01/06/2026
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነዉ
በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ የምርጫ ክልል ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው
በገሣ ጫሬ ከተማና በሎማ ቦሳ ወረዳ ህዝቡ በማለዳው የመራጭነት ካርዱን በመያዝ የቀጣይ መንግስቱን እየመረጠ ይገኛል።
ከምርጫው አስቀድሞም ከሌሊቱ 10:00 ጀምሮ በምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ጣቢያ ኃላፊዎች ፣ ታዛቢዎች ፣ የተወዳዳሪ ፓርቲ ተወካዮች በተገኙበት የምርጫ ቁሳቁስ ቆጠራ የተደረገ ሲሆን መራጮች ድምጻቸውን የሚጥሉት ኮሮጆ ባዶ መሆኑ የመፈተሽና መልሶ የማሸግ ስራም ተከናውኗል።
የምርጫ ታዛቢዎቹ ፣ የተወዳዳሪ ዕጩ ተወካዮችና የምርጫ አስተባባሪዎች የመተማመኛ ቃለ ጉባኤ በመፈረምም ወደ መራጮች የድምጽ መስጠት ስራ ጀምሯል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
30/05/2026
በሎማ ቦሳ ምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተከናወነ ነው
በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ ምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የሎማ ቦሳ ምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ ማቴዎስ ማሞ እንዳሉት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅድመ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ እስከ ግንቦት 22 ቀን ድረስ በምርጫ ክልል ስር ለሚገኙ 86 የምርጫ ጣቢያዎች የቁሳቁስ ስርጭት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።
አብዛኛዎቹ የምርጫ ጣቢያዎችም ከትናንት ጀምሮ አስፈላጊውን ቁሳቁስ ተረክበው በጣቢያዎቻቸው ዝግጁ አድርገዋል ሲሉ አቶ ማቴዎስ አክለዋል።
ይህን የቁሳቁስ ስርጭት ሂደት ያለምንም መስተጓጎል በስኬት ለማሳለጥ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
29/05/2026
ሚሊሻ አካባቢውን ሰላም በማድረግ የሕዝቡን ደህንነት የሚጠብቅ ሃይል መሆኑ ተጠቆመ
በሎማ ቦሳ ወረዳ በያሎ ላላ ማዘጋጃ የፊታችን ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለማስፈጸም የሚያስችል የግንዛቤና አዲሱን የሚሊሻ ደንብ ልብስ የማልበስ ሥነሥርዓት ተከናውኗል።
ሚሊሻ ከልማት ተግባሩ ሳይነጠል የአካባቢውን ፀጥታ በማስከበር ለልማቱ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ሃይል እንደሆነም ተገልጿል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
29/05/2026
በዳውሮ ዞን የሎማ ቦሳ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት፣ በመሬት አያያዝና አስተዳደር የአየር ንብረት ማሻሻያ (CALM-P4R) ፕሮጀክት አማካኝነት የአካባቢ ጥበቃን፣ የምግብ ዋስትናን እና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
የሎማ ቦሳ ወረዳ ግብርና አከባቢ ጥበቃና ሕብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ሀጅሦ በቤሮ ያማላ ቀበሌ ተገኝተው በCALM-P4R ፕሮጀክት በማህበር የተደራጁ አባላት እያከናወነ ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ምልከታ አድርገዋል።
ፕሮጀክቱ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በወረዳው ስራ የጀመረ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚያስችሉ የግብርና ተግባራትን ማከናወንና የተፈጥሮ ሀብትን መጠበቅ ነው ሲሉ አቶ ተስፋዬ ገልጿል።
ከአርሶ አደሩ እስከ ወረዳ ባለሙያዎች ድረስ ስለ ተፋሰስ ፅንሰ-ሀሳብና የአየር ንብረት ለውጥ ሰፊ ስልጠና ተሰጥቷል።
በአሁኑ ወቅት በወረዳው 5 ተፋሰሶች ህጋዊ እውቅና አግኝተው፣ የራሳቸው ገቢና ወጪ ያላቸው ማህበራት በመሆን አርሶ አደሩን እያገለገሉ ይገኛሉ ነው ያሉት።
ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጎን ለጎን የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የንብ ማነብ ስራዎች ተስፋፍተዋል። ለ5ቱም ተፋሰሶች የራሳቸው ጽሕፈት ቤት ተገንብቶላቸዋል። እነዚህ ቢሮዎች አስፈላጊ የሆኑ የቢሮ ቁሳቁሶች ተሟልቶላቸው ለተፋሰስ ማህበራቱ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
በቀጣይም ፕሮጀክቱ ያስገኛቸውን ውጤቶች በማስቀጠል፣ በተለይም የአፈር ለምነትን በማሻሻልና በገቢ ማስገኛ ረገድ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በCALM-P4R ፕሮጀክት የታቀፋ የቤሮ ያማላ ጌባኒ ተፋሰስ መሠረታዊ ህብረት ስራ ማህበር አባላት በበኩላቸው፣ በተፋሰስ ልማት መሠረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ አመላክተዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
28/05/2026
የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ሥርዓተ ምግብን ለማሻሻል እንዲሁም አርሶአደሩ በገቢ ረገድ ራሱን እንዲችል ከስልጠና ጀምሮ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ተሳትፏዊ ግብርናና የአየር ንብረት ሽግግር (PACT) ፕሮግራም ድጋፍ በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ ወረዳ ኡጉማኒ የመሬት ገጽታ (Land scape) የሱቦና ላላ አርሶ አደር መስክ ትምህርት ቤት ጉብኝት ተደርጓል።
የወረዳው ስትሪንግ ኮሚቴዎች፣ ቴክኒክ ኮሚቴዎች፣ የቀበሌ ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በአርሶአደሩ መስክ ትምህርት ቤት የተሰሩ መልካም ተሞክሮዎችን የመስክ ጉብኝት አድርጓል።
የሎማ ቦሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስፋው ጮራሞ በዚህ ወቅት እንደገለፁት የአርሶ አደር መስክ ትምህርት ቤት በአነስተኛ ማሳ ትምህርት የሚወስዱበት፣ በተግባር የተደገፈ የልምድና የዕውቀት መቅሰሚያ ማዕከል መሆኑን ገልጿል።
አሁን ላይ የአርሶአደር መስክ ትምህርት ቤት እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ሊበረታታ እንደሚገባ ነው ያሉት አቶ አስፋው ተግባሩን የመሩ አካላትን አመስግነዋል።
ወረዳው በሶስት አየር ንብረት የሚከፍል ስሆን በዚህ አየር ጠባይ የተለያዩ የግብር ተግባራትን በመፈጸም የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ፤ ሥርዓተ ምግብን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም አርሶ አደሩ ኢኮኖሚው እንዲሻሻል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሚገኝ የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብሩክ በላይነህ ተናግረዋል።
ለስኬቱ በተደጋጋሚ የግንዛቤ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ እንደአየር ጠባዩ የሚለሙ የምግብ ችግኞችን በማስራጨት፣ በእንስሳት ተዋጽኦ እንቁላል ጣይ ዶሮችን በመሰጠትና ሌሎችንም ለግብርና ስራ የሚያስፈልጉትን በማቅረብ ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ አክሊሉ አበራ ተናግረዋል።
በተጨማሪም በወረዳው ለሚገኙ ወደ 16 ለሚጠጉ ሥራ አጥ ወጣቶች በፎረስተር ችግኝ ጣቢያ የስራ ዕድል መመቻቸቱን፣ በሥርዓተ ጾታ በኩል የሴቶች ተሳትፎ በሁሉም መስክ ከፍ እንዲል በዚሁ በሁለት ዓመታት አመርቅ ስራ መስራቱ አስተባባሪው ጨምሮ አብራርተዋል።
በጉብኝኝት ወቅት ያነጋገርናቸው ጎብኞች በሰጡት አስተያየት የግብርናና አየር ንብረት ለወጥ ሽግግር ፕሮግራም (PACT) ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከዳውሮ ዞን ግብርና መምሪያና ከወረዳ ግብርና ጋር በመተባበር የፈጸመው ተግባር ያስመሰግነዋል ብለዋል።
በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ስልጣናዎችን ከመስጠት ባሸገር የተለያዩ ድጋፎች በአይነት በማድረግ እኛ የምግብ ዋስትና እንድናረጋግጥ፣ ሥርዓተ ምግብን እንዲንጠቀም እንዲሁም በገቢ ረገድ እራሳችንን እየቻልን እንዲንመጣ አድርጓናል ብለዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
27/05/2026
የ2ኛ ዙር ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!
