03/06/2026
የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የጤናው ቤተሰብ በአጠቃላይ በመደበኛው እና በወቅታዊ የንቅናቄ ስራዎች ላይ የተኮረ ውይይት ተደረገ ።
ግንቦት 26/2018 ዓ.ም
በሸኖ
በሀላባ ዞን የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በወቅታዊ እና በአጠቃለይ በጤናው ስራዎች ዙሪያ የጤናው ቤተሰብ ውይይት አደረገ ። ውይይቱም ያተኮረው በ ARM ቅድመ ዝግጅት ፣ ወባ መከላከልን የተመለከቱ እንዲሁም በተቋማት ድጋፍ እና ክትትል ፣ በሪፖርት ወቅታዊነትና ጥራት እንዲሁም በሌሎችም በመደበኛ ስራዎች ላይ ያተኮረ ዉይይት ተደርጓል።
የውይይት መድረኩን የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሃኢሻ አበቴ መርተዋል ። በዚህም በተነሱት ሀሳቦች ላይ ሰፊ ዉይይት ተደርጎ የጋራ አቅጣጫ በመያዝ ተጠናቋል።
13/05/2026
በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ስር ሁሉም ጤና ጣቢያ የ2018 በጀት ዓመት የ10 ወራት አጠቃላይ ተግባራት ዕቅድ ክንውን የስራ አፈጻጸም ተገመገመ።
ግንቦት 5/2018 ዓም
የግምገማውን ሰነድ ያየ የጤና ጣቢያው ሀላፊዎች አማካኝነት ሰፋ ባለ መልኩ ቀርቧል።
በግምገማውም የዌራ ዲጆ ወረዳ የተቋሙ ደጋፊ በየ በሚደግፉት ጤና ጣቢያ የተገኙ ስሆን በግምገማው መድረክ የሁሉም ቀበሌ ጤና ኤክስቴንሽን እና ጤና ጣቢያው የማኔጅመንት አባለት፣ የቀበሌ ደጋፊ ባለሙያዎችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካለት በተገኙበት አጠቃላይ የጤናው ተግባራት በደረጃ በአፈፃፀም ልክ የተገመገመ ስሆን በጤና ጣቢያና በወረዳ ደረጀ ስገመገም በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ለቀጣይ ዝቅተኛ በሆኑ አፈጻጸሞች ዙሪያ እንደ ተቋም አቅጣጫ ተይዟል ።
በመድረኩም ሰፊ ውይይት ተደርጎ ሀሳብ አስተያየት እንዲሁም ለተነሱት ጥያዎች ምላሽ ተሰጥቷል ።
በመጨረሻም በቀጣይ ቀሪ ወራት በሚተገበሩ ስራዎች ላይ የአጭር ግዜ ገደብ የያዘ የድርጊት መርሀግብሮችን በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል::
12/05/2026
በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ወቅታዊ የንቅናቄ የጤና ስራዎች እና የመደበኛ ተግባራት አፈጻጸም ተገመገመ ።
የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የወቅታዊ የንቅናቄ እና የመደበኛ ተግባራት አፈጻጸም ሁሉም የማኔጅመንት አባለትና ባለሞያዎች ጋር ተገመገመ ።
መድረኩን የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሀኢሻ አበቴ የመሩት ሲሆን ለዉይይት መነሻ የመደበኛ ተግባራት አፈፃፀምና በንቅናቄ የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም እንደ መነሻነት ተወስደዋል ።
በመደበኛነት የሚሰሩ የእናቶችና ህጻናት፣ የበሽታ መከላከልና አክሞ ማዳን፣ የሎጀስቲክ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የጤና መድህን ተግባር፣ የሬጉላቶሪ፣ የማህበረሰብ ጤና የድንገተኛ አደጋ ቁጥጥርና ምላሽ፣ የወባና የሌሎች የወረርሽኝ መከላከል ተግባራትና በንቅናቄ እየተፈፀሙ ያሉት የሞዴል ቀበሌዎችን የመፍጠር ተግባራት ያሉበት ደረጀ በተያያዘ በዉይይቱ በዋናናት ተገምግመዋል።
በግምገመዉ የተለዩት ክፍተቶች ቶሎ መታረም እንደሚገባ ፣ወቅታዊ የንቅናቄ ስራዎች በተያዘላቸዉ ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት ልተገበሩ አንደሚገባ እንዲሁም የወራርሽኝ መከላከልና መቆጣጠረ ተግባራት አጠናክረዉ በመስራት የተከሰቱ ወራርሽኞችን በአጠረ ጊዜ መቆጣጠር እንደሚገባ እና የሁሉም ቀበሌዎች ለጤና አጋዥ የሆኑ የጤና ኔትወርኮችን በመጠቀም የተጀመሩ የሞዴል ቀበሌ ስራ በአጠረ ቀን ማጠናቀቅ እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቅቋል።
በዉይይቱ ላይ የጽ/ቤቱ ሁሉም ማናጅመንት አባለት እና ባለሞያዎች ተገኝተዋል ።
