02/09/2024
የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ቭድዩ ኮንፈረንስ ባለሞያ የሆኑት በኮድ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ግለሰቦችን በማሰልጠንና በማብቃት 5 ሚሊየን የኢኮደር ስልጠና በመሰለጠን በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል። ይህ ፕሮግራም የተነደፈው ዲጂታል ማንበብና መጻፍን ለማጎልበት እና ለተለያዩ የተሳታፊዎች ቡድን አስፈላጊ ክህሎቶችን ለመስጠት ሲሆን ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው ዲጂታል አለም ውስጥ እንዲበለጽጉ ያስችላቸዋል። ተነሳሽነቱ በቴክኒካል ክህሎት ላይ ያተኮረ ብቻ ሳይሆን ችግር መፍታት፣ ሂሳዊ አስተሳሰብ እና በተማሪዎች መካከል ያለውን ትብብር አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥቷል።
31/07/2024
ማስታወቂያ
ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን #ኮደሮችን ለማሰልጠን ያለመ ፕሮጀክት አስጀምራለች።
ለ3 ዓመታት ያህል የሚቆየው ይሄ ፕሮጀክት ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ (UAE) ጋር በመተባባር የሚተገበር ነው ።
ምን መማር ይቻላል ?
Android Kotlin Development Fundamentals
Data Science Fundamentals
Programming Fundamentals
ትምህርቱን እንዴት ማግኘት ይቻላል ?
ስልጠናዎቹ በዩዳሲቲ (Udacity) በተሰኘው ኦላይን የትምህርት ፕላትፎርም ተዘጋጅተው የቀረቡ ናቸው።
ሰልጣኞች ያለ አንዳች ክፍያ በነጻ ኮምፒውተራቸውን ወይም ስልካቸውን በመጠቀም መሰልጠን ይችላሉ።
ስልጠናዎቹ 6-7 የሚሆኑ ሳምንታትን የሚፈጁ ሲሆን በማጠቃለያው ላይ ሞያዊ ሰርተፊኬት ይሰጣል።
የስልጠናዎቹን ይዘት እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎች በተዘጋጀው ድረ-ገጽ (https://www.ethiocoders.et/) ይጎበኙ!
30/07/2024
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ይፋ የተደረገው የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ መመዝገቢያ ከዚህ የሚከተለው ነው።
https://ethiocoders.et/?fbclid=IwY2xjawEViplleHRuA2FlbQIxMQABHbKXpC38LYFp5uKN1iw7fzfDEmZfAY9ORS9MwSQC2ixSeNrOdbYfzDIi-A_aem_1ClHTqIh3Wfs53JfTNZ67g
Ethiopian coders initiative – Ethiopian coders initiative
Acquire the essential digital skills necessary to establish a promising career in the ever-evolving technology industry with our comprehensive, fully-funded courses.
30/07/2024
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አምሰት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪን አስጀመሩ
==========
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አምሰት ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስልጠና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አምሰት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪን አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም ኢንሼቲቪን ሲያስጀምሩ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የነገ ተስፋዎች የሆኑ ወጣቶች ስልጠናውን በጥሞና በመከታተል ስራ ፈጣሪ፣ኩባንያ ፈጣሪና በዓለም ገበያ ተወዳድረው የሚቀጠሩ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
ኢንሼቲቩ 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያ ዘመኑን በዋጀው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን ትልቅ ዕድል ወጣቶች በአግባቡ በመጠቀም ለኢትዮጵያ የነገ ተስፋ መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
የአምሰት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪ ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ ጋር በመተባባር የሚተገበር ሲሆን 5 ሚሊዮን ዜጎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በአርቲፎሻል ኢለጀንሽስና በተያያዥ የዲጂታላዜሽን ክህሎቶች የሚሰለጥኑበት ኢንሼቲቭ ነው።
ኢንሽቲቩ በቀጣይ 3 ዓመታት 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ኮደሮች እንዲፈጠሩ ያለመ ንቅናቄ እንዲፈጠር የሚሰራበት ሲሆን ይህንን ዕድል ኢትጵያዊ ወጣቶች እንዲጠቀሙበትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠይቀዋል።
