01/06/2026
አትሌት ሰለሞን ባረጋ በእንግሊዝ የግሬት ማንቸስተር 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ድንቅ ብቃቱን በማሳየት በድጋሚ አሸነፈ
ግንቦት 23/2018 ዓ.ም
አትሌት ሰለሞን ባረጋ ፈታኝ የነበረውን የግሬት ማንቸስተር የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር በ27 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ በማጠናቀቅ አሸንፏል ።
አትሌት ሰለሞን ባረጋ ዘንድሮ ያስመዘገበው የ27 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ ሰዓት፣ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ውድድር ላይ ካስመዘገበው ሰዓት ጋር ሲነጻጸር ከ10 ሰከንድ በላይ መሻሻል ማሳየቱ የዘንድሮውን ድል ልዩ ያደርገዋል።
አትሌት ሰለሞን በአምናው የ2025 የግሬት ማንቸስተር ውድድር ላይ 27 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በሆነ አስገራሚ ፍጥነት በመግባት የራሱን ምርጥ ሰዓት አስመዝግቦ በአንደኝነት ማጠናቀቁ ይታወሳል ።
ዘንድሮ ደግሞ ያንን የራሱን የላቀ ሰዓት በማሻሻል በውድድሩ ላይ ያለውን የበላይነት በድጋሚ አረጋግጧል ።
ምንጭ :-AMN
31/05/2026
የኢትዮጵያ ካራቴ ብሔራዊ ቡድን አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አሸነፈ
*****************
በ2026 የምስራቅ አፍሪካ ካራቴ ሻምፒዮና ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ካራቴ ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው ቀን ውሎ ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን አሸንፏል።
በኬንያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው ውድድር ብሔራዊ ቡድኑ በወንዶች ከ75 ኪሎ ግራም በታች እና ከ53 ኪሎ ግራም በታች፣ እንዲሁም በሴቶች ካታ እና በቡድን ኩሚቴ ባሳየው ድንቅ ብቃት አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አሸንፏል።
በተጨማሪም በወንዶች ከ67 ኪሎ ግራም በታች እና በቡድን ካታ ውድድር ሁለት የብር ሜዳሊያዎች ተገኝተዋል።
በወንዶች ካታ፣ ከ60 ኪሎ ግራም በታች እና ከ84 ኪሎ ግራም በታች ሶስት የነሐስ ሜዳሊያዎች የተመዘገበባቸው ሌሎች ዘርፎች ናቸው።
በናይሮቢ እየተደረገ ያለው የምስራቅ አፍሪካ የካራቴ ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል።
በእሱባለው ተሾመ
30/05/2026
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ቡሩንዲን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ዙር አለፉ
**************
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ቡሩንዲን 2ለ1 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ዙር ማለፋቸውን አረጋገጡ፡፡
የኢትዮጵያን የማሸነፊያ ግብ ምኅረት አለየ እና ሊዲያ እያሱ ሲያስቆጥሩ ኢትዮጵያ በድምር ውጤት 4ለ2 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች።
ኢትዮጵያ በቀጣይ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዋን ከዛምቢያ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ አሸናፊ ጋር የምትጫወት ይሆናል።
30/05/2026
ፒኤስጂ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን በድጋሚ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፈረንሳዩ እግር ኳስ ክለብ ፒኤስጂ አርሰናልን በማሸነፍ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን በድጋሚ አንስቷል፡፡
ፒኤስጂ ከአስቸጋሪ አጀማመር በኋላ አርሰናልን …. በሆነ ውጤት በመርታት ነው ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማሳካት የቻለው፡፡
ጨዋታው በጀመረ በ6ኛው ደቂቃ ካይ ሃቨርትዝ ለአርሰናል የመሪነቷን ግብ አስቆጥሮ የመጀመሪያው አጋማሽ በአርሰናል 1 ለ 0 መሪነት ተጠናቅቋል፡፡
ይሁን እንጂበሁለተኛው አጋማሽ ፒኤስጂ በ65ኛው ደቂቃ በኡስማን ዴምቤሌ የፍጹም ቅጣት ምት ግብ አቻ ሆኗል።
መደበኛ የጨዋታ ጊዜው በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎም ጨዋታው ወደ ተጨማሪ 30 ደቂቃ ያመራ ሲሆን፥ በዚህም ሳይሸናነፉ ቀርተዋል።
በመጨረሻም የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊን ለመለየት በተሰጠ የመለያ ምት ፒኤስጂ አርሰናልን በማሸነፍ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን በድጋሚ ማንሳት ችሏል።
30/05/2026
ፓሪሰን ዠርማ 1-1 አርሰናል ፦ ጨዋታው ወደ ጭማሪ ደቂቃ አምርቷል
AMN ግንቦት 22/ 2018 ዓ.ም
ፓሪሰን ዠርማ ከ አርሰናል እያደረጉት የሚገኘው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ መደበኛው 90 ደቂቃ 1ለ1ተጠናቋል።
ካይ ሃቨርትዝ የመድፈኞቹን ግብ በመጀመሪያው አጋማሽ አስቆጥሯል። ኡስማን ዴምቤሌ ደግሞ ፓሪሰን ዠርማ አቻ ያደረገች ግብ ከፍፁም ቅጣት ምት አስገኝቷል።
ጨዋታው በመደበኛው ደቂቃ ባለመጠናቀቁ 30 ደቂቃ ተጨምሯል።
30/05/2026
አርሰናል 1 - 0 ፒኤስጂ የመጀመሪያ አጋማሽ...
