23/04/2026
ዛሬ የዓለም መጽሐፍ ቀን ነው
የዓለም መጽሐፍ ቀን፤ የዓለም መጽሐፍ እና ኮፒራይት ቀን ወይም ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን በሚል ስያሜም የሚታወቅ ሲሆን፤ በዩኔስኮ (የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት) የሚዘጋጅ ዓመታዊ ኹነት ነው፡፡
ዓላማውም ንባብን፣ ህትመትንና የቅጂ መብት ጥበቃን ማስፋፋትና ማጎልበት ነው፡፡
የመጀመሪያው የዓለም መጽሐፍ ቀን የተከበረው እ.ኤ.አ. አፕሪል 23 ቀን 1995 ዓ.ም ሲሆን፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየዓመቱ በዚሁ ቀን መከበሩን ቀጥሏል፡፡
የዓለም መጽሐፍና ኮፒራይት ቀን ኹነት ላይ ዩኔስኮ ከመጽሐፍ ኢንዱስትሪው ትላልቅ ዘርፎች ከተውጣጣ አማካሪ ኮሚቴ ጋር በመሆን፣ ለአንድ ዓመት የዓለም መጽሐፍ መዲናን ይመርጣሉ፡፡ ለዓመቱ የተሰየመ የዓለም መጽሐፍ መዲናም መጽሐፍትንና ንባብን ለማክበርና ለማስፋፋት የተለያዩ መርሃግብሮችን ዓመቱን ሙሉ ያከናውናል፡፡
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ!!!
"ዛሬም በንባብ፣ ለንባብ፣ ስለንባብ እንተጋለን!!!"
06/02/2026
ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን እነዚህን የደራሲ ሐብታሙ አለባቸው በቁጥር 10 መጻሕፍትን ለቤተመጻሕፍታችን በተወካያችን በኃይሉ ዘአዋሽ መልካሳ በኩል አበርክቶልናል።
በቤተመጻሕፍታችን ስም ከልብ እናመሰግናለን!!!
"ዛሬም በንባብ፣ ለንባብ፣ ስለንባብ እንተጋለን!"
11/01/2026
እስቲ እንኮራኮር
ያ ደግ ሰው አሮጌ ዕቃ እየገዛ በመሸጥ ወደሚተዳደር መኖር ወደሚባል ወጣት ሰው ዘንድ ሄደ።
ያ ደግ ሰው ወደ መኖር እንዲሄድ ያነሳሳው አንዲት አዲስ ጄሪካን ከአሮጌዎች ጋር አብራ ተንጠልጥላ አይቶ ስለነበር ነው።
መኖርም ምን ፈልገህ ነው ወንድሜ ? እኔ በደህና ዋጋ እገዛሀለው አለው
ያ ደግ ሰው አሮጌ እቃ ለምንድነው ምገዛው አለው
መኖር እየሳቀ አዲስ የሚሰራው እኮ ካሮጌ ነው አለው
ያ ደግ ሰው እስኪ ስለ አሮጌ ትንሽ ንገረኝ አለው
መኖር ከአገልግሎት በኋላ ያለ እረፍት አሮጌ ይባላል ። ደክሞህ እሮጠህ አየር ስትስብ አርጅተህ መልሰህ አዲስ እየሆንክ ነው። እንዲያው ግን ያንዳንድ ነገሮች ማርጀት አይገባኝም
ለምሳሌ አሮጌ መፅሀፍ እና አዲስ መፅሀፍ ይባላል ለአነባበቡ ልዩነት ያለው ይመስል። ምናልባት ግን ሰው እንደ ወረቀት የያዘውን ይዞ ባይቆይ፤ መርሳት ነቀዝ ሆኖ የልቡን ንብረት ቢፈጅበት ፤ ቆይተን ስንመርምር በሰው ልቦና ውስጥም ማርጀት አለ እንላለን። ወደ ወጋችን ስንመለስ ግን ወደ ሠሪው ያልተመለሰ ሁሉ አሮጌ ነው አለው።.
እንዲህ እንዲህ እያለ ይቀጥላል
አሮጌ ሁሉ ወደ ሰሪው ሲሄድ አዲስ ይሆናል አሮጌ በተመልካች እጅ እንጂ በሰሪው እጅ አሮጌ የሚባል እንደሌለ ያወጋናል።
የእለቱ ኮርኳሪ
ከደራሲ፦ ፍቃዱ አየልኝ
ግርባብ 2016ዓ.ም
09/12/2025
እንኳን ለ12ኛ ዓመት የልደት በዓላችን በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ!
