16/04/2022
የላሃ ከተማ አስተዳደር የላሃ ከተማ ማዘጋጃ ቤትና የመሎ ኮዛ ወረዳ ከ/ል/ኮ/ጽ/ቤት በጋራ በመሆን
ለማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጆችና ባለሙያዎች በመሬት ሀብት ቆጠራ ዙርያ እና የይዞታ ማህደር አደረጃጀት ዙሪያ
የጎፋ ዞን ከ/ል/ኮ መምሪያ መሬት ዘርፍ ስልጠና ሰጠ።
ሚያዝያ 8/8/2014 ዓ/ም
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በጎፋ ዞን በላሃ ከተማ አስተዳደር የላሃ ማዘጋጃ ቤት/Gofa Zone Laha Town Administration Laha, Government Organization, Round wolaita, Arba Minch'.
16/04/2022
የላሃ ከተማ አስተዳደር የላሃ ከተማ ማዘጋጃ ቤትና የመሎ ኮዛ ወረዳ ከ/ል/ኮ/ጽ/ቤት በጋራ በመሆን
ለማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጆችና ባለሙያዎች በመሬት ሀብት ቆጠራ ዙርያ እና የይዞታ ማህደር አደረጃጀት ዙሪያ
የጎፋ ዞን ከ/ል/ኮ መምሪያ መሬት ዘርፍ ስልጠና ሰጠ።
ሚያዝያ 8/8/2014 ዓ/ም
23/11/2021
በጎፋ ዞን በላሃ ከተማ አስተዳደር አዲሱ የከተማ አደረጃጀትን ጨረሰው በቅርቡ ወደ ሥራ ሊገቡ ነው።
በአዲሱ የከተማ አደረጃጀት የላሃ ከተማ አስተዳደር በቀበሌ፣በቀጠና፣በሠፈራና በጣቢያ የተደራጀ ሲሆን፦ከተማችን አንድ/1/ ቀበሌ፣ሦስት/3/ቀጠና፣አስሪ/10/ሠፈረ እና ሠላሳ ስምንት/38/ ጣቢያዎች አሉት።በአደረጃጀት የከተሞችን የከተማ ልማት አጀንዳዎችን ማሳካት የአጀንዳዎች መተግበሪያ መንገድ ነው!!
በወላይታ ዞን በኤሌክትሪክ ከፍተኛ የኃይል ባለ 132KV ማስተላለፊያ መስመር
ላይ ስርቆት በመፈጸሙ ከፍተኛ ኪሳራ መድረሱ ተገለጸ
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ አስተዳደር በሁምቦ
ላሬና ቀበሌ በኤሌክትሪክ ከፍተኛ 132KV የኃይል ማስተላለፍያ ታወር እና
መስመር ላይ የስርቆት ወንጀል መፈጸሙንና በዚሁም ምክንያት በደቡብ ኦሞ ዞን
፣ በጎፋ ዞን ሙሉ በሙሉ እና በጋሞ ዞን በከፊል የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ ሪጅን ዋና ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ
ዘበርጋ ገልጸዋል።
አቶ አለማየሁ እንደተናገሩት አጠቃላይ ከ3 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ከፍተኛ
የኃይል ተሸካሚ መስመሮች መኖራቸውን፣ ከወላይታ ሰብስቴሽን ተነስቶ ለሦስት
የደቡብ ክልል ዞኖች አገልግሎት የሚሰጠው በወላይታ ዞን የስርቆት ጥቃት
የደረሰበት የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ ታወር ከአራት አመት በፊት ከሀገር ውጪ
በመጡ ማቴርያሎች ሲጠገን የአንዱ ታወር ዋጋ የትራንስፖርትና የእጅ ስራ ዋጋ
እንዲሁም ኤሌክትሪክ በመቋረጡ የሚገኘውን ገቢ ሳይጨምር 1.5 ሚሊዮን
የኢትዮጵያ ብር የሚሰራ መሆኑን በዚህ ስርቆት ሁለት ታወሮች የወደቁና
በተመሳሳይ በዚሁ ቦታ ላይ 20 ታወሮች ብረታቸው ተመልምሎ የተገኘና
እነኚህም እያንዳንዳቸው በእንጨት ለመቀየር ከ500,000 ሺህ ብር በላይ
የሚያስወጡ መሆናቸውን በመጥቀስ የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚው ምሶሶ
በሌቦች በመዘረፉ ምክንያት በመንግስትና የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ
በሆኑ ማህበረሰቦች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ መድረሱንና በአቅራቢያ የሚገኙ
ሌሎችም የኃይል ተሸካሚ መስመሮች በሌቦች ጥቃት እየደረሰባቸው በመሆኑ
በቀጣይ አገልግሎት መስጠት በማይችሉበት ሁኔታ በአደጋ ላይ መሆናቸውን
