የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council

የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council

Share

የቻግኒ ከተማ ምክር ቤትንና ከተማዊ
አጠቃላይ እንቅስቃሴ እናደርሳለን፡፡
ለእውነተኛና ፈጣን መረጃዎች ይወዳጁን፤ ይከታተሉን!

Photos from Chagni communication's post 01/06/2026
Photos from የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council's post 29/05/2026

‎በቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ስር የሚገኙ የቀበሌ ምክር ቤቶች የ2018 በጀት አመት የግንቦት ወር ጉባኤ በቀረበዉ አጀንዳ ላይ በዛሬው እለት ውይይት አካሄደዋል/////////////////////
‎ግንቦት 21/2018 ዓ ም (ቻግኒ ከተማ ምክርቤት)
‎የጉባኤ አጃንዳ፡-
‎አጀንዳ1:- ወቅታዊ የወባ ወረርሽኝእና የአካባቢ ቁጥጥር ስራዎች በተመለከተ
‎ በአጠቃላይ የቀበሌ ምክርቤቶች በወቅታዊ የወባ ወረርሽኝና የአካባቢ የቁጥጥር ስራዎች አስመልክቶ ውይይት አደርገው እና በቀጣይ በየአካባቢዉ በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ የጋራ አቅጣጫ በመያዝ እንዲሁም ከቀበሌ ም/ቤት አባላት በሚጠበቁ ጉዳዮች ዙሪያ በቂ ዉይይት በማድረግ በዕለቱ በተገኙ የምክር ቤት አባላት የቀረበዉን አጀንዳ በማፅደቅ ጉባኤውን በስኬት አጠናቀዋል።

Photos from የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council's post 27/05/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ተዋበ ምህረት ለ1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን መልዕክት አስተላለፉ!

‎ግንቦት 19/09/2018 ዓ.ም ቻግኒ ከተማ ምክር ቤት

‎አቶ ተዋበ ምህረት በመልዕክታቸው ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺ 447ኛዉ ዒድ አል አድሃ(አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

‎በዓሉን ስናከብር ቅንነትን፣ መልካምነትን፣ መታዘዝን፣ በጎ አድራጊነትንና ትኅትናን በሕይወታችን ተግባራዊ በማድረግ ሊሆን ይገባል።

‎በዓሉ፤ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።

‎​መልካም_በዓል!!
‎ኢድ_ሙባረክ!!

Photos from የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council's post 16/05/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 47ኛ መደበኛ ጉባኤ የቀጣይ አቅጫዎችን
‎አስቀመጠ *************************

‎ግንቦት 08/09/2018 ዓ.ም ቻግኒ ከተማ ምክር ቤት

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ተዋበ ምህረት በቀረበው የ2018 በጀት አመት የተመረጡ የተቋማት የ9ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ያቀረቧቸው የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች
‎~የንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤትን የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የሚያደርገው ጥራት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንዲሚገባ አፈ ጉባኤው አስገነዘበ።
‎~ አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ ለተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት መቻል አለበት ?
‎~ማደያዎች በአግባቡ ነዳጅና ቤንዚን በህጋዊ መንገድ እንዲሰራጩ በትኩረት ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋል ።
‎ ~ የግብዓት አቅርቦት በተመለከተ በተለይ ኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት አለበት።
‎~ከንግድ አኳያ ህገወጥ ንግድን ከመቆጣጠር አኳያ በትኩረት ስራ መሰራት አለበት?
‎~ ከንግድ አኳያ የነዳጅና የቤንዚን ስርጭት በትኩረት መሰራት ?
‎~ከትራንስፖርት ጽህፈት ቤት አኳያ የትራንስፖርት አገልግሎት በደንብና አሰራር መሰረት መመራት አለበት?
‎~የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ በትኩረት ስራ መሰረት አለበት ?
‎~ ትራንስፖርት አኳያ ያለአግባብ ከታሪፍ ውጭ ከሚቀበሉት አሽከርካሪዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ስራ መሰራት አለበት በማለት አሰስቧል ? የቀረበው ሪፖርት በሙሉ ድምፅ በእለቱ በተገኙ የምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል። የአንድ ቀን ጉባዔ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ።

Photos from የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council's post 16/05/2026

‎የቻግኒ ከተማ ም/ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 47ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ/////////////////

‎ ግንቦት 08/09/2018ዓ.ም
‎ ቻግኒ ከተማ ም/ቤት

‎➢በዚህ ጉባኤ የሚመከርባቸው አጀንዳዎቹም:-
‎1.የዕለቱን አጀንዳዎች ማፀደቅ
‎2.የ4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 46ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማፅደቅ
‎3.በ4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 46ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ማዳመጥ
‎4.የቻግኒ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት አመት የተመረጡ ተቋማት የ3ኛው ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት መገምገም
‎~ የቋሚ ኮሚቴዎች የክትትልና ቁጥጥር የውሳኔ ሀሳብ ይቀርባል። ስለዚህ በአጠቃላይ ምክር ቤቱ የአንድ ቀን ውይይት ያድርገል የቀረቡ አጃንዳዎችም በዕለቱ በተገኙ ምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።


Photos from የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council's post 15/05/2026

‎የቻግኒ ከተማ ም/ቤት በ07/09/2018 ዓ ም የሴቶች ፎርም የቻግኒ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት አመት የተመረጡ የተቋማት የ3ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገመ አካሄዱ።


‎ግንቦት 07/09/2018ዓ.ም
‎ ቻግኒ ከተማ ም/ቤት



Photos from የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council's post 08/05/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤትን ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬ ተጀመረ ////////////////////////

