Harari Region Ethics & Anti corruption Commission

Harari Region Ethics & Anti corruption Commission

Share

ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፣በህብረት እንታገል።

24/06/2026

የትውልድን ሥነምግባር ማነጽ የሁላችንም ድርሻ ነው!

**********************

የትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ለአንድ አገር ዘላቂ ልማት፣ ሰላም፣ ፍትሕ እና መልካም አስተዳደር መረጋገጥ መሠረታዊ አካል ነው። ጤናማ፣ ኃላፊነት የሚሰማው፣ ታማኝና አገር ወዳድ ትውልድ ለመቅረጽ የሚከናወነው ይህ የሥነምግባር ግንባታ በዋናነት በሚከተሉት ቁልፍ ምሶሶዎች ላይ ይደገፋል፡፡

1. ቤተሰብ፡- ቤተሰብ የማኅበረሰብ መሠረት እና የመጀመሪያው የሥነምግባር መቅረጫ ማዕከል ነው። ልጆች መልካም እሴቶችን (ታማኝነት፣ አክብሮት፣ ሩኅሩኅነት እና ታጋሽነት) በመጀመሪያ በተግባር የሚያዩትና የሚቀስሙት ከወላጆቻቸው ወይም ከአሳዳጊዎቻቸው በመሆኑ ቤተሰብ አርዓያ ሊሆኑ ይገባል።

ከዚህ ባሻገር ቤተሰብ ከልጆች የሚያስተውሉትን ስህተቶች በወቅቱ የማረም እና መልካም ባህሪን የማበረታታት ኃላፊነት አለባቸው።

2. የትምህርት ተቋማት፡- ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉት መዋቅሮች መደበኛ ዕውቀትን ከማስጨበጥ ባለፈ የዜግነት ባህሪን የሚገነቡባቸው ቦታዎች ናቸው።

በተለይ የሥነዜጋና ሥነምግባር ትምህርት ሕግ አክባሪነትን፣ ሰብአዊ መብቶችን፣ ብዝሃነትን ማክበርንና ተጠያቂነትን በስርዓተ ትምህርት ውስጥ አካቶ ማስተማርን የያዘ ነው። እንዲሁም የአካዳሚክ ትምህር ደግሞ ታማኝነት በፈተናና በምርምር ሥራዎች ላይ ማጭበርበርን መዋጋት፣ የራስ ጥረትና ጥራትን ያካትታል።

3. የሃይማኖት ተቋማት፡- በማኅበረሰቡ ሕሊና እና የሞራል እሴት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የማሳደር አቅም አላቸው። የሕሊና ዳኝነት ሲኖር ከሕግ አስገዳጅነት ባለፈ፣ በፈሪሃ እግዚአብሔር/በሞራል የታነጸ እና ውስጣዊ እምነትን መሠረት ያደረገ በጎ ባህሪን ያላብሳል።

ከዚህ ባሻገር አገር በቀል እሴቶችም እንደ ዕርቅ፣ አብሮነት፣ ማኅበራዊ ኃላፊነት እና ታማኝነት ያሉ አገር በቀል የባህል እሴቶችን ለትውልድ ማሻገር ሌላኛው ኃላፊነት ነው።

4. የመንግሥት ተቋማት፡- መንግሥታዊ ተቋማት ሥነምግባርን በተግባር የሚተረጉሙበት እና ሥርዓት የሚያስይዙበት ምሶሶ ነው። ተቋማዊ ታማኝነትና ግልጽነት ሲፈጠርና የመንግሥት አሠራሮች ከሙስና እና ከአድልዎ የጸዱ ሲሆኑ፣ ትውልዱ በተቋማት ላይ እምነት ያሳድራል፤ የአሠራር ሥርዓቱንም ያከብራል።

እንዲሁም ጥፋት ያጠፋን የመቅጣት እና በታማኝነት ያገለገለን የማበረታታት የተጠያቂነት ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡

5. የሚዲያ ተቋማት፡- በአሁኑ ዘመን የትውልድን አስተሳሰብ፣ አመለካከትና የትርክት አቅጣጫ በመቅረጽ ረገድ ሚዲያ በተለይም ማኅበራዊ ሚዲያ ትልቅ ድርሻ አለው። በዚህም አርዓያ ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦችን ታሪክ ማጉላት እና የጋራ ብሔራዊ እሴቶችን ማስተዋወቅ ይገባል።

