Gamo Zone Government Communication Affairs Department

Gamo Zone  Government Communication Affairs Department

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gamo Zone Government Communication Affairs Department, Government Organization, Arba Minch'.

01/06/2026

"ገለልተኛ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ያለው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫው ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የጎላ ሚና አለው።" በጬንቻ ምርጫ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እጩ የተከበሩ እንዳልካቸው አስራት

Photos from Gamo Zone  Government Communication Affairs Department's post 01/06/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ ፤ በትውልድ ስፍራቸው ተገኝተው ድምፅ ሰጡ

‎አርባምንጭ ፡ ግንቦት 24፣2018 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን )

‎በገረሴ ቦንኬ ምርጫ ክልል የድምጽ አሰጣጡ ሂደት ሰላማዊ ፣ ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምጹን እየሰጠ መሆኑን የተለያዩ የፖለቲካ ፖርቲ አባላት ገለፁ

‎የገረሴ ቦንኬ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የተወካዮች ምክር ቤት ተወዳዳሪ ፕሮፌሰር ይስሀቅ ከቸሮና የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪዎች ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀና አቶ ሀኪሜ አየለ በተመዘገቡበት ምርጫ ጣቢያ ድምጽ ሲሰጡ እንዳሉት የነገይቱን ኢትዮጵያ ይመራል ያስተዳድራል ያሉትን ፓርቲ መምረጣቸውንና የምርጫው ሂደት ዲሞክራሲያዊና ፍትሀዊ በሆነ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

‎የባለደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የፌዴራል እጩ ተወዳዳሪ አቶ አቦነህ ጋሞ እንደገለጹት በገረሴ ቦንኬ ምርጫ ክልል የድምጽ አሰጣጡ ሂደት ሰላማዊ ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምጹን እየሰጠ መሆኑን አረጋግጠዋል።

‎የቦንኬ ገረሴ ምርጫ ክልል የኢዜማ የክልል ም/ቤት እጩ ተወዳዳሪ አቶ ኢሳያስ እዮብና የሰላም ኢትየጵያ ጥምረት ፓርቲ የክልል እጩ ተወዳዳሪ አቶ ሙላቱ ሙሴ እንዳሉት ከማለዳው ጀምሮ የድምጽ አሰጣጡ በፍጹም ሰላማዊነት እየተካሄደ መሆኑና ለሚወክላቸው ፓርቲ ድምጻቸውን መስጠታቸውን ገልጸውልናል።

‎በገረሴ ከተማ የምርጫው ሂደት በሁሉም ምርጫ ጣብያዎች በሰከነና ሰላማዊ በሆነ ሂደት ህዝቡ ድምጽ እየሰጠ መሆኑን ለመታዘብ ችለናል።
‎ኤፍኤም 90.9

Photos from Gamo Zone  Government Communication Affairs Department's post 01/06/2026

የኢጋድ ታዛቢዎችም የተገኙበት በአርባምንጭ ምርጫ ክልል ጫሞ ካምፓስ ምርጫ ጣቢያ

Photos from Gamo Zone  Government Communication Affairs Department's post 01/06/2026

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ድምፅ ሰጡ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ድምፃቸውን ሰተዋል።

Photos from Gamo Zone  Government Communication Affairs Department's post 01/06/2026

የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ዶክተር መስፍን መንዛ ሠላምበር ከተማ አስተዳደር ጎርማ ቀበሌ ኖክ ማደያ ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፅ ሰጥተዋል፡፡

ዕጩዎቹ ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ መጀመሩንና ያለምንም ችግር እየቀጠለ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

01/06/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ድምፅ ከሰጡ በኃላ ከጋዜጠኞች ጋር ያደረጉት ቆይታ

Photos from Gamo Zone  Government Communication Affairs Department's post 01/06/2026

ምርጫው ዴሞክራሲን በመትከል ሀገር የምናሻግረበት በመሆኑ መራጩ ሕዝብ በነቂስ በመሳተፍ ታሪክ መስራት ይገባዋል -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ከተማ የመራጭነት ካርዳቸውን በመጣል ድምጽ ሰጥተዋል፡፡

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ለክልሉ ሕዝብ ምክር ቤት በሚወዳደሩበት ምርጫ ክልል፤ በአርባ ምንጭ ከተማ በጫሞ ካምፓስ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት የመራጭነት ካርዳቸውን ተጠቅመው ድምጽ መስጠት ችለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ድምጻቸውን በሰጡበት ወቅት፤ 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፤ ነፃ፤ ፍትሃዊና ታአማኒ ሆኖ በስኬት በማጠናቀቅ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የሚንከፍትበት ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እንደ ሀገር ለምርጫው ዴሞክራሲያዊ ሆኖ በስኬት መጠናቀቅ ነፃና ገለልተኛ ምርጫ አስፈጻሚ ተቋማትን ከመገንባትና ከማጠናካር ጀምሮ ሰፊ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱንም ገልፀዋል፡፡

ምርጫ ዜጎች ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ያጎናፀፋቸውን የዜግነት መብት በአግባቡ ተጠቅመው በካርዳቸው የሚሽቱን አካል በነፃነት በመምረጥ፤ የሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነትን የሚያረጋግጡበት እና በድምጻቸው መንግስት በመመስረት ሀገር የሚያሻግሩበት ወሳኝ የዴሞክራሲ ሂደት መሆኑንም በአጽንኦት ገልፀዋል፡፡