በመናገር በሌቦች በዝርፍያ ከጥቅም ውጪ የሆነው የኤሌክትሪክ ኃይል
ተሸካሚው ምሶሶ በአጭር ጊዜ ለመገንባት ስለማይቻል ለጊዜው በእንጨት
ምሶሶ በመስራት የኤሌክትሪክ መስመሩን በማገናኘት የኤሌክትሪክ አገልግሎት
ለተቋረጠባቸው ለሦስቱ ዞኖች ነዋሪዎች አገልግሎት ለመስጠት ጥረት
እንደሚደረግ አቶ አለማየሁ ዘበርጋ ተናግረዋል።
የደቡብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮምኒኬሽን ቢሮ ስራ አስኪያጅ አቶ
ያዕቆብ ታሪኩ በወላይታ ዞን በተለያየ ጊዜ በተደራጁ ሀይሎች በከፍተኛ
በመካከለኛና በዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመሮች ላይ በተደጋጋሚ
ስርቆት የሚፈጸም በመሆኑን፣ የመጀመሪያ ተጎጂዎች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ
አገልግሎትና በስራችን የሚገኙ ደንበኞቻችን መሆናቸውንና ከዚህም በተጨማሪ
የኤሌክትሪክ መስመሩን የሚሰርቁት ግለሰቦች የሰረቁትን የኤሌክትሪክ መስመር
ለሌላ ህገወጥ የኤሌክትሪክ የመስመር ዝርጋታ የሚጠቀሙበትና በሰው
ህይወትና ንብረት ላይ ተጨማሪ ጉዳት የሚያመጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በወላይታ ዞን በከፍተኛ ሁኔታ የተስፋፋውን የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመሮችን
የስርቆት ወንጀል ለማስቆም የዞኑ የጸጥታ አካላት ከፍተኛ ሚና መጫወት
እንዳለባቸው፣ የአካባቢው ህብረተሰብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ
ማቴሪያሎችን እንደራሱ ንብረት በአግባቡ መጠበቅና ሌቦችን ለህግ አሳልፎ
መስጠት እንዳለበት የደቡብ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ስራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ
ታሪኩ ተናግረዋል።
በወላይታ ዞን በከፍተኛ በመካከለኛ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ
በከፍተኛ ሁኔታ እየደረሰ ያለውን የስርቆት ወንጀል ከመከላከል አንጻር ምን
እየተሰራ እንዳለ ምላሽ እንዲሰጡን የወላይታ ዞን ዐቃቤ ህግ መምሪያ የልዩ ልዩ
ወንጀል ጉዳዮች ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አሸናፊ ቶራ በወላይታ ዞን
በተደጋጋሚ በኤሌክትሪክ በከፍተኛ እና በዝቅተኛ መስመሮች ላይ የስርቆት
ወንጀል
25/04/2021
እንኳን የላሃ ከተማ አስተዳደር ምስረታ በዓል በሠላም አደረሳችሁ/አደረሰን !!!
23/04/2021
እንኳን ለላሃ ከተማ አስተዳደር የምስረታ በዓል ዋዜማ በሠላም አደረሳችሁ/አደረሰን !!!
02/04/2021
በመሎ ኮዛ ወረዳ በላሃ ከተማ ውስጥ ለውስጥ በሳሊኒ ድርጅት እየተሰራ ያለው የድች ሥራ በከፈል
09/03/2021
Welcome to Laha Town Administration!!
20/02/2021
በጎፋ ዞን በመሎ ኮዛ ወረዳ በላሃ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ ለውስጥ በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰሩ የድች ሥራ ይህንን ይመስላል!!!
በላሃ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የላሃ ከተማ ፅዳትና ውቤት ዙሪያ ከከተማ ማህበረሰብና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ
09/02/2021
በጎፋ ዞን በመሎ ኮዛ ወረዳ በላሃ ከተማ ውስጥ ለውስጥ በሳሊኒ ድርጅት የተሠሩ ድችና ቱቦ ቀበራ ሥራ በከፊል...
05/02/2021
እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ ከላሃ ከተማ ማዘጋጃ ወደ ላሃ ከተማ አስተዳደር !!!