ጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

Share

Follow us on our official site

Photos from ጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት's post 23/04/2026

የቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት የኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) online Course's ስልጠና በሁሉም ዘርፊ ባለመዘናጋት ሊወሰድ እንደሚገባ አሳሰቡ፡፡

ኤዞ፦15/082018 ዓ.ም (ቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ

የቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኅላፊ የሆኑት አቶ አማኑኤል አበበ የኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) online Course's ስልጠና በሁሉም ዘርፊ ባለመዘናጋት ሊወሰድ እንደሚገባ ያሳሰቡ ሲሆን ጠቀሜታው ዘረፈ ብዙ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

የኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) ተነሳሽነት በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማሳደግና ለዜጎች የቴክኖሎጂ ክህሎትን ለማጋራት የታለመ ታላቅ ብሔራዊ ፕሮጀክት ሲሆን ይህ ስልጠና በዋናነት በኢፌዴሪ መንግሥት እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥት በጋራ ትብብር የሚካሄድ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የሥልጠናው ዓላማ 5 ሚሊዮን ኮደሮችን 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በኮዲንግ (Coding) እና በዲጂታል ክህሎቶች ማሰልጠን እና በዘርፉ ወጣቶች በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና በራሳቸው የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን እንዲፈጥሩ ማስቻል ይገኙበታል።

የሚሰጡ ስልጠናው አይነቶች በዋናነት በነዚህ አራት ቁልፍ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ሆኖ :-የሞባይል መተግበሪያዎችን (Apps) ለመስራት፣ : መረጃዎችን በመተንተን ውሳኔ ሰጪነትን ማሳደግ፣ : የኮምፒውተር ፕሮግራም መሰረታዊ ዕውቀት እና ወይም AI ፡-ኮምፒውተሮች ወይም ማሽኖች እንደ ሰው የማሰብ፣ የመማር፣ ችግሮችን የመፍታት እና ውሳኔ የመስጠት ችሎታ እንዲኖራቸው ተደርገው የሚሰሩበት የቴክኖሎጂ ዘርፍ በማወቅ እውቀትን እንድንቀስም እናንዲሁም አለማችን በቴክኖሎጂው ያለችበትን ደረጃ ተረድተን አብረን እንድንጓዝ የሚረዳን ስለሆነ በየዘርፉ ስልጠናዎች ባለመዘናጋት ሊወሰዱ ይገባል ብለዋል፡፡

👍ለመመዝገብ፦ የድረ-ገጹን ሊንክ Ethiocoders.et ብላችሁ መጀመር ትችላላችሁ።

22/04/2026

በፋይዳ ምዝገባ ወቅት የሰጡት ስልክ ቁጥር ስህተት ነበረው? ወይስ ከምዝገባ በኃላ ስልክ ቁጥር ቀይረዋል?

እንዴት ማስተካከል እችላለው ብለው እያሰቡ ነው?

1. ለፋይዳ ሲመዘገቡ በሌላ ሰው ስልክ ቁጥር ተመዝገበው ከነበረ እና አሁን ወደ ራስዎ ስልክ ቁጥር ለመቀየር ከፈለጉ ድረገፅ https://id.et/update ላይ በመግባት በአካል መሄድ ሳያስፈልግዎ መቀየር ይችላሉ። (ያስተውሉ፡ በዚህ ሂደት ወደ ነባሩ ስልክ የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል ወይም OTP ስለሚላክ ስልኩ በእጅዎ ሊሆን ይገባል)

10/04/2026

ፋይዳ ተራዝሟል‼️

የፋይዳ መታወቂያን ከባንክ ሂሳብ ጋር ለማጣመር ተቅምጦ የነበረው የጊዜ ገደብ ተራዝሟል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ለማጣመር ተቀምጦ የነበረው የመጋቢት 30/2018 ዓ.ም የጊዜ ገደብ ለአንድ ጊዜ እንዲራዘም መወሰኑ ተገልጿል።