በተለይ የሐሰት መረጃዎችን፣ ጥላቻንና አምባገንነትን በመዋጋት ረገድ ትውልዱ ኃላፊነት የሚሰማው የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆን ማገዝም ያስፈልጋል።

6. ማኅበረሰብ፡- "አንድ ልጅ በባህልና በማኅበረሰብ አብሮነት ያድጋል" እንደሚባለው፣ ግለሰቡ የሚኖርበት አካባቢ ሥነምግባር በትውልዱ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አለው። ማኅበረሰቡ መጥፎ ድርጊቶችን በጋራ የሚያወግዝበት እና በጎ ተግባራትን የሚደግፍበት ማኅበራዊ እሴት ማጠናከር ጠቀሜታው የጎላ ነው።

እንዲሁም ወጣቶች በማኅበረሰብ ልማትና በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ የርኅራኄና የኃላፊነት ስሜትን ማሳደግ ያስፈልጋል።

በአጠቃላይ፣ የትውልድ ሥነምግባር ግንባታ የአንድ ወገን ሥራ አይደለም። እነዚህን ምሶሶዎች በተቀናጀ፣ በተደጋጋፊ እና እርስ በርስ በተሳሰረ መልኩ ሲሠሩ ጠንካራና አስተማማኝ አገራዊ ስብዕና ያለው ትውልድ ማፍራት ይቻላል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።

22/06/2026

የትውልድ ሥነምግባር ግንባታንና የፀረ-ሙስና ትግልን በማቀጣጠል የሀገረ-መንግስት ግንባታን እውን እናድርግ!

********************

በአንድ ሀገር ዘላቂ እድገት፣ ሰላምና ሉዓላዊነት ላይ አስተማማኝ መሰረት መጣል የሚቻለው በትውልድ ስብዕና ላይ ሲሰራ እና የሀገርን ሀብትና ንብረት ከሚያወድሙ እኩይ ተግባራት (ሙስና) የጸዳ ማህበረሰብ ሲገነባ ነው። ይህንን ተልዕኮ እውን ለማድረግ የሚከተሉትን ነጥቦች በንቃት መተግበር ያስፈልጋል።

👉 የትውልድ ሥነ-ምግባር ግንባታ፦ ሥነ-ምግባር የሚጀምረው ከቤተሰብ እና ከታችኛው የትምህርት እርከን ነው። ታማኝነትን፣ ታጋሽነትን፣ ሀገር ወዳድነትን እና የሥራ ክብርን በትውልዱ ውስጥ ማስረጽ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል። በተለይ መሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆች እና ታዋቂ ግለሰቦች ለትውልዱ በተግባር የሚታይ መልካም አርአያ መሆን አለባቸው።

👉 የፀረ-ሙስና ትግልን ማቀጣጠል፦ ሙስናን እንደ ተራ ወይም እንደማይቀሬ ነገር ከማየት ወጥቶ፣ የሀገርና የትውልድ የእድገት እቅፋት መሆኑን በመረዳት መጸየፍና ማጋለጥ ይገባል። በየትኛውም የኃላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኝ ግለሰብ በፈጸመው የሙስና ተግባር የሚጠየቅበት ግልጽ እና ጠንካራ አሰራር መዘርጋት ያስፈልጋል።

👉 የሀገረ-መንግስት ግንባታ፦ በግለሰቦች ፍላጎት ላይ የማይመሰረቱ፣ ገለልተኛ፣ ጠንካራ እና ህግን ብቻ የበላይ የሚያደርጉ ተቋማትን መገንባት አስፈላጊ ነው። ብዝሃነትን ያከበረ፣ ሁሉንም ዜጋ በእኩልነት የሚያሳትፍ እና ወደ አንድ የጋራ የብልጽግና ግብ የሚያራምድ ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል።

በአጠቃላይ፣ ያለ ሥነ-ምግባር እና ያለ ፀረ-ሙስና ትግል ጠንካራ ሀገረ-መንግስትን መገንባት አይቻልም፤ እያንዳንዱ ዜጋ ከራሱ ጀምሮ ለዚህ አላማ ሲቆም ሀገራዊ ህልማችን እውን ይሆናል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።

