉ ከሚገባው ግብር ላይ በየሶስት ወሩ የከፈሉት ተቀንሶ ቀሪውን ይከፍላሉ፡፡
የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ መያዝ ግዴታ የለለባቸው ሲሆን በፍቃደኝነት መያዝ ይችላሉ፡፡ የያዙት የሂሳብ መዝገብ ተቀባይነት ካገኘ የሚከፍሉት ግብር በሂሳብ መዝገባቸው ሠንጠረዥ ሐ መሰረት ይሆናል፡፡
ከላይ የተጠቀሰው ቢኖርም ለመጀመሪያ ጊዜ የገቢ ግብር የሚከፍሉ አዲስ ግብር ከፋዮች የመጀመሪያውን የግብር ዓመት በተመለከተ ዓመታዊ ግብር የሚከፍሉት በሚከተለው አኳኋን ይሆናል፤
ሀ) የደረጃ "ሀ" አዲስ ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ገቢያቸውን ማስታወቅ ባለባቸው ጊዜ በግብር ዓመቱ ሊከፍሉት የሚገባውን ግብር መክፈል አለባቸው፡፡
ለ) የደረጃ "ለ" አዲስ ግብር ከፋዮች ከሐምሌ 1 ቀን እስከ ሐምሌ 30 ቀን ባለው ጊዜ ዉስጥ ግብሩን መክፈል አለባቸው::
23/05/2026
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከአረፋ በዓል የከብት ገበያ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ!!!
የአረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከከብት በረት (ገበያ) 535,300 (አምስት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ሶስት መቶ) ብር ገቢ መሰብሰቡ ተገለፀ።
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ም/ካንቲባ እና የገቢዎች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አ/ቃድር ኢማም ሎላሶ እንደገለፁት የዕለቱን የበዓል ገበያውን ታሳቢ በማድረግ ከከተማው የቅዳሜ ገበያ የከብት ተራ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በተሰራው ሥራ ይህንን ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።
አቶ አብዲልቃድር አያይዘውም ከተማችን የምታመነጨውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመው በቀጣይም ለገቢ አሰባሰብ ስኬታማነት በጋራ እርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ም/ካንቲባው ለዚህ ስኬት መገኘት በቅንጅት ለሠሩት አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና የፀጥታ አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
22/05/2026
#ለመለዉ ለከተማችን ግብር ከፋዮች በሙሉ,, የከተማችን ልማት የሚቀጥለው ግብር ከፋዩ በሚከፈለው ገቢ በመሆኑ ጊዜዉ ሳይጠነቃቂ ግዴታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን !!
13/05/2026
የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብር የሚከፍሉት በሚከተለው አኳኋን ይሆናል፣