‎ሚያዚያ 30/2018ዓ/ም የቻ/ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤትን የ2018 በጀት አመት የ9ወር የእቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር አደረገ።

‎የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት በተዘጋጀው ቼክሊስት መሠረት የ2018 በጀት አመት የ9ወር እቅድ አፈፃፀማቸውን ሪፖርትም በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ፈንታሁን ደማም በኩል ቀርቧል።

‎ሰለሆነም በቀረበው ሪፖርት ላይ በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ማብራሪያ እንዲሁም ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎች እንደሚከተሉት አንስተዋል
‎~ ያለአግባብ ዋጋ በመጨመር ኑሮ ውድነትን የሚያባብሱ አካላት ላይ እየተወሰደ ያለ እርምጃ ካለ ቢገለፅ?
‎~ወቅታዊ የነዳጅ እጥረትን ምክንያት በማድረግ ህገወጥ ተግባራትን የሚያከናውኑ አካላትን በመቆጣጠር ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው እንዲስተካከሉ ከማድረግ አኳያ እየተሰራ ስራ ካለ ቢገለፅ ?
‎~ የሰንበት ገበያን በማመቻቸት አምራቾችንና ሸማቹን በማገናኘት የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እየተሰራ ስራ ካለ ቢገለፅ
‎~ጋርቾን በመደገፍና የገበያ ትስስር በመፍጠር ገበያ እንዲያረጋጋ ከማድረግ አኳያ የተሰራ ስራ ይብራራ
‎~ነዳጅ ከማደያ ከቀዱ በኋላ ምንም ዓይነት የትራንስፖርት አገልግሎት ሳይሰጡ ነዳጁን በህገወጥ መንገድ በመሸጥ ተግባር የተሰማሩ አሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ከትራንስፖርት ተቋም ጋር ያለው ቅንጅታዊ ስራ ምን ይመስላል ?
‎~የሚመጣውን ናፍጣና ቤንዚን በአግባቡ እንዲሰራጭ እንዲሁም ስራ ላይ እንዲውል ተቋም እያደረገ ያለው የክትትልና ቁጥጥር ስራ ይብራራ? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ተነስተው በቂ ውይይት ከተደረገ በኋላ በጽ/ቤት ኃላፊና በማኔጅመንቱ አባላት በኩል ምላሽና ማብራሪያ እየተሰጠባቸው ይገኛል።

Photos from የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council's post 01/05/2026


‎በቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ስር የሚገኙ ቀበሌ ምክር ቤቶች የ2018 በጀት አመት የሚያዚያ ወር ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች በዛሬው እለት ውይይት አካሄደዋል/////////////////////
‎የሚያዚያ 23/2018 ዓ ም
‎የጉባኤ አጃንዳዎች፡-
‎አጀንዳ1:- የትምህርት ስራዎች በተመለከተ
‎አጃንዳ2:- የፀጥታ ስራዎች ሁኔታ በተመለከተ
‎አጃንዳ3፡- የጤና ሰራዎች አኳያ፡-ወቅታዊ የወባ ወረርሽኝ ፣የትራኮማ በሽታ እና መንስኤ በተመለከተ
‎አጀንዳ4:- የቀበሌ የ9ወር የማህበራዊ ፍርድ ቤት በተመለከተ
‎ በአጠቃላይ በቀበሌ ምክርቤቶች ሰፊ ማብራሪያና ውይይት አደርገው በዕለቱ በተገኙ የምክር ቤት አባላት በማፅደቅ ጉባኤውን አጠናቀዋል።

Photos from የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council's post 10/04/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ተዋበ ምህረት
‎ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለትንሳኤ በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

‎ቻግኒ ፡ሚያዝያ 3/2018 ዓ.ም አቶ ተዋበ ምህረት መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

‎ በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣የፍቅር፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ በዓል እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ ፤በዓሉ በሚከበርበት ጊዜ ደጋፊና ረዳት የሌላቸዉን ወገኖቻችንን በማሰብና በማገዝ በአሉን ማክበር ይኖርብናል በማለት አሳስበዋል ።

‎በመጨረሻም የትንሳኤ በዓሉን የመተሳሰብና የመረዳዳት መንፈስ እንድናሳልፍ ጥሪን አስተላልፋለሁ።

‎በድጋሚ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

‎ ታምፁናስ!

‎ ***መልካም ፋሲካ በዓል ***

‎አቶ ተዋበ ምህረት የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ

Photos from የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council's post 31/03/2026


‎በቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ስር የሚገኙ 5ቱ የቀበሌ ምክር ቤቶች የ2018 በጀት አመት የመጋቢት ወር ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች በዛሬው እለት ውይይት አካሄደዋል///////////////////////////////
‎በመጋቢት 22/2018 ዓ ም
‎የጉባኤ አጃንዳዎች፡-
‎አጀንዳ1:- የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ በተመለከተ
‎አጃንዳ2:-የቀበሌ ስራ አስፈፃሚ ሹመት ማፅደቅ
‎አጃንዳ3፡- የጤና ሰራዎች አኳያ
‎አጀንዳ4፡-የሰላምና የድህንነት ስራዎችን መገምገም
‎አጀንዳ5:-የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ በተመለከተ
‎ በአጠቃላይ በ5ቱ ቀበሌ ምክርቤቶች ሰፊ ማብራሪያና ውይይት አደርገው በዕለቱ በተገኙ የምክር ቤት አባላት በማፅደቅ ጉባኤውን አጠናቀዋል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Amhara Region?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Chagni
Amhara Region