05/06/2026
መልካም ስነ-ምግባር በአንድ ጀምበር አይገነባም፤ ከልጅነት ጀምሮ በተከታታይ አርአያነት፣ ምክር፣ ፍቅር እና ትክክለኛ መመሪያ በመስጠት ይጎለብታል። መልካም ስነ-ምግባር በሁሉም የእድሜ ክልሎች ሊጎለብት ቢችልም፣ በተለይ በህፃንነትና በወጣትነት ዘመን ይበልጥ መሰረቱን ይጥላል።
☞ ከ0–6 ዓመት፤ ህፃናት የወላጆቻቸውን እና የአካባቢያቸውን ባህሪ በመኮረጅ መሰረታዊ ስነ-ምግባር ይማራሉ።
☞ ከ7–12 ዓመት፤ የሃላፊነት፣ የትብብር፣ የህግና የስርዓት ክብር እሴቶች ይጠናከራሉ።
☞ ከ13–18 ዓመት፤ የግል እሴቶች፣ ታማኝነት፣ ተጠያቂነት እና የስነ-ምግባር ውሳኔ የመስጠት ችሎታ ይዳብራል።
☞ ስለዚህ መልካም ስነ-ምግባር በተለይ በህፃንነት (0–12 ዓመት) የሚጣል መሰረት ነው፤ ከዚያም በወጣትነትና በጉልምስና ይጠናከራል።
“ልጅ በልጅነቱ የተማረው ስነ-ምግባር በህይወቱ ሁሉ ይመራዋል።” የሚለው አባባልም ይህንን ያሳያል። በመሆኑም ወላጆች የልጆቻቸው መልካም ስነ-ምግባር እንዲጎለብት የሚከተሉትን ማድረግ ይገባቸዋል፤
☞ አርአያ መሆን፤ ልጆች ከሚነገራቸው ይልቅ ከሚያዩት ይማራሉ፤ ታማኝነት፣ አክብሮት፣ ሀላፊነት እና ትህትና በተግባር ማሳየት፤
☞ ጥሩ ምክርና መመሪያ መስጠት፤ ስለ ትክክልና ስህተት፣ ሰውን ስለማክበር እና ስለ ተጠያቂነት ቀጣይነት ባለው መልኩ መነጋገር፤
☞ ጥሩ ባህሪን ማበረታታት፤ ልጆች መልካም ተግባር ሲያሳዩ ማመስገንና ማበረታታት።
☞ ሥርዓትና ደንብ ማስያዝ፤ በቤት ውስጥ ግልጽ የሆኑ ህጎችና ደንቦችን ማስቀመጥ እና በተመሳሳይ ሁኔታ ማስፈጸም፤
☞ ከልጆች ጋር ጊዜ ማሳለፍ፤ የልጆችን ችግሮቻቸውን ማዳመጥ፣ ሃሳባቸውን ማክበር እና ጥሩ ግንኙነት መፍጠር፤
☞ መልካም ወዳጅና አካባቢ እንዲኖራቸው መርዳት፤
☞ የመረዳዳትና የመተባበር ባህል ማስተማር፤ ለሌሎች ማሰብ፣ መርዳት እና ማካፈል እንዲለምዱ ማበረታታት፤
☞ የሐይማኖትና የማህበረሰብ እሴቶችን ማስተማር፤ ሥነ-ምግባራዊ እሴቶችን የሚያጠናክሩ ትምህርቶችን ማስተላለፍ ።
04/06/2026
መልካም ስነ-ምግባር የማንኛውም ሰው ባህሪና የህይዎት መሠረት መሆን ሲችል ነገሮች በሙሉ ይስተካከላሉ። ሰዎች በእውነተኝነት፣ በታማኝነት፣ በአክብሮትና በተጠያቂነት ሲኖሩ፣ በቤተሰብ፣ በስራ ቦታና በማህበረ-ሰብ ውስጥ መተማመን ይጠናከራል።
☞ መልካም ስነ-ምግባር ያለው ሰው በሚከተሉት ባህሪያት ይገለጻል፤
☞እውነትን ይናገራል፣ ቃሉንም ይጠብቃል፤
☞ ለተግባሩና ለውሳኔዎቹ ኃላፊነትን ይወስዳል፤
☞ ሁሉንም ሰው በእኩል ያስተናግዳል፣ በእኩል ይዳኛል፤
☞ ለሰዎች አክብሮትን ይሰጣል፤
☞ ሥራን በትኩረትና በብቃት ይሰራል፤
☞ አያጭበረብርም፣ ለግል ፍላጎቱ ቅድሚያ አይሰጥም፤
☞ ለሰዎች ርህራሄንና የመተባበር መንፈስ ያሳያል፤
☞ ጉቦን፣ አድሎአዊ አሰራርንና ሌሎች ብልሹ አሰራሮችን ይቃወማል፤
02/06/2026
ሙስና የመንግስትና የሕዝብን ሐብት ሚያወድም፣ ልማትን የሚያዘገይ እና ፍትሕን የሚያዛባ አደገኛ ተግባር ነው። ሙስና የአንድ ግለሰብ ችግር ብቻ ሳይሆን የማህበረ-ሰብ እና የሀገር እድገትን የሚጎዳ ክስተት ነው። ሁሉም ዜጎች በትብብር ሙስናን ሊታገሉ ይገባል ።
''ትውልድን በስነ-ምግባር ተቋምን በአሠራር !''