21/06/2026

ከተመሠረተ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ፣ መሶብ የኢትዮጵያን የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት መሠረታዊ በሆነ መንገድ ለውጦታል።

ውጤቶቹም በራሳቸው ይናገራሉ።

Photos from Harari Region Ethics & Anti corruption Commission's post 04/06/2026

በኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ላይ ለኮሚሽኑ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ።

ግንቦት 27/9/2018
ሀረር

የሀረሪ ክልል የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናው ከሀረሪ ክልል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ተሰጥቷል።

በስልጠናው ላይ ኤች አይ ቪ የሚተላለፍባቸው መንገዶች፣ የመከላከያ ዘዴዎች፣ የቅድመ ምርመራ አስፈላጊነት እና አለም አቀፍ፣ ሀገር አቀፍና እንደ ድሬደዋ የስርጭት መጠን እና ይበልጥ ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ስልጠናውን ከሀረሪ ክልል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከል ይበልት ተጋላጭ አስተባባሪ ባለሞያ ወ/ሪት ምህረት ገ/ወልድ የሠጡ ሲሆን የመንግስት ሰራተኞች በስራ ቦታቸው እና በማህበረሰቡ ውስጥ ትክክለኛ መረጃን በማስተላለፍ በበሽታው መከላከል ላይ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።

በኮሚሽኑም የሴቶች:ህፃናት ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ነጀሓ አህመድም ሰራተኞች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት በስራ ቦታቸውና በማህበረሰብ ውስጥ በማጋራት
የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

26/05/2026

🌙✨ እንኳን ለ1447 ዓ.ሂ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ✨🌙
=============//===============

የሀረሪ ክልል የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የ1447 ዓ.ሂ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የሰላም፣ የደስታ እና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን ከልብ የመነጨ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

ኢድ ሙባረክ! 🌙✨

14/05/2026
Photos from Harari Region Ethics & Anti corruption Commission's post 14/05/2026

ኮሚሽኑ በመልካም አስተዳደር እና አዲሱ የሲቭል ሰርቪስ ፖሊሲ ላይ ስልጠና ሰጠ።
**

ግንቦት 06/2016 ዓ.ም
ሀረር

የሀረሪ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአዲሱ ሰቭል ሰርቪስ የሰራተኞች ፖሊሲ ዙሪያ ለሰራተኞቹ ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናውም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አዳል ሙላቱ ተገኝተው በአዲሱ ፓሊሲ ስልጠና መዘጋጀቱ ሁሉም ሰራተኛ መብቱን እና ግዴታውን አውቆ በመስራት የሚሰራውን ስራ ተግባር ውጤት ተኮር አድርጎ እንዲሰራ ያነቃቃል ብሏል።
የግንዛቤ ስልጠናውን ሰነድ ወ/ሮ አይሻ አብደላ የኮሚሽኑ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የስልጠናውን ሰነድ በማቅረብ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በመጨረሻም ስለጠናዉ መሰጠቱ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ተሳታፊዎች በስነምግባር አገልግሎትን በመስጠት ሚናቸዉን እነደሚወጡ ገልፀው ፖሊስው መውጣቱም ጥሩ መሆኑን ገልጿል።

Photos from Harari Region Ethics & Anti corruption Commission's post 13/05/2026

ኮሚሽኑ በትምህርት ቤቶች እየተሰጠ ያለው የተማሪዎች ስነ ምግባር ግንባታ ግንዛቤ መፍጠሪያ እንደ ቀጠለ ነው።

ግንቦት 05/2018
ሀረር

ዛሬም በአባድር ወረዳ በሚገኘው አውመጀዲን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኮሚሽኑ የአውተር ክፍል ባለሙያዎች በመገኘት ለተማሪዎች በስነ ምግባር ግንባታ; ሙስና ዙሪያ እና ኩረጃን በተመለከተ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄዷል።
በግንዛቤውም ተማሪዎች ሊያጎለብቱ የሚገባው ስነ ምግባር እንዲሁም ኩረጃን እና ሙስናን ተፀይፎ በማደግ ለሀገርቷ ተረካቢ ተስፋ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑና በቀጣይም ወደ ሌላ ት/ቤቶች የሚቀጥል መሆኑ ነው።

Want your business to be the top-listed Government Service in Harar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Harar

Opening Hours

Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00