11/05/2026
የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ለወረዳዎች እና ሆስፒታሎች የተለየዩ ለጤና አገልግሎት የሚሆኑ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
=====
ግንቦት 3/2018 የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ለወረዳዎች እና ሆስፒታሎች የተለየዩ ለጤና አገልግሎት የሚሆኑ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
ይህ ድጋፉም፣ የዞን ጤና መምሪያ ከክልሉ ጤና ቢሮ የተገኘ ድጋፍ መሆኑን ተጠቁሟል።
በዚህ ወቅትም የሀላባ ዞን ጤና መመሪያ ሀላፊ ዶ/ር ሸምሱ ረሽድ እንደገለጹት ባለፉት አመታት የጤናውን ዘርፍ ለማዘመን መጠነ-ሰፊ ስራዎች ተሰርቷል ብለዋል።
በጤናው ዘርፍ የመጡ ውጤቶችን ለማስቀጠል የተደረገው ድጋፍ አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ የተገኘውን ድጋፍ ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንደሚገባ አሳስበዋል።
በተለይም የክትባት ፕሮግራም ተደራሽነት ለማስፋት፣ የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ስራዎችን ለማዘመን፣ የጤና ቁጥጥር ስራዎችን ለማቀላጠፍና ለጽዱ ኢትዮጵያ አተገባበር ድጋፉ ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
የሀላባ ዞን ዞን አስተዳደር ማህበራዊ አማካሪ አቶ ሁሴን ሮባ በበኩላቸው ለውጡ መንግስት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዞኑ የጤናው ዘርፍ ለማዘመን አገልግሎት ለማሻሻል የሚረዱ የተለየዩ ለጤና አገልግሎት ለሚሆን የተደረገው ድጋፍ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ድጋፉም 2 ሞተር ሳይክል፣ 11 ኮምፒዩተርና 4 ታብሌቶችን ጨምሮ ሌሎች ለጽዱ ኢትዮጵያ የሚያገለግሉ ግብዓቶች ስርጭት ለመዋቅሮቹ ተደርገዋል።
04/05/2026
በሀላባ ዞን የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት አጠቃላይ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ ።
ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም በሸኖ
የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት አጠቃላይ የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን ሁሉም የጽህፈት ቤት ባለሙያዎች በተገኙበት የበጀት አመቱን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ ክንውን በዛሬ ዕለት ገምግሟል ።
ለግምገማ የተዘጋጀውን ሰነድ የየስራ ክፍሉ አስተባባሪ አማካኝነት በሰፊው ለመድረኩ ተብራርቶ ቀርቧል።
የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሀኢሻ አበቴ በቀረበው አፈጻጸም መነሻ ሁሉም ጤና ተቋማት አጠናክረው መቀጠል ያለባቸውንና በቀጣይ ቀሪ የስራ ቀናት ውስጥ የተሸለ ውጤት መምጣት አለባቸው የተባሉትን ተግባራትን በዝርዝር ጠቅሰው አጠናክረው መሄድ እንዳለባቸው አስቀምጠዋል ።
አያይዘውም ከማህበረሰብ እና ከባለድርሻ አካለት ጋር የሚተገበሩ የጤና ስራዎችን ማለትም የወባ ቁጥጥር ፣ የማህበረሰብ ቲቢ ልያታ እና ህክምና ስራ እንዲሁም ሌሎችንም አጠቃላይ የጤና ስራዎችን አጠናክረው መከናወን እንዳለባቸውም አሳስበዋል ።
በመጨረሻም በየወሩ የተተገበሩ ተግባራት በየደረጃቸው የመረጃ ጥራት ተሰርቶላቸው ጤናማ የሆነ ስራ ተገምግሞ ወደ መረጃ ቋት እንዲገባ አሳስበዋል።
በመድረኩም የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሀኢሻ አበቴ ፣ የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ማኔጅመንት አካላት እና ሁሉም ባለሙያዎችም ተገኝተዋል ።
04/05/2026
በሀላባ ዞን የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት አጠቃላይ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገመ ነው ።
ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም በሸኖ
የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት አጠቃላይ የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን ሁሉም የጽህፈት ቤት ባለሙያዎች በተገኙበት የበጀት አመቱን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ ክንውን እየገመገሙ ይገኛሉ ።
ለግምገማ የተዘጋጀውን ሰነድ የየስራ ክፍሉ አስተባባሪ አማካኝነት በሰፊው እየቀረቡ እያስገመገሙ ይገኛሉ ።
የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሃኢሻ አበቴ የግምገማውን መድረክ የመግቢያ ንግግር በማድረግ በይፋ አስጀምረዋል ።
02/05/2026
አሚን ሆስፒታል በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል ለመገንባት መሠረተ-ድንጋይ ተጣለ።
ሚያዚያ 24/2018 ሀላባ ቲቪ
በመርሐግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር መሐመድ ኑርዬ፣ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባዔ ክብርት መነቴ ሙንድኖ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙዔል ዳርጌ፣ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን፣ የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሙበራ ከማል፣ ሌሎች የክልል፣ የዞን፣ የወረዳዎችና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሐይማኖት መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
30/04/2026
በሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም በዌራ ዲጆ ወረዳ በቀበሌና በወረዳ ለሚገኙ የስርዓተ ምግብ አባላት ሲሠጥ የነበረ የማህበረሰብ መማማሪያና ሰርቶ ማሳያ (Community Lab) ስልጠና ተጠናቀቀ።
ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም
በሸኖ
በዌራ ዲጆ ወረዳ በሰቆጣ ቃል ኪዳን ፤ ሞዴል ቀበሌና ወረዳን ለመፍጠር በታለሙ አራት ቀበሌያት ለሚገኙ ለቀበሌና ለወረዳ የስርዓተ ምግብ አባላት በማህበረሰብ መማማሪያና ሰርቶ ማሳያ (Community Lab) ላይ በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት የስርዓተ ምግብ ዘርፍ ፤ በጤና ሚኒስቴር የአለም አቀፍ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ ኢኒስቲቲውት እንዲሁም በሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ከዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ጋር በትብብር ሲሠጥ ቆይቷል።
የስልጠና ማጠቃለያ መድረኩን የወረዳው የጤና ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሀዕሻ አበቴ እና በማ /ኢ / ክ /መንግስት በርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት የስቆጣ ቃል ኪዳን ሞዴል ወረዳ ኢኒሼቲቭ አማካሪ አቶ አንዷለም መንግስቱ የመሩት ሲሆን
በማጠቃለያው አቶ አንዷለም መንግስቱ እንዳሉት የስልጠናው ዋና አላማ የማህበረሰብ መማማሪያና ሰርቶ ማሳያ መርሆችን በመከተል አካባቢያዊ የስርዓተ ምግብ ችግሮችን በመለየት፤ ነባራዊ ሁኔታ ግምት ዉስጥ ያስገቡ ነባርና አዳዲስ የመፍትሄ ሀሳቦች በመጠቀም ለአካባቢው የስርዓተ ምግብ ችግሮች አካባቢያዊ መፍትሄዎችን በማበጀት ፤ በመተግበርና ውጤታማ የሆኑ መፍትሄዎችን ወደ ሌሎች አካባቢያዎች ማስፋት በመሆኑ በአተገባበሩ ላይ ሁሉም አባላት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የወረዳው የጤና ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሀዕሻ አበቴ በበኩላቸው ለዓላማው መሣካት ሁሉም ባለድርሻ አካላት እገዛና ክትትል እንዲያደርጉ አስገንዝበው የማህበረሰብ መማማሪያና ሰርቶ ማሳያ አባላቶች በተቀመጠው የድርጊት መርሃ ግብር መሠረት ተግባራቶችን እንዲከውኑ አሳስበዋል።
