25/06/2026
በጅዳ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ት/ቤት የቅድመ-መደበኛ ትምህርት እና የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ የተማሪዎች ምረቃ በዓል ተካሄደ፣
(ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ጅዳ) በጅዳ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ት/ቤት የቅድመ መደበኛ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲሁም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ምረቃ በዓል ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በጅዳ በድምቀት ተካሄደ። በፕሮግራሙ ላይ የት/ቤቱ የትምህርት አመራር ቦርድ አመራር እና አባላት፣ የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር እና ማኔጅመንት አባላት፣ መምህራን እና ሰራተኞች፣ የተመራቂ ወላጆች እንዲሁም ተመራቂ ተማሪዎች በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል።
በፕሮግራሞቹ ላይ በጅዳ ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤት ምክትል ቆንስል ጀኔራል እና የቆንስል ጀኔራሉ ተወካይ የሆኑት አቶ ለዓለም ጥላሁን ባስተላለፉት መልዕክት የትምህርት ዓላማ እውቀትን እና ክህሎትን ማስጨበጥ ብቻ ሳይሆን የተሟላ ስነምግባርና ጠንካራ ስብዕና ያለው ዜጋ መቅረጽ መሆኑን ጠቅሰው፣ ምሩቃን ለውጤት እንዲበቁ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ አባላት እና ወላጆች ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም የመማር መስተማሩ ተግባር ስኬታማ እንዲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በሙሉ ከት/ቤቱ የትምህርት አመራር ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት ጋር በመቀናጀት የበኩላቸው አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል። በማስከተልም ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤቱ ት/ቤቱ የተጣለበትን ኃላፊነት በስኬት እንዲወጣ በመጪው 2026/27 የትምህርት ዘመን ከት/ቤቱ ቦርድ፣ የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ጋር ያለውን ጠንካራ ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በመልዕክታቸው ማጠናቀቂያ ላይ ለኢትዮጵያውያን የ12ኛ ክፍል ተመራቂ ተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት በቀጣይ የትምህርት እና የስራ ህይወታቸው የዲጅታሉ ዓለም የፈጠረላቸውን ዕድል በመጠቀም የሀገራቸው ኢትዮጵያን ባህል እና መልካም ዕሴቶች እንዲሁም የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ እንዲያስተዋውቁ ጠይቀዋል። በመጨረሻ ላይም ለተመራቂ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ተሰጥቶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
17/06/2026
. 📌ታድሶ የመጣ ፓስፖርት📌
*********************
አዲስ ፓስፖርት ተሰርቶ የመጣላችሁ ዜጐቻችን የስም ዝርዝራችሁን በማየት እና ተራ ቁጥራችሁን በመያዝ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 1 በአካል በመቅረብ ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ቆንስላ ጽ/ቤቱ ያሳውቃል።
ማሳሰቢያ፡-
አመልካቾች ፓስፖርት ለመውሰድ ስትመጡ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ላይ ከስማችሁ ትይዩ የተመለከተውን የኮድ ቁጥር መዝግባችሁ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችዃል፣
በተጨማሪም ሙሉ ዝረዝሩን በቆንስላ ጽ/ቤቱ የቴሌግራም ቻናል በሚከተለው ማስፈንጠሪያ በኩል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን:-
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20@
16/06/2026
. 📌ማስታወቂያ📌
*********************
ተጨማሪም መረጃዎችን በቆንስላ ጽ/ቤቱ ማኅበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ በሚከተሉት ማስፈንጠሪያ (Link) በኩል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን:-
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20@ See less
15/06/2026
. 📌ማስታወቂያ📌
*********************
ተጨማሪም መረጃዎችን በቆንስላ ጽ/ቤቱ ማኅበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ በሚከተሉት ማስፈንጠሪያ (Link) በኩል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን:-
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20@
13/06/2026
. 📌ታድሶ የመጣ ፓስፖርት📌
*********************
አዲስ ፓስፖርት ተሰርቶ የመጣላችሁ ዜጐቻችን የስም ዝርዝራችሁን በማየት እና ተራ ቁጥራችሁን በመያዝ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 1 በአካል በመቅረብ ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ቆንስላ ጽ/ቤቱ ያሳውቃል።
ማሳሰቢያ፡-
አመልካቾች ፓስፖርት ለመውሰድ ስትመጡ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ላይ ከስማችሁ ትይዩ የተመለከተውን የኮድ ቁጥር መዝግባችሁ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችዃል፣
በተጨማሪም ሙሉ ዝረዝሩን በቆንስላ ጽ/ቤቱ የቴሌግራም ቻናል በሚከተለው ማስፈንጠሪያ በኩል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን:-
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20
11/06/2026
በሳዑዲ አረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ 1655 ኢትዮጵያውያን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ እንዲሰጣቸው ተደረገ
___________________________
(ሰኔ 04 ቀን 2018 ዓ.ም.አዲስ አበባ): የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪያድ የሚገኘውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮን እና ጂዳ የሚገኘውን ቆንስላ ጽ/ቤት በማስተባበር ባደረገው የዲፕሎማሲ ጥረት በሳዑዲ አረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ 1655 ዜጎቻችን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ እንዲሰጣቸው ተደርጓል።
ይህ ውጤት መንግሥት በውጭ ግንኙነቱ ለዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ትኩረት የተገኘ ነው።
ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አኳያ በሳዑዲ አረቢያ ቀሪ የዲፕሎማሲ ጥረት የሚሹ ጉዳዮችን በተመለከተም ክትትል እያደረገ ነው።
በዚሁ አጋጣሚ መንግሥት ሕብረተሰቡ ከሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በማኅበራዊ ሚዲያ የታጀበ ሀሰተኛ ማታለያ ድርጊት የውጭ አገር ጉዞ ራሱን እንዲጠብቅ እያሳሰበ፤ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን የሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።