እስካሁን የተመዘገበው ሰው ቁጥር አመርቂ ባለመሆኑ እና በአንዳንድ ባንኮች ላይ የታዩ የሲስተም ችግሮችን ለመፍታት ሲባል ለአንድ ጊዜ እንዲራዘም ተወስኗል።

የተራዘመበት ትክክለኛ ቀን እስካሁን ያልተወሰነ ሲሆን በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ ብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።

እንዲራዘም የተወሰነው ብሔራዊ ባንክ እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ተወያይተውበት ነው።

ህብረተሰቡ በሊንክ ወይም ደግሞ በአካል በመቅረብ ምዝገባውን እንዲያከናውን እና ባንኮች የቴክኒክ ችግሮችን እንዲያስተካክሉ መመሪያ ተሰጥቷል፡፡

02/04/2026

የኢትዮ ኮደርስ (5 Million Ethiopian Coders) ስልጠና ለምን ለBPR አስፈላጊ ሆነ?

የዲጂታል ብቃት መለኪያ፦ አዲሱ የመንግስት አሰራር ወደ ዲጂታላይዜሽን እያመራ በመሆኑ፣ ማንኛውም ባለሙያ መሰረታዊ የኮምፒውተር እና የቴክኖሎጂ እውቀት እንዳለው ማረጋገጫ ይፈለጋል።

ተጨማሪ ነጥብ፦ በስራ ምደባ ወቅት ከስራው ባህሪ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስልጠናዎች መኖራቸው በምዘናው ወቅት የተሻለ ነጥብ ለማግኘት ይረዳል።

የአመለካከት ለውጥ፦ ስልጠናውን መውሰድዎ ራስዎን ለማሻሻል እና አዳዲስ አሰራሮችን ለመቀበል ዝግጁ መሆንዎን ያሳያል።

አሁንም አልረፈደም!🏃‍♂️🏃‍♀️ ስልጠናው በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ ባሉበት ሆነው መከታተል እና ሰርተፊኬቱን ማግኘት ይችላሉ።

በተለይ በዳታ ሳይንስ (Data Science)፣ በዌብ ሳይት ዝግጅት (AI Development) እና በአንድሮይድ መተግበሪያዎች (Android Development and programming Development ) ዙሪያ የሚሰጡት ትምህርቶች ለስራዎ ትልቅ አቅም ይሆኑዎታል።

🔗 ለመመዝገብ፦ [የድረ-ገጹን ሊንክ Ethiocoders.et ብላችሁ መጀመር ትችላላችሁ።

24/03/2026
22/03/2026

የኢትዮ ኮደርስ (5 Million Ethiopian Coders) ስልጠና ለምን ለBPR አስፈላጊ ሆነ?

የዲጂታል ብቃት መለኪያ፦ አዲሱ የመንግስት አሰራር ወደ ዲጂታላይዜሽን እያመራ በመሆኑ፣ ማንኛውም ባለሙያ መሰረታዊ የኮምፒውተር እና የቴክኖሎጂ እውቀት እንዳለው ማረጋገጫ ይፈለጋል።

ተጨማሪ ነጥብ፦ በስራ ምደባ ወቅት ከስራው ባህሪ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስልጠናዎች መኖራቸው በምዘናው ወቅት የተሻለ ነጥብ ለማግኘት ይረዳል።

የአመለካከት ለውጥ፦ ስልጠናውን መውሰድዎ ራስዎን ለማሻሻል እና አዳዲስ አሰራሮችን ለመቀበል ዝግጁ መሆንዎን ያሳያል።

አሁንም አልረፈደም! 🏃‍♂️🏃‍♀️ ስልጠናው በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ ባሉበት ሆነው መከታተል እና ሰርተፊኬቱን ማግኘት ይችላሉ። በተለይ በዳታ ሳይንስ (Data Science)፣ በዌብ ሳይት ዝግጅት ( AI Development) እና በአንድሮይድ መተግበሪያዎች (Android Development and programming Development ) ዙሪያ የሚሰጡት ትምህርቶች ለስራዎ ትልቅ አቅም ይሆኑዎታል።