በመድረኩም በማ /ኢ / ክ /መንግስት በርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት የስቆጣ ቃል ኪዳን ሞዴል ወረዳ ኢኒሼቲቭ አማካሪ አቶ አንዷለም መንግስቱ ፣ የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሀዕሻ አበቴ ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የቀበሌ ሊቀመንበሮችና ስራ አስኪያጆች ፣ ጤና ኤክስቴንሽና የግብርና ባለሙያዎች፤ የት/ት ቤት ርዕሰ መምህራን እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
30/04/2026
በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት በተለያዩ ቀበሌያት ቤት ለቤት የ TB contact case screeng ስራ (TB)ልየታ ዘመቻ ስራዎች ተጠናክረው እየተተገበሩ ይገኛሉ ።
28/04/2026
የማህበረሰብ መማማሪያና ሰርቶ ማሳያ (Community Lab) ስልጠና በዌራ ዲጆ ወረዳ በሰቆጣ ቃል ኪዳን ሞዴል ቀበሌና ወረዳን የመፍጠር ኢኒሼቲቭ በተመረጡ አራት ቀበሌያት እየተሰጠ ይገኛል።
ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም
በሸኖ
በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ በሰቆጣ ቃል ኪዳን ሞዴል ቀበሌና ወረዳን የመፍጠር ኢኒሼቲቭ የማህበረሰብ መማማሪያና ሰርቶ ማሳያ (Community Lab) ስልጠና በተመረጡ አራት ቀበሌያት እየተሰጠ ይገኛል።
የስልጠናውን መድረክ የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሀዕሻ አበቴ የመግቢያ ንግግር በማድረግ በይፋ አስጀምረዋል ።
ስልጠናው በጤና ሚኒስቴር የአለም አቀፍ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ኢንስቲቲዩት ፤በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት የስርዓተ ምግብ ዘርፍ እንዲሁም የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ከዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ጋር በትብብር እየተሰጠ ይገኛል።
የማህበረሰብ መማማሪያና ሰርቶ ማሳያ የማህበረሰብ መማማሪያና ሰርቶ ማሳያ ማለት የተለያዩ ዘርፈ ብዙ አካላትን ወደ አንድ መድረክ በማምጣት በማህበረሰብ ደረጃ የስርዓተ ምግብ ችግሮችን በመለየት፤ የአንድን አካበቢ ነባራዊ ሁኔታ ግምት ዉስጥ ያስገቡ ነባርና አዳዲስ የመፍትሄ ሀሳቦች የሚፈልቁበት እና የሚተገበሩበት ስልት ነዉ፡፡
የማህበረሰብ መማማሪያና ሰርቶ ማሳያ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ የሚዋቀር ሲሆን አብዛኛዉ የምግብ-ስርዓትና ኒዉትሪሽን ምክር ቤት አባላትን ያካተተ በመሆኑ ምንም ዓይነት የሃላፊነት መደበባለቅ አይፈጥርም ፡፡
የማህበረሰብ መማማሪያና ሰርቶ ማሳያ የሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራም እና ሞዴል ወረዳ ኢንሼየቲቭ የማስፈጸሚያ ስልት ነው ፡፡ በህፃናት ላይ የሚከሰት የመቀንጨር ችግርን ለመለየት አሰቸጋሪ እና ዉስብሰብ በመሆኑ ከጤናው ሴክተር በተጨማሪ የሌሎች ሴክተሮችንም ምላሽ እና ቅንጅት የሚፈለግ በመሆኑ እና ማህበረሰቡን ያላሳተፈ ትግበራ ውጤታማ ስለማይሆን እና በተለመደው የአሰራር መንገድ በመሄድ ለውጥ እንደማይመጣ ስለታመነ የማህበረሰብ መማማሪያና ሰርቶ ማሳያ አስፈለጊ ሆኗል፡፡
በመድረኩም የዌራ ዲጆ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሀዕሻ አበቴ ፣ ከተለያዩ ቀበሌያዎች የተወጣጡ የሀይማኖት አባቶች ፣ የቀበሌ ሊቀመንበሮች ፣ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችም እና ሌሎችም ይገኙበታል ። ስልጠናው ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።