የአቶ አሻድሊ ሀሰን መልዕክት
ሠኞ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም
***
ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የህዝብ ሉአላዊነት እና ብቸኛ የሥልጣን ምንጭነት ማረጋገጫ ነው።
እነሆ የዘንድሮው 7ኛው አገርአቀፍ ምርጫ በዛሬው ዕለት እንደአጠቃላይ በመላው ሀገራችን በተለይ ደግሞ በክልላችን በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ሠለማዊ በሆነ መንገድ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በከፍተኛ መነቃቃት እየተካሄደ ይገኛል።
እኔም በአሶሳ ዞን በቡልዲግሉ ወረዳ ምርጫ ክልል በመገኜት ድምፄን ሰጥቻለሁ።
መላ የክልላችን ህዝብ የምርጫውን ፋይዳ ከልብ በመረዳት ድምፁን ለመስጠት ያሳየውን ከፍተኛ መነቃቃት እስከምርጫ ማጠናቂያ ሠዓት ድረስ በማስቀጠል እና ድምፁን በመስጠት በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታችን ውስጥ ታሪካዊ አሻራውን እንዲያስቀምጥ የአደራ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!!
Benishangul Gumuz Education Bureau
የትምህርት ጥራት ተጠብቆ የተማሪዎቻችን ውጤትና ስነ-ምግባር እንዲሻሻል እንሰራለን !!! Equity
30/05/2026
ለትምህርት ቤታቸው ጉልህ አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለውለታ መምህራን የሸለመ የገመሃሩ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
---------- ------------- ------------- -----------
የቀድሞዋ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት የሹሜ የአሁኗ የሰላም በር ርዕሰ መምህርት ትምህርት ቤቱ ዕውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።
በስራ ዝውውር ወደ ሌላ ትምህርት ቤት ለሄዱ መምህራን ትምህርት ቤቱ ዕውቅና ሽልማት ሰጥቷል።
የትምህርት ቤቱ ወተመህ ሰብሳቢ አቶ ነሜ መምህርት ሹሜ
ለትምህርት ቤቱ ዕድገት የተጋች ፤ በስራዋ ታታሪና በለችበትም የተሻለ ውጤት እንድታስመዘግ ተመኝተዋል ፤ መምህራንም ለመምህርቷ ያላቸው መውደድ ክብር ፣ ታታሪነት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ይህን ማህበራዊ መስተጋብር ፣ የምስጋና ፕሮግራም ፣ የጋራ ትብብርን ማጠናከር ለቀጣይ ዓመት ስራ ስንቅ ነው ፤ ሌሎችም ትምህርት ቤቶች ይህን አብነት ብንጋራ እንላለን። ዘገባው የቢሮው ኮሙኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው።
29/05/2026
27/05/2026
የቡለን ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የግንባታ ማስጀመሪያ መሰረተ ድንጋይ በኢ.ፈ,ድ.ሪ ጤና ሚንስቴር ሚንስቴር ደኤታ ክብርት ወ/ሮ ፍሪሕይወት አበበ ፣ በቤ/ጉ/ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ እና በክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ተመስገን ዲሳሳ ተጣለ ።
********
ቡለን ግንቦት 19/2018 ዓ/ም)በፕሮግራሙ የፈደራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የመተከል ዞን አመራር ፣ የወረዳ አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝቷል ።
እንደ ሀገረ የትምህርት ጥራትና አግባብነትን ከመሰረት ለማሻሻል የቀድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ወሳኝ መሆኑን የቤ/ጉ/ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ክብር ዶ/ር ተመስገን ዲሳሳ አሳስበዋል ።
ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በጡሩ ስነ ምግባር የታነጸ ፣ቡቁ አምዕሮ ያለዉ እና በሀገር አቀፍ ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን ለማፍራት የታቀደ ሀገራዊ ፕሮጀክት መሆኑን ዶ/ር ተመስገን ዲሳሳ ገልጿል ። ዘገባው የወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነውደ
26/05/2026
የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር) ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺህ 447ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ ሲል መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
በዓሉም የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ከልብ ተመኝተዋል።
መልካም በዓል!