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ አርሰናል ፒኤስጂን 1 ለ 0 እየመራ አጠናቅቋል።
30/05/2026
የክልል አቀፍ የዉስጥ የጠረጴዛ ቴኒስ የነጠላ ሻምፒዮና ተጀመረ !
ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
የክልሉ ቮሊቦል እና ጠረጴዛ ቴኒስ ፌደረሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ይሁን ገድፍ በዉድድሩ መክፈቻ ላይ እንደገለፁት ክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ለአከባቢው ህብረተስብ እና ተተኪ ታዳጊ ወጣቶች ሁሉንም የኦሎምፒክ ስፖርቶች ተደራሽነትና ተጠቃሚነት ከፍተኛ በጀት በመበጀት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዉ ይህ የሻምፒዮና ዉድድር ከፌዴሬሽኑ ዕቅድ አንዱ መሆኑን አብራርተዋል!
በመቀጠልም የፌደረሽን ጽ/ቤት ሃላፊ እንደተናገሩት በዛሬዉ ዕለት በአሶሳ ከተማ ሼህ ሆጄሌ ሁለገብ መዝናኛ የተጀመረዉ ክልል አቀፍ የዉስጥ የጠረጴዛ ቴኒስ የነጠላ ሻምፒዮና ላይ ከሦስት ተቋማት (አሶሳ ዩኒቨርስቲ :ARRS የሰደተኛኞች ተመላሾች እና አሶሳ ከተማ አሰተዳደር ወረዳ 2 ) በዘጠኝ ተወዳዳሪዎች መሀከል ከዛሬ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 28/2018 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑን አስረድተዉ የዉስጥ ዉድድሩም ዓላማ :-
1ኛ. ስፖርቱን በክልሉ የማስፋፋትና ለማነቃቃት
2ኛ. የዉድድር ዕድል ያላገኙ ስፖርተኞች ተሳታፊ ና ተጠቃሚ ማድረግ:
3ኛ. በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደዉ ሻምፕዮና ክልሉን ወክሎ የሚሳተፉ ስፖርተኞች መልምሎ ከወዲሁ ዝግጅት የማድረግ ዓላማዎችን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አብራርተዋል !
በመጨረሻም ተወዳዳሪ ስፖርተኞች ዕጣ የማንሳት ስነስርዓት ተደርጎ ዉድድሩ ተጀምሯል !
ይምጡ ይዝናናሉ !
በተስፋዬ ያደታ
30/05/2026
ስፖርት ኮሚሽን ነጥብ ተጋርቷል!
የክልል ሴክተር ቢሮዎችና ተቋማት ማስ ስፖርት
ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
የዕለቱ ሁለተኛ የጨዋታ መረሀ ግብር ስፖርት ኮማሽን ከ ቤጉ ሚድያ መሀከል የተካሄደ ሲሆን ስፖርት ኮሚሽን ከዚህ ቀደም የነበረበትን ክፍተቶች በማስተካከል በጥሩ አጨዋወት ምድቡን እየመራ ከሚገኘዉ ቤጉ ሚድያ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ዉጤት ነጥብ መጋራት ችሏል !
🏟 ጎሞጁ አርቴፊሻል ሳር ሜዳ
በተስፋዬ ያደታ
30/05/2026
ግብርና ምርም በፎርፌ እሸንፏል!
የክልል ሴክተር ቢሮዎችና ተቋማት ማስ ስፖርት
ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
ግብርና ምርምር ከ ባህልና ቱሪዚም የዕለቱ መረሀ ግብር የመጀመሪያ ጨዋታ የነበረ ሲሆን ባህልና ቱሪዝም ቡድን ከጨዋታ በመቅረቱ ግብርና ምርምር ቡድን 3 ለ 0 በሆነ ዉጤት ፎርፌ አሸናፊ ሆኗል!
🏟 ጎሞጁ አርቴፊሻል ሳር ሜዳ
በተስፋዬ ያደታ
29/05/2026
ሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆን በኃላፊነት ሾመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆ የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ ዋና አሰልጣኝ ሆነዋል፡፡
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆ በሪያል ማድሪድ ቤት እስከ ፈረንጆቹ 2029 ድረስ የሚያቆያቸውን ውል ተፈራርመዋል፡፡
አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም ከፈረንጆቹ 2010 እስከ 2013 ሪያል ማድሪድን ማሰልጠናቸው ይታወሳል፡፡
ምንጭ :- FBC