ከኅዳር 30/2006 ዓ.ም እስከ ኅዳር 30/2018 ዓ.ም ላለፉት 12 ዓመታት ያለመታከት በቤተመጻሕፍታችን በመሥራችነት፣ አመራርነት፣ በአባልነት ያገለገላችሁ ከሁሉ በፊት እናንተ ቅድሚያ ትመሰገናላችሁ።
መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆናችሁ ተቋማት፣ ግለሰቦች፣ ጉምቱ ጋዜጠኞች፣ ደራስያን፣ ገጣምያን፣ የመጻሕፍት መደብሮች በተለይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት፣ ንባብ ለሕይወት ኢትዮጵያ፣ ጋዜጠኛ በፈቃዱ ዓባይ፣ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ፣ ጋዜጠኛ ቢኒያም ከበደ፣ ጋዜጠኛ አንተነህ ከበደ፣ ጋዜጠኛና ደራሲ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ፣ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ [ዶ/ር]፣ ገጣሚ ይታገሱ ጌትነት፣ ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ፣ መምህርና ደራሲ መዘምር፣ እነሆ መጻሕፍት መደብርና ባለቤቱ አቶ ኤርሚያስ በላይነህ፣ ኤዞፕ መጻሕፍት መደብርና ባለቤቱ አቶ መሳይ፣ ጃዕፈር መጻሕፍት መደብርና ባለቤቱ አቶ ጃዕፈር ሺፋ እና ሌሎችም እስከ አሁን ላደረጋችሁልንና ወደፊትም አብራችሁን ስለምትሆኑ ከልብ እናመሰግናለን!
በድጋሚ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ!
03/12/2025
መምህርቷ ማርታ ነጋሽ በእንገናኝ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ ፩ ቁጥር ፪ ላይ "ጎበዟ ተማሪዬን ምን ነካት" የሚል ጽሑፍ አስነብባናለች።
የአንደኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ወጥተሽ አንብቢ ስባል ፊደላቱን ገጣጥሜ ቃል ለማድረግ የማየውን መከራ ጠላቴም አይየው። በመደነቃቀፌ የሚሳቅብኝ ጣሪያ የሚበሳ ሳቅ አሁንም ጆሮዬ ላይ አለ። ሞክሬ በመሳሳቴ አስተማሪዬ ትሰድበኝ የነበረው ስድብ አንድ በአንድ ስድር ብሎ ከአእምሮዬ ጓዳ ተቀምጧል። ጓደኞቼ ለቀልድ የሚወራወሯቸውን ስድቦች ስሰማ እደነግጣለሁ። ምንም እንዳልመሠለው ሆኜ ብታይም አእምሮዬ የትውስታውን ጦር ሰብቆ ሲወጋኝ ይታወቀኛል።
"ደደብ" የሚለውን ቃል አልወደውም። (የሚወደድ ቃል አይደለም። እኔ እንደምጠላው የሚጠላው ሰው መኖሩን ግን እጠራጠራለሁ።) ሰውን ያህል ነገር በዚህ ቃል ማሳነስ ልክ ነው?
የተማሪው ሳቅ ሳያባራ እያመናጨቀች ወደመቀመጫዬ ስትገፈትረኝ ዕንባ ዕንባ እያለኝ ኩምሽሽ ብዬ እቀመጣለሁ። የጓደኞቼን ዓይን ሽሽት መሬት መሬቱን ማየት ይሆናል ስራዬ። አባቴ ''የኔ ጀግና ልጅ!'' ብሎ ያሞገሰኝ ፤ እማዬ ''የኔ ልጅ እኮ አንደኛ ነች!'' እያለች ያሞካሸችኝ እንዳይከፋኝ ብቻ ይመስለኛል። አስተማሪዬ ያለችኝን አምናለሁ።
ሙሉውን ለማንበብ
https://t.me/engenagndigitalm/312
11/09/2025
እንኳን ለ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!
በዓልን በንባብ የምንዘክርበት መሰናዶ በዚህም ዓመት እያከበርን እንገኛለን!
14/08/2025
አስደሳች ዜና
ቤተመጻሕፍታችን ከኮርፓ ኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ንግድ ዘርፍ ማህበር [ICTET] ከ Ethiopia 2050 Program Digital Economy Task Force ጋራ ባደረገው ስምምነት እነዚህን ኹለት ላፕቶፖች በውሰት ውል ተረክበናል።
ተቋማቱ የኢንተርፕረነርሽፕ ጥረትን ወደ አዳጊ ከተሞች ማስፋፋትን ለማገዝ ባለው ፍላጎት ለዲጂታል ክህሎት ስልጠናና ተዛማጅ ሥራዎች እንዲውል እና እንድንጠቀምበት ነው ስምምነት ያደረግነው።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የቤተመጻሕፍታችን አባል ወጣት በኀይሉ ኢትቻ (በኃይሉ ዘአዋሽ መልካሳ) ቤተመጻሕፍታችንን በመወከል ላፕቶፖቹን ተረክቧል።
የላፕቶፕ ድጋፍ ያደረጉልንን ተቋማት ከልብ እያመሰገንን በዚህ እድል እንድንጠቀም ሰፊውን ድርሻ የተወጣውን የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ መምህሩን መዘምር ግርማን በቤተመጻሕፍታችን ስም ከልብ እናመሰግናለን።
!