26/05/2026
ታላቅ የድጋፍ ሰልፈ 👏👏
በአሶሳ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
ግንቦት አሶሳ 18/2018 ዓ.ም — ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ በአሶሳ ከተማ የብልጽግና ፓርቲን የሚደግፍ ታላቅ የሕዝብ ሰልፍ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህ ከማለዳ ጀምሮ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የከተማዋ ነዋሪዎችና የፓርቲው ደጋፊዎች በነቂስ የወጡ ሲሆን፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም ተገኝተዋል። የክልሉ ትምህርት ቢሮ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል። Photos credit Waza Media
25/05/2026
ዛሬ በተመረቀው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደስተኞች ነን ፤ የቡልድግሉ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፦
--------- ------------ ------------- ------------
ተማሪዎችም በአዲስ ትምህርት ቤት ለመማር እንደጓጉና በትምህርታቸው የተሻለ ለማስመዝገብ መነሳሳት አሳድሮብናል ይላሉ፡፡
እንደተማሪ ረሺዳ አብዱረማን ያሉ ሴት ተማሪዎች ቀደም ሲል ሲማሩበት የነበረው ትምህርት ቤት ምቹ ያልሆነና በተለይም ለሴት ተማሪዎች የሚመጥን አይደለም ትላለች፡፡
ተማሪ አሸሪፍ አሻድሊ ፣ ተማሪ ቶፊቅ ኡስማንና ተማሪ እስላም አኑር የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ ምቹና ደረጃው የጠበቀ የትምህርት አካባቢ ለትምህርት ውጤታቸው መሻሻል ጉልህ ድርሻ እንዳለው ተመሳሳይ አስተያየት ሰጥተዋል።
ዘገባው የቢሮው ኮሙኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡
25/05/2026
የቡልድግሉ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጠናቆ በዛሬው ዕለት ተመርቋል
--------- ------------- -------------- ----------------
(ግንቦት 17/2018 ዓ.ም ፤ ቡልድግሉ) በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል በቡልድግሉ ወረዳ የሚገኘው የቡልድግሉ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታው ተጠናቆ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡
በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልላዊ መንግስር ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አሻድሊ ሀሰን ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ፣ የወረዳ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎችና የትምህርት ቤቱ ህብረተሰብ በተገኙበት ትምህርት ቤቱ በደማቅ ስነ-ስርዓት ተመርቋል፡፡
የተማሪዎችን ውጤት ከሚያሻሽሉ ጉዳዮች ማካከል ደረጃቸውን የጠበቁ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ ፤ ለዚህም ምቹ መማሪያ ክፍልና መሰል የትምህርት አገልግሎት ሰጪዎች በዋናነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በቡልዲጊሉ ወረዳ ይሄኛው ትምህርት ቤት ደረጃውን ጠብቆ የተገነባ ሲሆን በቀጣይም ተመሳሳይ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት መንግስስት ቁርጠኛ ነው ተብሏል።
የክልሉ መንግስትም ለትምህርቱ ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት ዘመኑን የሚመጥን የትምህርት ተቋማትን እያስገነባ ይገኛል፡፡ ዛሬ የተመረቀው የቡልዲጊሉ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና በቅርቡ ክቡር ርዕሰ መስተዳድርና የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጋር ሆነው ያስጀመሯቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ የአሶሳ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትና የአሶሳ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ማስጀመራቸው ይታወሳል።
ግንባታው በክልሉ መንግስት ሙሉ በሙሉ የተሸፈነ ሲሆኖ 155 ሚሊየን ብር ገደማ ወጪ የተደረገበት መሆኑን ለማዎቅ ተችሏል። ዘገባው የቢሮው ኮሙኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡
25/05/2026
የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታን ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን አስጀመሩ
---------- ------------ ----------- ------------- -----------------
(ግንቦት 17/2018 ዓ.ም ፤ ቡልድግሉ) በቡልድግሉ ወረዳ የሁለት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታን ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ መሃንዲስ አቶ አበበ ለርዕሰ መስተዳድሩና ለልኡካኖቻቸው ግንባታውን አስመልክቶ ገለጻ አድርገውላቸዋል።
ግንባታው በዚህ ዓመት ተጠናቆ ቀጣይ ዓመት አገልግሎት እንደሚጀምሩ የተገለጹ ሲሆን በክልሉ ትምህርት ቢሮና በኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር 440 ሚሊዮን ብር ገደማ አጠቃላይ በጀት የተያዘለት መሆኑን በክልሉ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ተቋማትና የትምህርት መሳሪያዎች አቅርቦት ዳሬክተር አቶ አብዱልቃድር ሀሰን ነግረውናል። የዘገበው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኮሙኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Asosa