25/07/2024
ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና እንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ብሮ ለጋሞ ዞን ሳይንስና እንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ለፈጠራ ስራ የተሻለ አፈጻጸም እና የሳይንስ ቀን በማክበር የተሳተፉ ወረዳ ትምህርት ቤቶች የተበረከተ የፈጠራ ስራ ቱል ኪት በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት በፈጠራ ስራ ድጋፍ እና ክትትል አስተባባሪ ለቆላ ሼለ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተሻለ አፈጻጸም ስላላቸዉ የተሰጠ
24/06/2024
one vision is equals to -----------
13/06/2024
የክላውድ ኮምፕዩቲንግ ወሳኝ
*********************************************
በኮምፒውተር ኢንዳስትሪ ማርሽ ቀያሪ ሊባሉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች በየግዜው ይከሰታሉ። ክላውድ ኮምፕዩቲንግ ምናልባት ከነዚህ ተጠቃሽ ቴክኖሎጂ ውስጥ አንዱ ሊሆን ይችላል። ቃሉን በቀጥታ ወደ አማርኛ ከተረጎምነው ዳመና ላይ ማስላት ሊሆን ይችላል፤ ይሁንና ይህን ዓይነት ትርጉም መስጠት ከቴክኖሎጂው መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳብ ጋር ይበልጥ ስለማይጎዳኝ የእንግሊዘኛውን ስያሜ መጠቀም የተሻለ ነው።
ክላውድ ኮምፒዩቲንግ በአጭሩ ሲገለጽ የኮምፒውተር አገልግሎቶች ማለትም ሰርቨሮች፣ ዳታ ማጠራቀምያዎች፣ አውታር መረቦች፣ ሶፍትዌሮች እና ሌሎች አገልግሎቶችን ኢንተርኔት (ክላውድ) ተጠቅሞ የሚያቀርብልን ቴክኖሎጂ ነው። ይህ ማለት ዳታ የምናስቀምጠው በኮምፒተራችን ሳይሆን፤ ሌሎች ድርጅቶች በሚቆጣጠሩት ኮምፒውተር ነው ማለት ነው። ያስቀመጥነውን ዳታ ማግኘት ስንፈልግ፣ ኢንተርኔትን ተጠቅመን ወደ የግላችን ኮምፒውተር መገልበጥ ወይም እዛው ክላውድ ላይ እያለ በማሰሻ (browser) ከፍተን ማየት እንችላለን።ይሁንና ክላውድ ኮምፒዩቲንግ ዳታ ማከማቻ ጎተራዎች ብቻ አይደለም በአገልግሎት መልክ የሚያቀርብልን፤ ማንኛውም ኮምፒውተራችን ላይ ማድረግ የምንችለውን ተግባር በተሻለ ፍጥነት እና ዋጋ ማከናወን የሚይስችለን ቴክኖሎጂ ነው።
ከክላውድ ኮምፕዩቲንግ መምጣት በፊት፤ ሶፍትዌር የሚያመርቱ እና የሚጠቀሙ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ብዙ ዓይነት ሶፍትዌር እና ሃርድዌር ገዝተው ይጠቀሙ ነበር። ይህ ውድና ውስብስብ ከመሆኑም በላይ፤ ለአጭር ጊዜ ብቻ መጠቀም የምንፈልገውን ሃርድዌር ከመግዛት ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረም። በዚህም ምክንያት ወደ ገበያ ለመግባት የሚፈልጉ ድርጅቶች ከጅምሩ ብዙ ወጪ ማውጣት ግድ ይላቸው ነበር። ድርጅቶች ከጅምሩ ምን ያክል የዳታ ማጠራቀምያ (storage)፣ የማስያ ጉልበት (processing power) ወዘተ…. እንደሚያስፈልጋቸው በቀላሉ መገመት አይችሉም። ድርጅታቸው ከሚፈልገው በላይ ጉልበት ያላቸው ሃርድዌር ከገዙ ለአላስፈላጊ ወጪ ይጋለጣሉ፤ ካሳነሱት ደግሞ ሲስተማቸው ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ይቸገራል። ይህንን ዓይነት ችግር ለመፍታት ክላውድ ኮምፒዩቲንግ እጅግ ወሳኝ ቴክኖሎጂ ነው።
እንደ አማዞን፤ ማይክሮሶፍት እና ጉግል የመሳሰሉ ድርጅቶች ብዙ ክፍተኛ አቅም ያላቸውን ኮምፒውተሮችን አዘጋጅተው ለድርጅቶች እና ግለሰቦች ያከራያሉ። ለምሳሌ አንድ ሰው 100 ኮምፒተሮችን ተጠቅሞ ውስብስብ የሆነ የኮምፒውተር ሲሙሌሽን መስራት ቢፈልግ፤ 100 ኮምፒተሮችን መግዛት አይጠበቅበትም ማለት ነው። ከአማዞን እነዛን ኮምፒተሮች ተከራይቶ ተገቢውን ሶፍትዌር ኮምፒተሮቹ ላይ በርቀት (ኢንተርኔት ተጠቅሞ) ይጭናል። የፈለገውን ስራ አከናውኖ የተገኘውን ውጤት ወደ ራሱ ኮምፒተር መውስድ ይችላል። ይህ ሰውዬ እንደዚህ በማድረጉ ብዙ ነገር አትርፏል። አንደኛ ስራው መጀመርያ እንዳሰበው በ100 ኮምፒተሮች ብቻ የማይከናወን ከሆነ በቀላሉ ተጨማሪ ኮምፒተሮችን ማሰማራት ይችላል። ሁለተኛ ደግሞ ሰውዬው ክላውድ ኮምፕዩቲንግ ሲጠቀም የሚከፍለው ብር ልክ እንደ ውሃና ኤሌክትሪክ በተጠቀመበት መጠን በመሆኑ እነዛን 100 ኮምፒተሮች ለ አንድ ሰዓት ብቻ ከተጠቀመ የሚከፍለው በዛ ልክ ብቻ ነው። ይህም ክላውድ ኮምፕዩቲንግን እጅግ አስፈላጊ ከማድረጉም በተጨማሪ ተለጣጭ ወይም (elastic) ባህሪ ያለው ቴክኖሎጂ ያደርገዋል።
የክላውድ ኮምፒዊቲንግ ቀላል ምሳሌ ከፈለግን በሞባይላችን ዳታ መጠባበቅያ (backup) ስናስቀምጥ፤ ኢሜል ስንጠቀም እና ሌሎች ነገሮችን ስናደርግ መረጃችን ያለምንም መጨናነቅ መቀመጣቸው የክላውድ አስፈላጊነትን በሚገባ ያሳዩናል። ስልካችን ቢጠፋም አስፈላጊውን ቅጽ በመሙላት የጠፉብንን ዳታዎች የምናገኘው በክላውድ የተነሳ ነው። ለምሳሌ ፌስቡክን ካየነው ሙሉ በሙሉ ክላውድ መሰረት ያደረገ አፕሊኬሽን በመሆኑ ኢንተርኔት እስካለን ድረስ ማንኛውንም ፌስቡክ ላይ ያደረግነውን እንቅስቃሴ በየትኛውም የዓለም ክፍል ሆነን ማየት እንችላለን።