☞የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን በተለያዩ አማራጮች ይከታተሉ !!!
☞page ☞ https://web.facebook.com/bgrseacc/
☞Telegram Channel ☞ https://t.me/bgrseaccpr
☞YouTube ☞ https://www.youtube.com/
☞ለጥቆማ ☞ Web.☞https://www.bgrseacc.gov.et/
☞Email: ☞ [email protected]
31/05/2026
መልካም ሥነምግባር ያለው መራጭ ለሀገሩ ዘላቂ ሰላም፣ ለፍትሕ መረጋገጥ እና ለጠንካራ ተቋማት ግንባታ መሠረት የሚጥል ንቁ ዜጋ ነው!
*****************
የአንድን ሀገር እድገት የሚያሳድገውና ወደ ብልፅግና የሚያሸጋግረው በዕውቀት፣ በኃላፊነት ስሜት እና በበሰለ የሞራል እሴት የሚመራ ንቁ ዜጋ ሲኖር ነው።
በአንድ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ የመራጩ ሕዝብ ንቃተ ሕሊና እና የሥነምግባር ደረጃ የሂደቱን ስኬታማነት የሚወስን ዋነኛ ምሰሶ ነው። መራጮች መልካም ሥነምግባርን ተላብሰው ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን ሲወጡ የሚከተሉትን ጥቅሞች ይኖሩታል።
👉 የሕዝብ እውነተኛ ፍላጎት ይንጸባረቃል፦ መራጩ ሕዝብ ከጥቅማ ጥቅም፣ ከዘር ወይም ከማስፈራራት ነፃ ሆኖ በራሱ ሕሊና እና በፓርቲዎች አማራጭ የፖሊሲ ሃሳብ ላይ ብቻ ተመስርቶ ድምፁን ሲሰጥ፣ እውነተኛ የሕዝብ ውክልና ያለው መንግስት ይቋቋማል።
👉 ሰላማዊና ሥርዓታዊ ሂደት ይኖራል፦ ሥነምግባር ያለው መራጭ የሌሎችን የመምረጥና የመመረጥ መብት ያከብራል፤ የሐሳብ ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ ያስተናግዳል። ይህም በምርጫ ወቅትና ከምርጫ በኋላ ሊነሱ የሚችሉ አላስፈላጊ ጉዳዮችን ያስቀራል።
👉 ተጠያቂነት የሰፈነበት ሥርዓት ይገነባል፦ መራጮች ድምጻቸውን በጥንቃቄና በኃላፊነት ስሜት ሲሰጡ፣ ተመራጭ ፓርቲዎችም ቢሆኑ ለሕዝብ ቃል የገቡትን ተግባራዊ ለማድረግና በቅንነት ለማገልገል ይገደዳሉ።
በመሆኑም፣ እያንዳንዱ ዜጋ ወደ ምርጫ ጣቢያ ሲያቀና፣ የሚሰጣት አንዲት ድምፅ የሀገርን የወደፊት ዕጣ ፈንታ፣ ሰላምና ልማት የመወሰን ታላቅ አቅም እንዳላት ማመን አለበት። ይህንን ኃላፊነት በሰላማዊ፣ በታማኝ እና በበሰለ ሥነምግባር መወጣት የሁሉም ዜጋ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል።
!!
ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!
ከፌዴራል የስ-ነምግባርና ፀረ-ሙስና ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ
26/05/2026
ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለኢድ አል-አድሃ /አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! በዓሉ የሰላም፣ የደስታ ፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን!!!