🔗 ለመመዝገብ፦ [የድረ-ገጹን ሊንክ Ethiocoders.et ብላችሁ መጀመር ትችላላችሁ።

Photos from ጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት's post 21/03/2026

Ethio coders ኮርሶች ተምሮ ማጠናቀቅ ወሳኝነቱ ጠንክሯል።

16/03/2026

ባሉበት ሆነው የሚወስዱት ነፃ የኦንላይን ስልጠና
በአምስት ሚልዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደሮች ኢንሼቲቭ በመሰጠት ላይ የሚገኙትን
🌐 በዌብ -ፕሮግራሚንግ
🤖 በአንድሮይድ ማበልፀግ
📊 ዳታ ሳይንስ እንዲሁም
🧠 አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች ዙርያ ያተኮሩ የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎትን ለማዳበር የሚያስችሉ ነጻ የኦንላይን ሥልጠናዎችን https://ethiocoders.et/ በዚህ ሊንክ ላይ ያገኟቸዋል፡፡

Photos from ጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት's post 14/03/2026

የፌስቡክ አካውንትዎን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ነጥቦች ተግባራዊ ያድርጉ

በሀገራችን ኢትዮጵያ ከ12 ሚሊየን በላይ እንዲሁም በዓለማችን 3.7 ቢሊየን ገደማ ንቁ ወርሃዊ ተጠቃሚዎች (Active users) ያሉት ፊስቡክ የማሕበራዊ ትስስር ገጽ፤ በርካታ መንግስታዊ እና የግል ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ከተገልጋዮች ጋር ቅርብ የሆነ ግንኙነት ለመፍጠር ይህንኑ ፕላትፎርም ይጠቀማሉ፡፡

ይህን ያህል በርካታ ቁጥር ተቃሚዎች ያሉት የፌስቡክ ገጽ በየእለቱ ከሦስት መቶ ሺ እስከ ስድስት መቶ ሺ ያህል የፕላትፎርሙ ተጠቃሚዎችን አካውንቶችን ሰብሮ የመግባት (log in) የጥቃት ሙከራዎች ያስተናገዳሉ፡፡ በርግጥ እነዚህ የጥቃት ሙከራዎቹ ከሙከራ ሳይዘሉ በፕላትፎረሙ ጠንካራ የደህንነት ስርአት ይከሽፋሉ፡፡

እነዚህን የጥቃት ሙከራዎች ለመከላከል ተቋማትም ይሁን ግለሰቦች የሚከተሉትን የጥንቃቄ መንገዶች ተግባራዊ ማድረግ ይገባቸል፡፡

11/03/2026

ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበሻል?

ፋይዳ ላንቺ ፋይዳው ብዙ ነው።

- ከትምህርት ገበታ ላይ ወደኃላ እንዳትቀሪ ፣
- በኢኮኖሚ ዘርፍ ንቁ ተሳታፊ እንድትሆኚ ፣
- የማሕበራዊ ዋስትና እና የጤና መድህን ተጠቃሚ መሆን እንድትችይ ፣
- እንዲሁም በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፍ ንቁ ተሳታፊ እንድትሆኚ ይረዳሻል።

#ፋይዳላንቺ #መታወቅ #በሀገርሽታወቂ

10/03/2026

የባንክ እና የቴሌብር ሒሳብዎን እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርዎን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር አላጣመሩም?

የባንክ እና የቴሌብር ሒሳብዎን እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርዎን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ማጣመር ከመቼውም ጊዜ በላይ ቀላል ሆኗል።

ባሉበት ሆነው የባንክ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የቴሌብር ሊንክ (ሱፐርአፕ) በመጠቀም ያጣምሩ ፤ ጊዜና ገንዘብዎን ይቆጥቡ።

የማጣመሪያ ሊንክ ሁሉንም በአንድ ላይ: https://id.et/connect ያገኙታል።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለሁሉም

Want your business to be the top-listed Government Service in Arba Minch'?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


ቆጎታ ኤዞ
Arba Minch'