❇️❇️ የወጣት ባለሀብት አሻራ❇️❇️
በተሰማሩበት የሙያ መስክ በውጤት የተጀበ ወጣት ባለሀብት አለሙ በቀለ በመላው ህዝብ ስም ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን🇪🇹
በገሣ ጫሬ ከተማ አሰተዳደር የካዎ ሀላላ ግሮሰር ባለቤት ወጣት ባለሀብት አለሙ በቀለ፥ ከነበራቸው የልማት ጥማት የተነሳ ሎማ ባሌ-ሚዳ ዘደሊ መንገድ ሥራ ድጋፍ ንቅናቄውን በይፋ በመቀላቀል የ2ኛ ዙር ድጋፍ 1,000 ሺህ ብር (አንድ ሺህ ብር) ገቢ አድርጓል !!! የሀላላ ልጆች ዳግም ታሪክ መስራት ጀምረዋል።
#የሎማ ባሌ-ሚዳ ዘደሊ መንገድ በጋራ እንሥራ! ሌሎቻችሁም ተሳተፉ በውስጥ መስመር አድርሱን እኛም እናደርሳለን!!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000656064459 Bale Mida Zedeli Menged Tigena Gebi
27/05/2026
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ እንዲከናወን መወሠኑ ይታወቃል።
በዚህም መሠረት በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ በዕለቱ ድምፃቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድ እና የደምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራዊ እንዲሆኑ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/ 2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሠረት ለመንግሥታዊ እና ለማንኛውም መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ያሳውቃል።
በዚህም መሠረት:-
- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ፣
- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ዝግ እንዲያደርጉ እያሳወቀ፤
- የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ ሲሆን፤ የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም።
- የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና ዕቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ ያበረታታል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም
27/05/2026
መምህራን ትውልድን በመቅረጽና ሀገርን በመገንባት ረገድ ያላቸው ሚና አይተኬ መሆኑ ተገለጸ
በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አባል መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች ውይይት መድረክ ተካሂዷል።
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሎማ ቦሳ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አየለ አይኑ፤ “መምህራን የሀገር ግንባታ ዋልታ እና ማገር ናቸው። ለሀገር ብልፅግና ትውልድን በእውቀትና በስነ-ምግባር በመቅረፅ የሚያደርጉት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው” ብለዋል።
አፈ ጉባኤው በተጨማሪም፤ “በትምህርት ዘርፍ የሚገኘው ስኬት የሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ትብብርን የሚጠይቅ ሲሆን መምህራን ለተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለማህበረሰቡ ጭምር የለውጥ አርአያ መሆን ይገባቸዋል” ሲሉ ገልጸዋል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህክምና አገልግሎቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምትኩ ታመነ መምህራን ትውልድን በመቅረጽና ሀገርን በመገንባት ረገድ ያላቸው ሚና አይተኬ ነው ብለዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች በበኩላቸው፤ ከመምህራን ጥቅማ ጥቅምና ከትምህርት ግብዓት አንጻር የሚስተዋሉ ክፍተቶች እንዲፈቱም ጠይቀዋል።
በሰነዱ ላይ ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠ ሲሆን፤ መምህራንም በቀጣይ በትምህርት ጥራት፣ በስነ-ምግባር ግንባታና በተማሪዎች ውጤት ላይ የበለጠ ትኩረት በማድረግ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ አስረድተዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
27/05/2026
የ2ኛ ዙር ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!
❇️❇️ የምሁር አሻራ❇️❇️
በተሰማሩበት የሙያ መስክ ግንባር ቀደም በውጤት የተጀበ አቶ ሽፈራው ጮፎረ በመላው ህዝብ ስም ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን🇪🇹
አቶ ሽፈራው ጮፎረ የሎማ ባሌ-ሚዳ ዘደሊ መንገድ የልማት ጥሪ በታላቅ ደስታ ተቀብለው የ2ኛ ዙር 1,000 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ ለሁላችንም አርአያ ሆነዋል። ላሳዩት መልካም ተግባር በወረዳው ህዝብ ስም ልባዊ ምስጋና እናቀርባለን። የሀላላ ልጆች ዳግም ታሪክ መስራት ጀምረዋል።
#የሎማ ባሌ-ሚዳ ዘደሊ መንገድ በጋራ እንሥራ! ሌሎቻችሁም ተሳተፉ በውስጥ መስመር አድርሱን እኛም እናደርሳለን!!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000656064459 Bale Mida Zedeli Menged Tigena Gebi