26/05/2026
"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" በሚል መሪ ሐሳብ በአሶሳ ከተማ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ በህዝባዊ ሰልፍ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ…።
20/05/2026
☞ በተቋማት ውስጥ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚያግዙ ስልቶች
☞ የፋይናንስ እና የአስተዳደር ሂደቶችን ግልጽ ማድረግ፤
☞ ውሳኔዎችን ለሕዝብ እና ለሠራተኞች በግልጽ ማቅረብ፤
☞ የግዥ ሂደቶችን በክፍት ውድድር ማካሄድ፤
☞ ህግን በእኩል መተግበር፤
☞ ተጠያቂነትን ማጠናከር፤
☞ ጠንካራ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓትን መዘርጋት፤
☞ የሰራተኞችን ስነ-ምግባር ማሻሻል፤
☞ የገንዘብ እና የንብረት አጠቃቀምን ግልፅ ማድረግ፤
☞ የህዝብ ተሳትፎን ማበረታታት ፤
☞ ጥቆማ ሰጪዎችን ማበረታታት፤
☞ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አሰራርን ማዘመን፤
☞ በየጊዜው ኦዲት እና ክትትል ማድረግ፤
19/05/2026
የክልል ሴክተር መ/ቤት ሴት የመንግሥት ሰራተኞች “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!” በሚል መሪ ቃል ለብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ !
18/05/2026
ተማሪዎች/ ወጣቶች/ እና ማሕበራዊ ሚዲያ …..
ማሕበራዊ ሚዲያ ጥቅሞች እንዳሉት ሁሉ ጉዳቶችም አሉት፡፡ ቴክኖሎጂ በራሱ የሞራል ጠላት አይደለም፤ አጠቃቀሙ ነው ውጤቱን የሚወስነው። የዲጂታል ግብረ-ገብ፣ ኃላፊነት እና ቁጥጥር ካለ ቴክኖሎጂ የተማሪዎችን/ የወጣቶችን/ ስብዕና ሊያጠናክር ይችላል።
☞ማሕበራዊ ሚዲያ/ Social Media/ በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋል ከቻለ…
☞ቴክኖሎጂ ትምህርትን ቀላልና ፈጣን ያደርጋል፤
☞የዓለም እውቀት በቀላሉ እንዲዳረስ ያደርጋል።
☞የፈጠራ እና የምርምር ችሎታን ያዳብራል።
☞አዳዲስ ክህሎቶችን ለመማር ይረዳል፡፡
☞ማሕበራዊ ሚዲያ/ Social Media/ በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋል ካልቻለ፤
☞ተማሪዎች ለስልክና በስልክ ውስጥ ባሉ ጨዋታ/ Game/ ሱስ ይጋለጣሉ።
☞ኮፒ መስራት (Plagiarism) በጣም ይስፋፋል።
☞የግል መረጃ ያለ ጥንቃቄ ይጋራል።
☞ተማሪዎች ከቤተሰብና ከማህበረ-ሰብ እሴቶች ይርቃሉ፡፡
በመሆኑም ወላጆች የልጆቻቸውን የማሕበራዊ ሚዲያ መጠቀሚያ ጊዜ ላይ ገደብ ማድረግ፤ የሚጠቀሙትን ይዘትን መከታተል፤ በትምህርት ቤት መምህራን ለተማሪዎቻቸው ስለ ማህበራዊ ሚዲያ ጥቅምና ጉዳት ማስተማር፤ በትምህርት ጊዜ ላይ ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ መከላከል አስፈላጊ ነው፡፡
14/05/2026
በኮሚሽኑ የ2019 ዓ/ም የበጀት ፍላጎት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡
የክልሉ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በመጪው የ2019 ዓ/ም የፕሮግራም በጀት ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡
ከኮሚሽኑ ተልዕኮ አኳያ በበጀት ፍላጎት ዕቅድ በዋናነት ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች፤ የስነ-ምግባርና ሙስና መከላከል ስልጠናዎችን ተደራሽ ማድረግ፣ በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ሐብትን ማዳን፣ የአሰራር ጥናቶችን በማድረግ ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ አሰራሮች እንዲታረሙ ማድረግ፣ የሐብት አስመዝጋቢዎችን መረጃ ማዘመንና ዲጂታላይዝድ ማድረግ፣ የሐብት ምዝገባ ማጣራትና የዕርምት ዕርምጃ መውሰድ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የክልሉ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ከማል ሃሰን ውይይቱን ሲያጠቃልሉ፣ የበጀት ፍላጎታችንን ካለን ውስን ሃብት ጋር አጣጥመን ውጤታማ ሥራ ለመስራት ከወዲሁ መዘጋጀት አለብን በማለት የማኔጅመንት ኮሚቴውን አሳስበዋል፡፡