15/12/2024
ልክ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ሲሆን የቤተ-መጻሕፍታችንን 11ኛ ዓመት ማክበር እንጀምራለን።
በአዋሽ መልካሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ዝግጅታችንን ጨርሰን የእናንተን [የከተማችንን ነዋሪዎች] መምጣት በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን!
08/12/2024
የ11 ዓመታት ጉዞ በከፊል
ዛሬም በንባብ፣ ለንባብ፣ ስለንባብ እንተጋለን!
08/12/2024
ታኅሣሥ 06_2017 ዓ.ም ተሰባስበን የቤታችንን 11ኛ ዓመት የልደት በዓል እናከብራለንና በአዋሽ መልካሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ እንገናኝ!
07/12/2024
እንኳን ለ11ኛ ዓመት የልደት በዓላችን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!
በነዚህ 11 ዓመታት ሳትታክቱ አብራችሁን የነበራችሁ እና አሁንም ያላችሁ የቤተመጻሕፍታችን አባላት፣ መጻሕፍትን እየተዋሳችሁ ስታነብቡ የነበራችሁ የከተማው ማሕበረሰቦች፣ ደራስያን፣ ጋዜጠኞች፣ የመጻሕፍት ነጋዴዎች፣ መንግሥታዊ ተቋማት፣ ግለሰቦች እና መንግሥታዊ ያልሆናችሁ ተቋማት ከልብ እናመሰግናለን፤ የንባብ ባሕላችን እስኪቀየርና እስኪስተካከል ብሎም ልማድ እስኪሆን ሁሌም እንተጋለን!
አብራችሁን 11 ዓመታት ከዘለቃችሁት መካከል ለማመስገን፦
[ብራና የሬድዮ መሰናዶ]
[ዶ/ር]
[ወመዘክር]
#ወ/ሮ_ሙሉ[ነፍሰ_ኄር]_እና_መላው_ቤተሰቦቻቸውን
ጥቂቶቹ ስትሆኑ በነዚህ ባለፍናቸው ዓመታት በእጅጉ አበርትታችሁናል፣ ደግፋችሁናል ስለበዛው ውለታችሁ በአደባባይ አመሰገንናችሁ!!!
06/12/2024
እንኳን ለ11ኛ ዓመት የልደት በዓላችን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!
በነዚህ 11 ዓመታት ሳትታክቱ አብራችሁን የነበራችሁ እና አሁንም ያላችሁ የቤተመጻሕፍታችን አባላት፣ መጻሕፍትን እየተዋሳችሁ ስታነብቡ የነበራችሁ የከተማው ማሕበረሰቦች፣ ደራስያን፣ ጋዜጠኞች፣ የመጻሕፍት ነጋዴዎች፣ መንግሥታዊ ተቋማት፣ ግለሰቦች እና መንግሥታዊ ያልሆናችሁ ተቋማት ከልብ እናመሰግናለን፤ የንባብ ባሕላችን እስኪቀየርና እስኪስተካከል ብሎም ልማድ እስኪሆን ሁሌም እንተጋለን!
አብራችሁን 11 ዓመታት ከዘለቃችሁት መካከል ለማመስገን፦
ጋዜጠኛ በፈቃዱ አባይ [ብራና የሬድዮ መሰናዶ]
ጋዜጠኛ ቢኒያም ከበደ
ደራሲና ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ
ጋዜጠኛ አንተነህ ከበደ እና ባለቤቱ ሕይወት ታደሰ
ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ
ጋዜጠኛ ሚልኪያስ ጌታቸው
ደራሲ ቃልኪዳን ኃይሉ
ደራሲት ዶ/ር መስከረም ለቺሳ
ኤዞፕ መጻሕፍት መደብር
እነሆ መጻሕፍት መደብር
ምንተስኖት መጻሕፍት መደብር አዳማ
ደራሲ ይባቤ አዳነ
ደራሲ እና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ
ደራሲ እና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ማሞ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት [ወመዘክር]
ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ
መምህር ይኩኖአምላክ መዝገቡ የወመዘክር ዋና ዳይሬክተር
ወ/ሮ ሙሉ [ነፍሰ ኄር] እና ቤተሰቦቻቸው ጥቂቶቹ ስትሆኑ በነዚህ ባለፍናቸው ዓመታት በእጅጉ አበርትታችሁናል፣ ደግፋችሁናል ስለበዛው ውለታችሁ በአደባባይ አመሰገንናችሁ!!!