በተለይ የበርካታ ብዝኃ ማንነቶች ባለቤት በሆነችው ሀገራችን ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን የሚንገነባበት ከመሆኑም ባሻገር ሀገራዊ አንድነታችንን የምናጠናክርበት ሂደት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ መራጩ ህዝብ በምርጫው በነቂስ በመሳተፍ፤ በካርዱ ዴሞክራሲን በመትከል ሀገራዊ አንድነትን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የምርጫ ዴሞክራሲያዊነት በቅድመ ምርጫ፤ በምርጫ እና በድህረ-ምርጫ ሂደት ባሉ ነገሮች የሚወሰን መሆኑንም ጠቅሰው፤ የቅድመ ምርጫ ሂደትን እጅግ ሰላማዊ፤ ነፃና ፍትሃዊ በሆነ ሂደት በስኬት በመሻገር ለዛሬው ታሪካዊ ድምጽ መስጫ ዕለት መብቃት መቻሉንም ገልፀዋል፡፡

የዛሬው የድምጽ መስጫም ሆነ የድህረ-ምርጫው ሂደት፤ 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ኢትዮጵያዊያን በሰለጠነ መንገድ፤ በሰከነ ፍትሃዊና ተአማኒ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት እንደሚንችል ለተቀረው አለም የሚናሳይበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

የምርጫው ውጤት ምንም ሆነ ምን በሂደቱ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን ያሸንፋሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ እንደ ሀገር ውደቀታችንን የሚሹ አፍራሽ ኃይሎች ወደ ኋላ ሊጎትቱን በሚጥሩበት በዚህ ወቅት፤ ካርድ የወሰዱ ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን በዚህ ታሪካዊ ምርጫ በድምጻቸው ዴሞክራሲን በመትከል ሀገር እንዲያጸኑ በድጋሚ ጥሪ በማስተላለፍ ሃሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡

Photos from Gamo Zone  Government Communication Affairs Department's post 01/06/2026

“የትናንቷን ኢትዮጵያ የዛሬ አምስት ዓመት አናያትም” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አርባምንጭ ፦ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ( ጋሞ ዞን መ/ ኮሙኒኬሽን )

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትውልድ ስፍራቸው በሻሻ በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ምርጫ የኢትዮጵያን መፃኢ ጊዜ የሚወስን ወሳኝ ሁነት መሆኑን ጠቅሰው፣ “የትናንቷን ኢትዮጵያ የዛሬ አምስት ዓመት አናያትም፤ የተለየች የበለጸገች ሀገር ማየት ደግሞ የሁሉም ኃላፊነት ነው” ብለዋል።

“እኔን ጨምሮ ዛሬ የምንወዳደረው ተመራጮች ትልቅ የሕዝብ አደራ አለብን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገምባት ያለው ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው፤ ይህን ለማሳካት ደግሞ ምርጫ ወሳኝ ነው” ብለዋል።

ይህ ምርጫ በሰላም እንዳይጠናቀቅ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚዘውሯቸው ኃይሎች በስፋት ሲሠሩ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ “ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማድረግ አይቻልም” እያሉ ብዙ ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ገልጸዋል።

በትናንሽ ፕሮፓጋንዳዎች ሸብረክ የማይል እና ታሪክ መሥራት ልማዱ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በእነዚህ ኃይሎች ሳይዘናጋ በነቂስ በውጣት በመምረጥ ላይ ይገኛል፤ ይህም መካሪ እና ገሳጭ ሳያስፈልገው በራሱ ታሪክ እየሠራ እንደሚገኝ ማሳያ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን በሚያስፈልግ ሰዓት መሰብሰብን መዝመትን እና አንድነትን በሚገባ ያውቁበታል ሲሉም ገልጸዋል።

“ይህን ሕዝብ ለማገልገል መመረጥን ይጠይቃል፤ ሁሉም ተመራጮች ሕዝብን ማዕከል አድርገው ሊሠሩ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳስበዋል።

Photos from Gamo Zone  Government Communication Affairs Department's post 01/06/2026

በኢትዮጵያ የሚደረግ ስኬታማ የምርጫ ሂደት ከድንበሯ ባለፈ ትልቅ ትርጉም አለው-ኡሁሩ ኬንያታ

አርባምንጭ፣ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ ኮሙኒኬሽን )

በኢትዮጵያ የሚደረግ ስኬታማ የምርጫ ሂደት ከድንበሯ ባለፈ ትልቅ ትርጉም እንደሚኖረውና በመላው አህጉሪቱ እንደሚያስተጋባ የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ኡሁሩ ኬንያታ ገለጹ።

Photos from Gamo Zone  Government Communication Affairs Department's post 01/06/2026

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) ድምፅ ሰጡ

አርባ ምንጭ፦ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን)

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ከተማ የመራጭነት ካርዳቸውን በመጣል ድምጽ ሰጥተዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው የምርጫ ካርድ በወሰዱበት በአርባ ምንጭ ከተማ በጫሞ ካምፓስ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ነው ድምፃቸውን የሰጡት።

በጋሞ ዞን በሁሉም አከባቢዎች 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን ህዝቡ በነቂስ በመውጣት በምርጫ ጣቢያዎች ድምፃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

Want your business to be the top-listed Government Service in Arba Minch'?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Arba Minch'
NEW