ADAL PRESS 405

ADAL PRESS 405

Share

Beware of speaking too much, for it increases mistakes and engenders boredom.

29/05/2026
28/05/2026

ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በህይወት ዘመናቸው 420 ጁምአ ሰላት ኹጥባ«ንግግር »አድርገው አንድ ኹጥባ እንኳን በሐዲስ አልተዘገበም

28/05/2026

ወደ አንተ በንግግር (በሐዲስ) ሲመጡ... እንዲህ በላቸው፡
"በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?" (አል-ኒሳእ: 87)
​እገሌም እንዲህ አለ እያሉ ሲመጡብህ... እንዲህ በላቸው፡
"በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?" (አል-ኒሳእ: 122)
​የኢማሞቻቸውንና የሸይኾቻቸውን መጻሕፍት ይዘውልህ ሲመጡ... እንዲህ በላቸው፡
"ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል፡፡ እነዚያንም በጎ የሚሠሩትን ምእመናን ለእነሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መኾኑን ያበስራል።" (አል-ኢስራእ: 9)
​የመሻይኾቻቸውን ማብራሪያ (ተፍሲር) ይዘውልህ ሲመጡ... እንዲህ በላቸው፡
"በማንኛውም ምሳሌ አይመጡብህም፣ እውነትንና የተሻለ ማብራሪያን ያመጣንልህ ቢሆን እንጂ።" (አል-ፉርቃን: 33)
​የአባቶቻቸውንና የቀደምቶቻቸውን (የሰለፎችን) መንገድ እንከተል ባሉህ ጊዜ... እንዲህ በላቸው፡
"ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» በል።’" (ዩሱፍ: 108)
​ መዝሃቦቻቸውንና መንገዶቻቸውን እንድትመርጥ ባቀረቡልህ ጊዜ... እንዲህ በል፡
«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡» (አል-አንዓም: 153)
​አላህ እውነትን ተናገረ... ቀጣፊዎችም ዋሹ።

24/05/2026

ቢላል ኢብኑ ረባሕ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በኢስላም ታሪክ ውስጥ እጅግ ከሚወደዱ፣ ከሚከበሩና ስማቸው በደመቀ ሁኔታ ከሚነሳ ታላላቅ ሰሐባዎች (የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ባልደረቦች) አንዱ ናቸው። በተለይም የመጀመሪያው የኢስላም ሙአዚን (የሶላት ጥሪ አድራጊ) በመሆን ይታወቃሉ።
ቢላል ኢብኑ ረባህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በጀነት መግባታቸው በነቢዩ ﷺ አንደበት በተደጋጋሚ የተመሰከረላቸው ታላቅ ሰሐባ ሆነው ሳለ፣ «አስሩ በጀነት የተመሰከረላቸው» (አል-ዐሸራ አል-ሙበሸሩነ ቢል-ጀናህ) በሚለው ታዋቂ ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም።
​«ነቢዩ ﷺ [ለቢላል] “በጀነት ውስጥ ከፊቴ የጫማህን ኮቴ (ድምፅ) ሰምቻለሁ” በማለት አብስረውታል።»
ታዲያ 10 ሰሐቦች ብቻ ተለይተው በዝርዝር መቀመጡ ፣ እንዴት ነው ነገሩ?

23/05/2026

ቁርአንን አንከተልም ሐዲስን እንጂ ለምትሉ ወገኖች ይሁን

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
የተከበረውን የአላህን ቃል በቁርአን ውስጥ ቆም ብለን ብናስተነትን ኖሮ፣ ቁርአን አንድ ሙስሊም ከእሱ ውጭ ሌላን ሳይሻ ሊጠነቀቅበትና ሊይዘው የሚገባ ብቸኛው መጽሐፍ መሆኑን በረጋገጥን ነበር። እንዲሁም ቁርአን እነዚህን የሰዎች መጻሕፍት ፈጽሞ እንደማይሻ በተረዳን ነበር፤ ምክንያቱም የተከበረው ቁርአን አንዳችም ነገር አላስቀረም (አልበደለም)፣ ሁሉንም ነገር ግልጽ ለማድረግ ወርዷል፣ ማብራሪያና ዝርዝር ለሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ዝርዝር ማብራሪያ ይዞ መጥቷልና።
​ቁርአን እርሱ ማስታወሻ (ዚክር) ነው፤ እርሱ ጥበብ (ሒክማ) ነው፤ እርሱ ቀጥተኛው መንገድ (ሲራጠል ሙስታቂም) ነው፤ እርሱ ምንም ጥርጥር የሌለበት እውነት (ሐቅ) ነው። በመጨረሻም፣ ቁርአን ብቸኛው የኢስላም ምንጭ ነው፤ ሊሆን የሚገባውም ይህው ነው። እውን ከሆነማ፣ ኑና በዚህ ዙሪያ ያሉትን የአላህን አንቀጾች (አያቶች) እንመርምር።»
ልዑል አላህ ስለ ገናናው ማንነቱ እንዲህ ይላል፦

وَاتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن كِتَابِ رَبِّكَ ۖ لَا مُبَدِّلَ لِكَلِمَاتِهِ وَلَن تَجِدَ مِن دُونِهِ مُلْتَحَدًا

ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ለቃላቶቹ ለዋጭ የላቸውም፡፡ ከእርሱም በቀር መጠጊያን በፍጹም አታገኝም፡፡

ስለዚህ፣ በውሳኔውና በፈርዱ ላይ አንዳችም አካልን የማያጋራው ብቸኛው ረዳትና ጠባቂ (ወሊይ) አላህ ብቻ ነው።
​ቁርአንም ቢሆን፣ ወደ ነቢዩ የተወረደ፣ ለቃላቶቹ መለወጥ የሌለበት ብቸኛው መጽሐፍ እርሱ ነው፤ ነቢዩም ከቁርአን ውጭ የሚጠጉበትና የሚማጸኑበት ሌላ መጽሐፍ ከቶ አያገኙም።
​ነቢዩም ቢሆኑ፣ ጌታና አምላክ አድርገው ከልዑል አላህ በቀር ወደ ሌላ አይጠጉም (አይማጸኑም)፤
ነቢዩም ቢሆኑ፣ የሚጠጉበትና የሚማጸኑበት (ሙልተሐድና መልጃእ) ከቁርአን ውጭ ሌላ የላቸውም፤
‹ከጌታህ መጽሐፍም ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፤ ለቃላቶቹ ምንም ለዋጭ የለም፤ ከእርሱም ሌላ መሸሸጊያን (የምትጠጋበትን) ፈጽሞ አታገኝም።›
​ይህ ለነቢዩ (ሰ. ዐ. ወ) የተባለ ከሆነማ... ታዲያ እኛማ እንዴት ልንሆን ይገባል?!»

20/05/2026

18/05/2026

Want your business to be the top-listed Government Service in Harar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Harar