06/10/2025
ጋጮ ባባ ወረዳ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት G/B/W Labor and Social Affairs Office
ይህ ትክክለኛ የጋጮ ባባ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ፌስቡክ ገጽ ነው።
06/10/2025
27/08/2025
14/08/2025
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ባካሄደው 4ኛው ሴክቶሪያል የጋራ ጉባኤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበጀት አመቱ በማህበራዊ ዘርፍ ባከናወናቸው ስራዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለፀ
ጂንካ :-ነሐሴ 7/2017)
ሚኒስተር መስሪያ ቤቱ ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮችን እንደ አፈፃፀማቸው በድጋፍ ክትትልና ሱፐርቪዥን ባደረገው ምልከታ መሠረት በጣም ከፍተኛ፣ ከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ ብሎ የፈረጀ ሲሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በማህበራዊ ዘርፍ ባከናወናቸው ስራዎች ከፍተኛ በሚል መፈረጁ ተገልጿል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ስቡስቤ ቡናቤ እንደገለፁት ቢሮው በበጀት አመቱ የአረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች እና ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ሁለንታዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተቀናጀ መልኩ በተሰራው ስራ የተመዘገበው ውጤት እጅግ አስደሳችና በቀጣዩ የ2018 በጀት አመት ይበልጥ ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።
የቢሮ ኃላፊው አክለውም ቢሮው ላስመዘገበው የላቀ ውጤት
የክልሉ መንግስትና ፓርቲ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ፈፃሚዎች፣ የቢሮው አመራሮችና ባለሙያዎች፣ በየደረጃው የሚገኙ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሴክተር አመራሮችና ባለሙያዎች ላደረጉት አስተዋጽኦም በቢሮው ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች እና ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመደገፍና ለመንከባከብ እንዲሁም በዘላቂነት ለማቋቋም የሚሰራው ስራ በአንድ ተቋም ብቻ የሚሳካ ባለመሆኑ ሁሉም በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት የተለመደውን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲያስቀጥሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
South Ethiopia Region Labour & Social Affairs
ጋሞ ዞን ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ/Gamo zone Labour & Social Affairs Department
13/08/2025
13/08/2025
08/07/2025
!
ለመላው የጋጮ ባባ ወረዳ ግብር ከፋዮች በሙሉ እንኳን የ2017 ዓመታዊ የግብር መክፈያ ወቅት በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን።
በወረዳችን የ2017 ግብር ዘመን ዓመታዊ ግብር ሐምሌ 1/2017 ዓም በይፋ ይጀመራል።
ግብር የዜጎችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን ለማሟላትና የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያግዝ ቁልፍ መሳሪያ ነው።
ስለሆነም የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች ከሀምሌ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚጠበቅባችሁን ግብር በተገቢው በመክፈል የዜግነት ግዴታችሁን እንድትወጡ የጋጮ ባባ ወረዳ ዋና አስተዳደር ክቡር አቶ ብሩክ ቡፃ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።
Mr. Biruk Butsa Gita
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Gacho Baba
Arba Minch'
