20/06/2025
የቴምብር ቀረጥ አከፋፈል ልክ
ሰኔ 12/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
📌 በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ መከፈል የሚገባው የቀረጥ መጠን ከታች በሠንጠረዥ
እንደተዘረዘረው ይሆናል፡፡
📌 አንድ ሰነድ በተደጋጋሚ ተፈጻሚ ሲሆን ሊከፈል የሚገባ የቀረጥ መጠን አዚሁ
ሠንጠረዥ ውስጥ የተመለከተ ነው፡፡
19/06/2025
ለደረጃ " ሐ" ግብር ከፋዮች በሙሉ
ከአሁን ላይ ግብርዎን በቴሌብር በቀላሉ እና በፍጥነት መክፈል ይችላሉ።
ይህ አዲስ አገልግሎት ጊዜዎን ለመቆጠብ እና ግብርዎን ምቹ በሆነ መንገድ ለመክፈል ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
እንዴት ግብርዎን በቴሌብር ይከፍላሉ?
ቴሌብር መተግበሪያዎን ይክፈቱ።
"ክፍያዎች" (Payments) የሚለውን ምናሌ ይምረጡ።
"ግብር ክፍያ" (Tax Payment) የሚለውን ይጫኑ።
የግብር መለያ ቁጥርዎን እና የሚከፍሉትን መጠን ያስገቡ።
ክፍያውን ለማረጋገጥ የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
ክፍያዎ እንደተጠናቀቀ የማረጋገጫ መልዕክት ይደርስዎታል።
ለምንድን ነው በቴሌብር መክፈል ያለብዎት?
ምቹነት:- ከየትኛውም ቦታ ሆነው በማንኛውም ጊዜ መክፈል ይችላሉ።
ፍጥነት:- ወረፋ ከመጠበቅ ይድናሉ፤ ክፍያዎም በፍጥነት ይፈጸማል።
ደህንነት:- የቴሌብር ስርዓት አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።
አስተማማኝ የልማት አቅም እንፈጥራለን !!
24/01/2025
በጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ የታክስ ትምህርት ኮሚኒኬሽን ና ቅሬታ አጣሪ ዳይሬክቶሬት ለአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ለደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋዮች የተሰጠ የክህሎት ሥልጠና
23/10/2024
ዛሬ ቀን 13/02/2017 ዓ.ም በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በ ጽ/ኮይራ ቀበሌ በ ገጠር መሬት አዲስ አዋጅ ዙሪያ ከ አርሶአደሮች , ከ ቀበሌ አመራሮች እና ከግብርና ባለሙያዎች ጋር የተደረገ ውይይት።
02/07/2024
ቀን 25/10/2016 ዓ.ም የ2016 የደረጃ "ሐ" ግብር ማስጀመሪያ የውል ስምምነት ውይይት በ አ/ም/ዙ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ኃላፊ በ አቶ ያዕቆብ ኤርምያስ እና በ አ/ም/ዙ/ወ/ን/ገ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ በ አቶ ቱላ ተኬ መሪነት ከ ፈፃሚ ባለሙያዎች ጋር እና ከ ዞን ከመጡ ደጋፊዎች ጋር የተደረገ ውይይት
15/08/2023
ቀን 9/12/2015 ዓ/ም የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሠራተኞች በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ውይይት እየተደረገ
09/07/2023
ግብር ለሀገር ክብር!
ዛሬ ሐምሌ 1/2015 ዓ.ም ዓመታዊ የግብር አሰባሰብ በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በ4 ማዕከላት በደማቅ ስነ ስርዓቶ ተጀምሯል፡፡
***
ከወረዳው በመጡ አመራሮች ; ከዞን ገቢዎች እና ከንግድ ኢንዱስትሪ ለ ድጋፍ በመጡ ባለሙያዎች እና በወረዳው ገቢዎችና ንግድ ኢንዱስትሪ ኃላፊዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል
08/07/2023
ሐምሌ 1/2015 የ ደረጃ "ሐ" አመተዊ ግብረ ተጀመረ የመጀመሪያ ግብር ከፋዮች በመሆናቹ እናመሰግናለን በማለት የምስክር ወረቀት ሠጥተናቸዋል ወ/ሮ ድንቅነሽ ማዴቦ እናመሰግናለን
07/07/2023
የ 2016 በጀት አመት የመጀመሪያ ተግባር የ ሆነውን የ ደረጃ "ሐ" ነጋዴዎች ዓመታዊ ግብር አከፋፈል ዙሪያ ከ ንግድ ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች እና ከ ገቢ ባለሙያዎች ጋር የተደረገ ውይይት ; ኦሬንተሽን እና የምደባ ገለፃ በ ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ እና በ ንግድ ኢንደስትሪ ጽ/ቤት ኃላፊ መሪነት እና ከ ዞን ገቢዎች ለ ድጋፍ ከ መጡ ባለሙያዎች ጋር የተደረገ ውይይት።